የጥቁርና ነጭ ፖለቲካችን መክሰምና የሶስተኛ አማራጭ መሰረት መጣል

ኢዴፓን በመመስረቱ ሂደት ተሳትፎ የነበራቸው “የ3ኛ አማራጭ ጠንሳሾች” በተቃዋሚው ጎራ ውስጥ ጎላ ጎላ ብለው የሚስተዋሉ ችግሮችን በዝርዝር አቅርበው ከተወያዩ በኋላ “ለእነዚህ ችግሮች መፍትሄው ምንድን ነው? ምንስ መደረግ አለበት?” የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት የመፍትሔ ሃሳቦችንም አስቀምጠዋል፡፡ መደረግ የሚገባውን አቅጣጫም ለማመላከት ጥረት አድርገዋል፡፡ ከመፍትሄ ሃሳቦቹ መካከልም የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው። እነሱም፡-•    የፍረጃ ፖለቲካን በተመለከተ፣ በሀገሪቱ ለዘመናት … [Read more...]

“የጥቁር እና ነጭ” ፖለቲካችን ጀንበር ማዘቅዘቅና የሶስተኛ አማራጭ መጠንሰስ

በምክክር መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ዋነኛ ጠንካራ ጎን ተደርጎ የተወሰደው ከገዢው ፓርቲ በተጨማሪ ለሀገሪቱ አማራጭ የፖለቲካ ኃይል እንደሚያስፈልግ ግንዛቤ በመውሰድ ተደራጅተው የፖለቲካ ፓርቲ (ድርጅት) ማቋቋማቸው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የታየው ጠንካራ ጎን ደግሞ በነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች ዙሪያ የተሰበሰቡት ዜጎች በርካታዎቹ የሀገር ፍቅር ስሜት ያላቸው መሆናቸው ነው።እነዚህ “ሀገር ወዳድ” (Nationalist) ፖለቲከኞች ጠመንጃም፣ ወታደርም፣ ደህንነትም፣ … [Read more...]

“የነጭና ጥቁር” ፖለቲካችን እንክርዳድ ሲበጠር!

“ሕዝብ” ለሚለው ቃል ወይም ጽንሰ ሃሳብ ሁሉንም ፖለቲከኞች የሚያስማማ አንድ ዓይነትና ወጥ ትርጓሜ ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው። በእኛ ሀገር ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ሀገሮች (ባደጉ ሀገሮች ጭምር) ያሉ ፖለቲከኞች “ሕዝቡ ጠልቷል፣ ህዝቡ መርጧል፣ ሕዝቡ እንዲህ ብሏል፣ ሕዝቡ… ህዝቡ…” እያሉ መናገር የተለመደ ነው። ሁሉም የፖለቲካ መሪዎችና ፖለቲከኞች በዙሪያቸው ተሰባስበው ድጋፋቸውን የሚገልጹላቸውን ሰዎች “ሕዝብ” እያሉ መጥራትን ያዘወትራሉ። ይህ ዓይነቱ ድርጊት ‘የያዝኩት … [Read more...]

“የነጭና ጥቁር” ፖለቲካችን ስንክሳር ሲበራይ!

በበኩሌ ይህንን ተከታታይ መጣጥፍ ለማቅረብ የተነሳሁት እንደ ገደል ማሚቶ ራሴ ጩኸት አሰምቼ፣ የራሴን ጩኸት በማዳመጥ ልቤን በሀሴት ለመሙላት ሳይሆን፤ የአንባቢን ስሜት ኮርኩሬ ወደ ውይይት መድረክ ለመሳብ በመሆኑ በቀጣይ ጊዜአት የውይይት ሃሳቦችን የያዙ ሰፋፊ አስተያየቶች እንደሚቀርቡ ተስፋ በማድረግ ወደ ዛሬው ርዕሰ ጉዳይ ላምራ!ለመጀመር ያህል፣ በክፍል አንድ መጣጥፌ መንደርደሪያ ላይ በጥያቄ ምልክት ቋጥሬ ያስቀመጥኩትን ጥያቄ ደግሜ ላንሳ። “እኛ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች … [Read more...]

ሦስተኛ አማራጭ የሌለው “የጥቁርና ነጭ” ፖለቲካችን አባዜ

የሀገራችን ፖለቲካ እጅግ በጎላ መልኩ ጥዋት ማታ ይወቀጣል፡፡ ይሰለቃል። ሲቻል በአደባባይ፣ ሳይቻል በየጓዳው እንደጉድ ይብጠለጠላል። በየመሸታ ቤቱ በወሬ ቱማታ ይበራያል፡፡ ይሁን እንጂ፣ የሚወራለትንና የሚመከርበትን ያህል ውጤቱ ያማረ አልሆነም። ባለመታደል ለፍሬ አልበቃም፡፡ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አላደገም። ድህነት አልጠፋም። (መጥፋት ቀርቶ አልተቀነሰም) የህዝቡ ሰላምና ደህንነት ከስጋት አልወጣም። ሰብአዊ መብት አልተጠበቀም። መልካም አስተዳደር አልሰፈነም። ከሀገሪቱ የድርቅና … [Read more...]