ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሐኪም ቤት መግባቱ ተገለጠ (ዶይቸ ቬለ)

Temesgen Desalegnበእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ረፋዱ ላይ ዝዋይ ባቱ ሐኪም ቤት እንደገባ የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ለዶይቸ ቬለ ተናግሯል። በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ረፋዱ ላይ ዝዋይ ባቱ ሐኪም ቤት እንደገባ ተሰምቷል። የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ለዶይቸ ቬለ ዛሬ እንደገለፀዉ ጋዜጠኛ ተመስገን በምን ኹኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ ወደ ሐኪም ቤቱ ሄደው ቢጠይቁም መግባት እንደተከለከሉ ገልጧል።

ታሪኩ ጋዜጠኛ ተመስገንን ካለፉት ዐሥር ቀናት አንስቶ ማየት እንዳልቻሉ፥ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝም እንደማያውቁ አስታውቋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይገኝበታል የተባለው የባቱ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኑራ ነገዎ «እንደዛ የሚባል ሰው እኛ ጋ አልገባም» ሲሉ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

Read previous post:
Ethiopian FM: Opposing Groups are Working in Egypt, Authorities yet to Comment

Aawsat.com -Ethiopian government announced that it is cooperating with the Egyptian government, yet still awaits a response to the official...

Close