ኃይሌ ወደ ሩጫው ዓለም መመለሱን አስታወቀ

የሠላሳ ሰባቱ ዓመት ታዋቂ አትሌት የለንደን ኦሎምፒክን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ውድድሮች መወዳደሩን እንደሚቀጥል ገልጿል።

የኃይሌ የውድድሮች ሥራ አስኪያጅ ጆስ ሔርሜስ ባለፈው ሳምንት የኒው ዮርክ ማራቶን በሕመም ምክንያት አቋርጦ ከወጣ በኋላ ወደ ውድድር ይመለሳል የሚል እምነት እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል።

የኃይሌን ከሩጫው ዓለም በድንገት የመሰናበት ጉዳይ ብዙዎችን ሲያዝንና ታዋቂ አትሌቶች፣የመገናኛ ብዙኃንና ሌሎች በአትሌቲክስ መስክመ የሚሰሩ ባለሙያዎች ውሳኔው በሚገባ ያልታሰበበት ነው ማለታቸው ይታወሳል።

አትሌት ኃይሌ ከዓለማችን የምንጊዜም ምርጥ አትሌቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑን የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው።

Read previous post:
Marathon Sunday: A New Ethiopian Champ Wins the Marathon, a Chilean Miner … – WNYC

The race kicked off with a scramble across the Verrazano Narrows Bridge and runners coming off the exit at Dahlgren...

Close