ኢዴፓ ከሚያወጣቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች ጋር በተያያዘ የመንግስት ሚዲያዎች የሚያወጡትን የተዛባ ዜና አወገዘ

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የአዲስ አበባ – ኦሮሚያ የተቀናጀ ማስተር ፕላንን ተከትሎ ከተቀሰቀሰው ተቃውሞና በቅርቡ ደግሞ የወልቃይት – ጠገዴን ህዝብ የማንነት ጥያቄን ተከትሎ እስከተፈጠረው ከፍተኛ ቀውስ ድረስ ጉዳዩችን እየተከታተለ መግለጫዎችን ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በሰጣቸው መግለጫዎችም ፓርቲያችን በዚህ ግጭትና ተቃውሞ የሃገሪቱ ቀውስ ተባብሶ እንደ ሃገርም እንደ ህዝብም ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ከመክፈላችን በፊት መንግስት፣ ህዝቡ፣ የመገናኛ ብዙሃንና … [Read more...]

የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች

በሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ተንሳኤ ከሃያ አምስት ዓመት ኢህአዴግ የደርግን መንግስት በጦርነት አሸንፎ የሀገራችንን ፖለቲካዊ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ ቀስ በቀስ እያደጉ የመጡ ፖለቲካዊ ችግሮች በግልፅ ጎልተው መታየት ጀምረዋል፡፡ አሁን ገዥው ፖርቲና ፖርቲው የሚመራው መንግስትም የችግሮቹን መኖር አምኖ ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ መንገር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ ሁኔታ ለማንኛውም የሀገሩን ደህንነትና ሰላም፤ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ማህበራዊ ብልፅግና፤ … [Read more...]

መጪው ምርጫ “ሠርገኛ መጣ…” እንዳይሆን

(ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የፓርላማ አባል) (ይህ ጽሑፍ በቅጽ 1፣ ቁጥር 01፣ ጥቅምት 22 ቀን 2007 ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣው፣ ቢንያም ከበደ በሚያዘጋጀውና እኔም ጭምር በዓምደኛነት በምሳተፍበት “ኅብረ-ብዕር” መጽሔት ላይ ታትሟል፡፡ መጽሔቱን የማያገኙ፣ በተለይም በውጭ ሀገር ያሉ ዜጎች ሁሉ ቢያነቡት ‘ይጠቅማል፤ ለመወያያም መነሻ ሊሆን ይችላል’ በሚል መንፈስ በዚህ ድረ-ገጽ በኩል እንዲታተም ተልኳል፡፡) መንደርደሪያ በዓለም ላይ የዴሞክራሲ ስርዓት … [Read more...]

ከቡር ፕሬዚዳንት ይቅር ብለናል ግን…

(ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የፓርላማ አባል) (ይህ ጽሑፍ በቅጽ 13 ቁጥር 772፣ ጥቅምት 22 ቀን 2007 ዓ.ም በወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ታትሟል፡፡ ጋዜጣውን የማያገኙ ቢያነቡት ይጠቅማል በሚል መንፈስ በዚህ ድረ-ገጽ በኩል እንዲቀርብ ተልኳል፡፡) የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ንግግር በማድረግ የዓመቱን የሕግ አወጣጥ መርሐ-ግብር (Legislative Program) ማሳወቃቸው … [Read more...]

“መሬት ለአራሹ” – ለኢትዮጵያ የዳቦ ቅርጫትነት ትንሳዔ!

(ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የፓርላማ አባል) Email: ahayder2000@gmail.com (ይህ ጽሑፍ ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2006 ዓ.ም በወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ታትሟል፡፡ ጋዜጣውን ያላገኙ ሰዎች ቢያነቡት ይጠቅማል፣ መወያያም ይሆናል በሚል መንፈስ በዚህ ድረ-ገጽ ላይ እንዲታተም ተልኳል) በአዲስ አበባ ከተማ፣ በምኖርበት አያት - መሪ አካባቢ አንዲት አነስተኛ ባህላዊ ገበያ አለች፡፡ የአካባቢው አርሶ አደሮች በየሳምንቱ ረቡዕ እና ቅዳሜ ወደዚች ገበያ … [Read more...]

20 ዓመት ሙሉ ውህደትና ጥምረት ያልሰመረለት የተቃዋሚ ጎራ

አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) እና የመላው ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ውህደት ይፈፅማሉ ተብሎ ሲጠበቅ መኢአድ ለአንድነት በፃፈው ደብዳቤ፣ ውህደቱ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን አስታውቋል፡፡ በመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መኃሪ ፊርማ የወጣው ደብዳቤ፣ የፕሮግራምና የደንብ ጉዳይ፣ የስያሜ፣ የኃላፊነት፣ አንድነት ከመድረክ ጋር ስላለው ግንኙነት እንዲሁም የንብረት ጉዳዮችን በተመለከተ ተጨማሪ ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ … [Read more...]

ይድረስ ለፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

ሟቾችም እኛው፣ ገዳዮችም እኛው፣ መስካሪዎች እኛው፣ ፈራጆችም እኛው - ማን ይቅርታ ይጠይቅ? (ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የፓርላማ አባል) Email: ahayder2000@gmail.com ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ የተባሉ “ምሁር” ባለፈው ሰሞን “እርቅና ሰላም፤ የህይወት ቅመም” በሚል ርዕስ በተለያዩ ድረ-ገፆች ያሰራጩት መዘዘኛ ጽሑፍ ነው፡፡ የፕሮፌሰሩ የጽሑፍ ርእስ አሳሳች ነው፡፡ “እርቅና ሰላም፤ የህይወት ቅመም” የሚለውን ርእስ ከስሩ … [Read more...]

ኢዴፓ በሀረር ከተሰተው የእሳት አደጋ ጋር በተያያዘ መግለጫ አወጣ

የመግለጫው ይዘት እንደሚከተለው ነው - በሐረር ከተማ የተፈጠረው ችግር አስቸኳይ መፍትሄ ያሻዋል! የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም ምሽት ሁለት ሰዓት አካባቢ በሐረር ከተማ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ተከስቷል፡፡ ከዚህ በፊትም በዚሁ አካባቢ ተደጋጋሚ የእሳት ቃጠሎዎች መከሰታቸው ይታወሳል፡፡ ችግሩ እንደተከሰተ መንግሥት ድርጊቱን የፈፀመውን አካል ለማወቅ የማጣራትና ህብረተሰቡን የማረጋጋት ሥራ መሥራት ሲገባው በተመሳሳይ ቀን በተቻኮለ ሁኔታ ግሬደር አቅርቦ አካባቢውን ማፅዳት … [Read more...]

“ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል”

ከፍቅሩ አየለ በላይ ይህ ጽሑፍ ዛሬ በታተመው 9ኛ ዓመት፣ ቁጥር 442፣ ሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ታትሟል፡፡ ጋዜጣውን የማያገኙ፣ በተለይም በውጭ ሀገር ያሉ ዜጎች ሁሉ ቢያነቡት ‘ይጠቅማል’ በሚል መንፈስ በዚህ ድረ-ገጽ በኩል እንዲታተም ተልኳል) ሰንደቅ ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት እትሟ ትኩረት ከሰጠቻቸው ጉዳዮች አንዱ የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን “ተናግረውታል” የተባለውን ንግግርና ያስከተለውን ውዝግብ በተመለከተ ነው፡፡ በጋዜጣው ላይ ከቀረበው … [Read more...]

የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ!

(ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የፓርላማ አባል) Email: ahayder2000@gmail.com በፋክት መጽሔት ቁጥር 29 እትም ላይ “አስተያየት በሦስት ጉዳዮች ላይ” በሚል ርእስ አንድ ጽሁፍ አቅርቤ ነበር፡፡ አበበ አካሉ ክብረት የተባሉ ግለሰብ ለዚያ ጽሑፌ በዚያው በፋክት መጽሔት ቁጥር 31 እትም ላይ መልስ ሰጥተው ነበር፡፡ እኔም የመልስ መልስ አዘጋጅቼ ለመጽሔቱ ዝግጅት ክፍል በኢሜይል ልኬ ነበር፡፡ መድረሱንም አረጋግጫለሁ፡፡ ይሁን እንጂ የመጽሔቱ ዝግጅት ክፍል … [Read more...]