ከሳምንቱ የጋዜጦች ዘገባ

ቅዳሜ ታህሳስ 30 ቀን 2003 ዓ.ም የወጣው ሳምታዊው አዲስ አድማስ ጋዜጣ በፊት ለፊት ገጹ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነጋዴዎችን አስጠነቀቁ” በሚል ርእስ ሰፊ ዘገባ አቅርቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለፈው ሀሙስ እለት በአዲስ አበባ ነዋሪ ከሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር ባደረጉት ስብሰባ፣ ከውጪ ሀገር በሚገቡ ሸቀጦች ላይ መንግስት የዋጋ ተመን ያወጣ መሆኑንና ነጋዴዎች ለተፈጻሚነቱ የማይተባበሩ ከሆነ በዘርፉ የውጪ ሀገር ባለሀብቶች እንዲሳተፉ የሚያደርግ እርምጃ … [Read more...]

የመኢአድ አመራሮች ተደባደቡ፤ ፓርቲው የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

በሁኔታው የተበሳጩት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል “ጠቅላላ ጉባዔ በሰጠኝ ስልጣን መሰረት ማስጠንቀቂያ መጻፍ ብቻ ሳይሆን ማገድም እችላለሁ” የሚል መልስ መስጠታቸውንና ከአቶ ማሙሸት አማረ ጋር እዚያው መድረክ ላይ ረዘም ያለ ውዝግብና የቃላት ምልልስ ማድረጋቸውም ታውቋል።ስብሰባው እየተካሄደ ባለበት ወቅት አቶ ማሙሸት አማረ ያደራጇቸው ወጣቶች አዳራሹ በር ላይ ሆነው “ኢ/ር ኃይሉ ወያኔ፣ ያዕቆብ ወያኔ” በማለት ዘለፋ ያቀርቡ እንደነበር የዓይን ምስክሮችን ዋቢ አድርጌአለሁ ያለው ኢትዮ … [Read more...]

በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሊበራል ዴሞክራሲ አዋጭነት

የፓርቲው አባላት በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ባደረጉት ጥልቅ ውይይት - የሊበራል ዴሞክራሲ ታሪካዊ አመጣጥንና በአሁኑ ወቅት የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ፤ ሊበራል ዴሞክራሲ ከሌሎች ርዕዮተ አለማዊ አቅጣጫዎች ጋር ሲነጻጸር ዘላቂ ሰላምን ከማምጣት፣ ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ከማጠናከር፣ ማህበራዊ ችግሮችን ከማቃለል፣ የመቻቻል ፖለቲካን ከማስፈን፣በእውነተኛ የነፃ-ገበያ ስርአት አማካኝነት ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን ከማምጣትና የግልን የቡድን መብቶችን በተሞላ ሁኔታ ከማክበር አንፃር … [Read more...]

ከጋዜጦች ዘገባ በጥቂቱ

በግንቦት ወር 2002 ዓ.ም በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ከቦንጋ ወረዳ አሸንፈው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው የተመረጡት የግል ተወዳዳሪው ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የእስከ አሁኑ የፓርላማ ቆይታቸው እንደተመቻቸው ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ በሰጡት ሰፊ ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።“አሁን ያለው ፓርላማ አስቀድሞ ከነበሩት በብዙ ለውጥና መሻሻል በዳበረ ደረጃ ላይ ነው። እንደ ዱሮው ሰዓት ሳይገደብ፣ … [Read more...]

“የጥቁር እና ነጭ” ፖለቲካችን ጀንበር ማዘቅዘቅና የሶስተኛ አማራጭ መጠንሰስ

በምክክር መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ዋነኛ ጠንካራ ጎን ተደርጎ የተወሰደው ከገዢው ፓርቲ በተጨማሪ ለሀገሪቱ አማራጭ የፖለቲካ ኃይል እንደሚያስፈልግ ግንዛቤ በመውሰድ ተደራጅተው የፖለቲካ ፓርቲ (ድርጅት) ማቋቋማቸው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የታየው ጠንካራ ጎን ደግሞ በነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች ዙሪያ የተሰበሰቡት ዜጎች በርካታዎቹ የሀገር ፍቅር ስሜት ያላቸው መሆናቸው ነው።እነዚህ “ሀገር ወዳድ” (Nationalist) ፖለቲከኞች ጠመንጃም፣ ወታደርም፣ ደህንነትም፣ … [Read more...]

ከሳምንቱ የጋዜጦች ዘገባ በጥቂቱ

የሺጥላ አክሊሉ፤ዓርብ ዕለት የታተመው ነጋድራስ ጋዜጣ “የደርጎች የይቅርታና የብሔራዊ እርቅ አጀንዳ” በሚል ርእስ የታዋቂ ግለሰቦችንና የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን አስተያየት አስነብቧል። በዚሁ ጋዜጣ ላይ የሺጥላ አክሊሉ የተባሉ ግለሰብ “ኮሎኔል ዳንኤልና ዶ/ር ሰናይ ልኬ ውስጥ ውስጡን የመቦርቦር ስራ ይሰሩ ነበር። አብዮታዊ ሰደድ የወዝ ሊግ ወታደራዊ ክንፍ ሆኖ ሰርቷል። እነ ጄኔራል ተፈሪ በንቲ ላይ እርምጃ የወሰዱት ወዝ ሊጎች ናቸው። እነሱ ደግሞ ባልጠበቁት ሁኔታ ተመቱ…” … [Read more...]

ኢ/ር ኃይሉ የመኢአድ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ታወቀ

ሲሉ የነበሩት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል አሁንም የመኢአድ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን የሪፖርተራችን ዘገባ አመልክቷል። ቀደም ሲል የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ያዕቆብ ልኬ ደግሞ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ተመርጠዋል ተብሏል።ቀደም ሲል የመኢአድ ዋና ፀሐፊ የነበሩት ወ/ሮ መሶበወርቅ ቅጣው፣ አንዳንድ የማእከላዊ ኮሚቴና ሌሎች ተራ አባላት በዚህ የመኢአድ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የኢትዮ-ፋክት ሪፖርተር የትናንትናውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን … [Read more...]

“የነጭና ጥቁር” ፖለቲካችን እንክርዳድ ሲበጠር!

“ሕዝብ” ለሚለው ቃል ወይም ጽንሰ ሃሳብ ሁሉንም ፖለቲከኞች የሚያስማማ አንድ ዓይነትና ወጥ ትርጓሜ ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው። በእኛ ሀገር ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ሀገሮች (ባደጉ ሀገሮች ጭምር) ያሉ ፖለቲከኞች “ሕዝቡ ጠልቷል፣ ህዝቡ መርጧል፣ ሕዝቡ እንዲህ ብሏል፣ ሕዝቡ… ህዝቡ…” እያሉ መናገር የተለመደ ነው። ሁሉም የፖለቲካ መሪዎችና ፖለቲከኞች በዙሪያቸው ተሰባስበው ድጋፋቸውን የሚገልጹላቸውን ሰዎች “ሕዝብ” እያሉ መጥራትን ያዘወትራሉ። ይህ ዓይነቱ ድርጊት ‘የያዝኩት … [Read more...]

ኢዴፓ መንግስት ነዳጅን እንዲደጉም መግለጫ አወጣ

መንግስት እንዲህ ዓይነት ተራ ትንታኔ እያቀረበ በመዘናጋቱ በአገሪቱ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣት ዛሬ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ኢዴፓ በመግለጫው ላይ አስታውቋል። አያይዞም፤ “መንግስት ይህንን በአገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚም ሆነ በህዝቡ የእለት ከእለት ኑሮ ላይ ከፍተኛ አደጋ እያስከተለ የሚገኘውን ችግር ለማቃለል የሚያስችል እርምጃ ይወስዳል ተብሎ በሚጠበቅበት በአሁኑ ወቅት በነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ሊባል የሚችል የዋጋ ጭማሪ” ማድረጉ ተገቢ … [Read more...]

እንጅነር ኃይሉ ሻውል ስልጣን አስረክባለሁ ማለታቸው ታወቀ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለፉት ሃያ ዓመታት ባላቸው ተሳትፎ በአንጋፋነታቸው የሚታወቁት የፖለቲካ መሪዎች ስልጣን የመልቀቃቸው ዜና ሰሞኑን እየተደጋገመ መምጣቱንና ከሁለት ሳምታት በፊት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከኦፌዴን ሊቀ መንበርነት መልቀቃቸውን የዜና ምንጩ ከአዲስ አበባ የላከልን ዜና አስታውሶ፣ በመጪዎቹ ሳምንታት ከኢ/ር ኃይሉ ሻውል ሌላ አቶ ልደቱ አያሌው የኢዴፓን የፕሬዝዳንትነት ስልጣን ለሌላ ሰው እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል ብሏል።“የፖለቲካ መሪዎች በየፓርቲያቸው ውስጥ … [Read more...]