ዶ/ር ነጋሦ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት መሆናቸው ተነገረ

የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለሁለተኛ ጊዜ እስር ቤት ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ የምክትል ፕሬዝዳንትነት ኃላፊነት ይዘው ፓርቲውን በበላይነት ሲመሩ የነበሩት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ምክንያት የሆነው ድርጅቱ ያዘጋጀው የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ መሆኑንም የሪፖርተራችን ዘገባ አመልክቷል። የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ባለፈው ቅዳሜና እሑድ ባደረገው ስብሰባ የአምስት ዓመት እቅድና የስትራቴጂ ሰነድ ይፋ አድጓል። … [Read more...]

የጥቁርና ነጭ ፖለቲካችን መክሰምና የሶስተኛ አማራጭ መሰረት መጣል

ኢዴፓን በመመስረቱ ሂደት ተሳትፎ የነበራቸው “የ3ኛ አማራጭ ጠንሳሾች” በተቃዋሚው ጎራ ውስጥ ጎላ ጎላ ብለው የሚስተዋሉ ችግሮችን በዝርዝር አቅርበው ከተወያዩ በኋላ “ለእነዚህ ችግሮች መፍትሄው ምንድን ነው? ምንስ መደረግ አለበት?” የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት የመፍትሔ ሃሳቦችንም አስቀምጠዋል፡፡ መደረግ የሚገባውን አቅጣጫም ለማመላከት ጥረት አድርገዋል፡፡ ከመፍትሄ ሃሳቦቹ መካከልም የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው። እነሱም፡-•    የፍረጃ ፖለቲካን በተመለከተ፣ በሀገሪቱ ለዘመናት … [Read more...]

እነ አቶ ገብሩ አስራት ከአረና ትግራይ ፓርቲ ተባረሩ ተባለ

የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ ባለፈው ቅዳሜ ጥር 21 ቀን 2003 ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ በአቢሲኒያ ሜዲካል ኮሌጅ አዳራሽ የተደረገ ሲሆን፣ በዚሁ ስብሰባ ላይ ነባሩ የፓርቲው አመራር (እነ አቶ ገብሩ አስራት) ተነስቶ አዲስ አመራር ተመርጧል፡፡ ይህንን ስብሰባ እነ አቶ ገብሩ እንደማያውቁትና “የተደረገው ስብሰባ ህጋዊነት የለውም፣ ፓርቲውን ለማጥፋት የሚደረግ ዘመቻ አካል ነው” በማለት እየገለጹ መሆኑም ታውቋል፡፡በዚሁ ስብሰባ የፓርቲው ጊዜያዊ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ … [Read more...]

የመኢአድ ጉድ ቀጥሏል፤ ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ታገዱ!

የእገዳ እርምጃውን በቅድሚያ የወሰደው የኢ/ር ኃይሉ ቡድን ሲሆን፣ ኢ/ር ኃይሉ ራሳቸው ጥር 13 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፉት ደብዳቤ አራት የስራ አስፈጻሚ እና አስር የላዕላይ ምክር ቤት፣ በድምሩ 14 የፓርቲውን ከፍተኛ አመራር አባላት ማገዳቸውን አስታውቀዋል። ኢ/ር ኃይሉ ይህንን የእገዳ እርምጃ የወሰዱት አስራ አራቱ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት አባሪ ተባባሪ በመሆን ከጉባዔው በፊት፣ በጉባዔው ወቅትና ከጉባዔው በኋላ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ውጪ ጠቅላላ ጉባዔው … [Read more...]

የሳምንቱ ጋዜጦች ዳሰሳ

የኑሮ ውድነትን በተመለከተ፤በሳምንቱ መጀመሪያ አካባቢ የወጣው ሳምንታዊው መሰናዘሪያ ጋዜጣ በፊት ለፊት ገጹ “የዘይት ዋጋ ጨመረ” በሚል ርእስ ይጀምራል። ጋዜጣው መንግስት ያወጣውን የሸቀጦች ዋጋ ዝርዝርም ለአንባብያን ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ በውስጥ ገጹ ላይ አትሟል።በየሳምንቱ ረቡዕ የሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ በበኩሉ፣ “የዋጋ ተመኑ በሌሎች ሸቀጦች ላይም ይቀጥላል” በሚል ርእስ የንግድ ሚኒስቴርን በመጥቀስ የዜና ዘገባ አቅርቧል። መንግስት በሀገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ንረት … [Read more...]

የማሙሸት ቡድን ማህተም ይዞ ተሰወረ፤ ኢ/ር ኃይሉ ሌላ ማህተም አስቀረጹ

መኢአድ በአሁኑ ወቅት በለየለት መልኩ ለሁለት የተከፈለ መሆኑን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ በትናንትና እትሙ ባቀረበው ዘገባ አመልክቷል። በዚህም መሰረት በአንድ በኩል በኢ/ር ኃይሉና በአቶ ያዕቆብ ልኬ የሚመራ ቡድን እየጎላ የመጣ መሆኑንና ይኸው ቡድን ሰሞኑን በወሰደው እርምጃ እነ ማሙሸት አማረ የሰወሩትን ማህተም የሚተካ አዲስ ማህተም አስቀርጿል። ለዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ፣ ለአቶ ገ/ጻዲቅ ኃ/ማሪያም እና ለአቶ ማሙሸት አማረ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፉም ታውቋል።ፓርቲውን … [Read more...]

እነ ፕ/ር መስፍን ይቅርታ እንዲጠይቁና የአንድነት ፓርቲ ‘ተራ አባል’ ሆነው እንዲቀጥሉ ሃሳብ መቅረቡ ታወቀ

የእነ ፕሮፌሰር መስፍን ቡድን በዚህ ሳይወሰን “የፓርቲው ህጋዊ ባለቤቶች እኛ ስለሆንን የፓርቲውን ንብረትና ጽ/ቤት አስረክቡን” የሚል አታካሮ በመፍጠር በፓርቲው ላይ የተጋረጠውን አደጋ ወደተወሳሰበና ደም አፋሳሽ ሁኔታ ያሸጋገረው መሆኑም ይታወሳል።በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የተቀሰቀሰው ሁኔታ በዚህ ደረጃ ላይ እንዳለ ወ/ሪት ብርቱካን ከእስር በመፈታታቸው የሁለቱ ባላንጣ ቡድኖች አመራር አባላት በወ/ሪት ብርቱካን መኖሪያ ቤት በድንገት በተገናኙበት ወቅት ሰላምታ ከመለዋወጥ … [Read more...]

ግልጽ ደብዳቤ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ የአማርኛው ፕሮግራም

አቶ ታደሰ እንግዳ ያስተላለፉት ይህ የሀሰት ዘገባ ከአንድ ጋዜጠኛ ነኝ ብሎ ከሚያምንና የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ወኪል ከሆነ ሰው የማይጠበቅ ተግባር መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ አቶ ታደሰ በጉዳዩ ላይ የኢዴፓን አቋም ማወቅና መዘገብ ቢፈልጉ ኖሮ ወደ ፓርቲው ቢሮ መሄድ እንኳን ሳያስፈልጋቸው አመራር አባላቱን በቀላሉ በስልክ ማነጋገር በቻሉ ነበር፡፡ ግለሰቡ ሌላ ምክንያት ባይኖራቸው ኖሮ ጀርመን አገር የሚገኙ የጣቢያችሁ ጋዜጠኞችም ሆኑ አዲስ አበባ የሚገኙት ሌላው … [Read more...]

የዋጋ ተመኑ የህዝቡን የኑሮ ውድነት በዘላቂነት ለመፍታት በቂ መፍትሄ አይደለም!

ችግሩ አሁን በደረሰበት ደረጃ አሣሣቢ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ከመሆን አልፎ ፖለቲካዊ ችግር ወደመሆን እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡ ይህም ስርአቱ የሚያራምደው አጠቃላይ የኢኮኖሚ አቅጣጫና እስትራቴጂ በብዙ ስህተቶች ድክመቶች የተሞላ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡ ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ … [Read more...]

ሚኒስቴሩ የዋጋ ቁጥጥር የሚደረግባቸው መሠረታዊ የንግድ ዕቃዎች የጅምላና የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ አወጣ

በመሆኑም ከጥር 9 ቀን 2003 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የጅምላ መሸጫ ዋጋና የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከለሳ ተደርጎባቸዋል።በዚሁ መሠረት አንደኛ ደረጃ ስንዴ ዱቄት ባለ50 ኪሎ ግራም ጅምላ 363ብር 65ሣንቲም፣ በችርቻሮ 378ብር 20 ሣንቲም፣ባለ 25 ኪሎ ግራም በጅምላ 183 ብር፣በችርቻሮ 190 ከ25 ሣንቲም፣ባለ 10 ኪሎ ግራም በጅምላ 74 ብር ከ40 ሣንቲም፣ በችርቻሮ 77 ብር ሲሆን፣ ባለ አምስት ኪሎ ግራም በጅምላ 38 ብር፣በችርቻሮ 39 ብር ከ45 ሣንቲም እንዲሸጥ … [Read more...]