ለኢህአዴግ የቀረቡት ምርጫዎች የእባብ ወይስ የንስር ተሃድሶ?

በሙሼ ሰሙ ኢህአዴግ በ2007 ምርጫ መቶ ፐርሰንት ተመረጥኩ ባለ ማግስት መሬት አንቀጠጥቅጥ ሕዝባዊ ቁጣ እየናጠው ይገኛል፡፡ ህዝባዊ አመጹ በይዘቱም ሆነ በስፋቱ ታሪካዊ ሊባል የሚችል ገጽታን የተላበሰና በክልልና በጊዜ ያልተገደበ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ከዝቅተኛው የደህንነትና መለዮ ለባሽ ጀምሮ እስከ ከፍተኛው የመንግስት አካላት ድረስ ህዝባዊ ቁጣው እንዲቆም የተለያየ ማስፈራሪያና ዛቻ ቢቃጣም ህዝቡ ግን “ውሻዎቹ ይጮሃሉ ግመሎቹ ጉዟቸውን ቀጥለዋል” እንዳለ … [Read more...]

“ኢህአዴጎች” ሆይ ሁለቱን ሙሰኞች አሰራችሁ ዘጠና ዘጠኙ ሙሰኞች የታሉ?

ሙሼ ሰሙ (የኢዴፓ ፕሬዚደንት) (PDF) መንግስትና ኢህአዴግ አንድና ሁለት ባለስልጣናትን በመሰዋት ሙስናን በቁርጠኝነት እየታገሉ መሆኑን ለማስመስከር የሚሞክሩበት ዘመን ጀምበሩ እንዳዘቀዘቀ ግልጽ ሆኗል፡፡ ዛሬ ላይ ሕጻን አዋቂ ሳይል "እቺን ዓይነቷን ጨዋታ" ከዚህ ቀደም ተጫውተናታልና ጨዋታና ዜማ ለውጡ፤ ከዚህ ቀደም አንድ ጊዜ ተወናብደናል ሁለተኛ አትደግሙንም እያለ ነው፡፡ የሁላችንም ጥያቄ አንድ አይነት ነው፡፡ እስካሁን አንድ ሁለቱ ሙሰኞች ታስረዋል ቀሪዎቹ ዘጠና … [Read more...]

እውነትም “ያለበት” ይገንበት እንዳይሆን ?

ከሙሼ ሰሙ(የኢዴፓ ፕሬዚዳንት) “በዓለም ላይ ያሉ  ሃገሮች የራሳቸው መከላከያ ሰራዊት አላቸው፡፡ የኛ መከላከያ ሰራዊት ግን አልጄሪያ የሚባል የራሱ ሃገር አለው፡፡”    አዲስ አድማስ ጋዜጣ በዜና ዘገባው ላይ የመከላከያ ሳምንትን አስመልክቶ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋማችንን እንድንገልጽ እድል ሰጥቶን ነበር፡፡ በዚህ እድል ሃሳባቸውን ከገለጹት ተጋባዦች መካከል አንዱ እኔ ነኝ፡፡ ዜና ዘጋቢው ለአምዱ ስፋት ይመጥናል ባሉት ልክ ሃሳቤን ቀንጨብ አድርገው በማቅረባቸው … [Read more...]

Pages: 1 2

አማራጮች ያልቀረቡበት የዘንድሮ ምርጫ!

ከሙሼ ሰሙ ምርጫዎች ቀን ቆጥረው ይመጣሉ፤ ውጤቱን እንዲለውጡ ግን አንፈልግም” ሶሻሊስቶች ለህዝብ ጥቅም በሚል ሰበብ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚሹት በዲሞክራሲያዊ መንገድ አይደለም፡፡ በዚህም ሳቢያ ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ አይዋጥላቸውም፡፡ ተፈጥሯዊ ባህርያቸውም አይደለም፡፡ የእነሱ ዝነኛ ብሂል “የትም ፍጪው [ስልጣኑን] አምጭው” የሚል ነው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአገራችን በሚካሄዱ ምርጫዎች፣ ምርጫ ቦርድና አስፈጻሚዎቹ ለምርጫ ሕጎችና አሰራሮች አልፎ ተርፎም … [Read more...]

ዜጎችን አሳንሶ ራሱን ያገዘፈው “ልማታዊ መንግስት” (ከሙሼ ሰሙ)

በሌላ በኩል ደግሞ የሊብራል ዴሞክራሲ ፍልስፍና፤በዜጎች እኩልነትና ነጻነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሊብራል ዴሞክራሲ ዜጎች በፖለቲካውና በኢኮኖሚው ለሚኖራቸው አይተኬ ሚና ልዩ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ በዚህም ምክንያት ዜጎች በኢኮኖሚው ውስጥ በሚኖራቸው ተሳትፎ ልክ የሃገርን ኢኮኖሚያዊ አቅም ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ በማጎልበት የስራ እድል ፈጠራን በማስፋፋት፣ለሃገር ልማትና እድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በመንግስትም ሆነ በተቋማቱ እንዳይተካ ፍጹም የሆነ ከለላ ይሰጣል፡፡ … [Read more...]

ክቡር ሚኒስቴር በመልስዎ ውስጥ ያልነገሩን መልሶች

በርካታ የኢኮኖሚ ምሁራን እንደሚስማሙት ከሆነ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት ተመላሽን (Economic Return) ከግምት ውስጥ ያላስገባ፣ በኢንተርፕረነርሺፕ ላይ ያልተመሰረተና ቀጣይነቱ ያልተረጋገጠ፤ ሃገራዊ ሃብት በከፍተኛ ደረጃ በመንግስት ተጽእኖ ስር እንዲወድቅ በማድረግ የግል ኢኮኖሚ ዘርፉን ያቀጨጨና ያሰናከለ ከመሆኑም በላይ መንግስት የልማትም ሆነ የእድገቱ ብቸኛ አሳላጭ እንዲሆን አድርጓል፡፡ … [Read more...]

“የጅብ እርሻ ነገር ሳያድግ በቡቃያው”

በጊዜው ጉዳዩን ያለ አርምሞ በሳቅ በፈገግታ እንደዘበት አልፌዋለሁ፡፡ ስምንት ዓመት መሆኑ ነው እንግዲህ፣ በጊዜ ሂደት ግን አርሶ አደሮቹ ከገሃዱ ዓለም የተማሩት እውነታ ዛሬ ፍንትው ብሎ እየታየ ነው፡፡ ከኢህአዴግ ሃያ አንድ ዓመት የስልጣን ዘመን በኋላ፣ ዛሬም ስለኑሮ ውድነት፣ ስለትራንስፖርት ችግር፣ ስለመብት ጥሰትና ስለጋዜጠኞች መታፈን፤ በግዳጅ የኢህአዴግ አባል ስለመሆን፣ ስለአስከፊ ሙስናና በስልጣን መባለግ፣ ስለአስተዳደራዊ በደል፤ በአጠቃላይ ስለ ኢኮኖሚያዊና … [Read more...]

“ሕገ መንግስትና ምርጫ ‘እያነቡ እስክስታ’ ”

 ከዚህ ቀደም እንደታየው ሚዛናዊ የሆነ ውድድር ማድረግ ባለመቻሉ ምክንያት ውጥረት ውስጥ የወደቀው የመድብለ ፓርቲ ምርጫ ስርዓታችን በሂደት ፍጹም እንዳይዳፈንና በአንጻራዊነትም ቢሆን ሚዛናዊነቱን ሳይስት ከቅርጫ ወደ ምርጫነት እንዲሸጋገር በማሰብ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ባደረግነው ድርድር መሰረት በ2001 ዓ.ም በተረቀቀውና በጸደቀው የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ደንብ አንቀጽ “አርባ ሰባት” ንዑስ አንቀጽ “አንድ” ላይ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የገንዘብም ሆነ … [Read more...]

ለትምህርት ስርዓታችን ህልውና ከፖለቲካዊ ብልጠት ይልቅ ብልህነት ያሻል

 ለደርግ በወቅቱ የነበረው አጣዳፊ ጉዳይ አብዮቱ በመሆኑ በመማርና ማስተማር ላይ የነበሩትን መምህራንና ተማሪዎች በነቂስ አሰልፎ አብዮቱን ለማስተዋወቅ በሚል ሰበብ ወደ እድገት በሕብረት የዕውቅትና የስራ ዘመቻ አዘመተ፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ እራሱን በጥቂቱም ቢሆን ማጎልበት የጀመረው የትምህርት ስርዓት ከባድ ፈተና ውስጥ ወደቀ፡፡ ከየመንግስት መስርያ ቤቱና ተቋማቱ ሁሉም ዓይነት ባለሙያዎች በወረንጦ እየተለቀሙ የማስተማር ሂደቱን በግድ እንዲቀላቀሉ ተደረገ፡፡ እዚህ … [Read more...]

አል ኢስላሚያ ወርሃዊ መጽሔት ከአቶ ሙሼ ሰሙ የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (pdf) Source … [Read more...]