Logo

መጪው ምርጫ “ሠርገኛ መጣ…” እንዳይሆን

November 4, 2014

(ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የፓርላማ አባል)

(ይህ ጽሑፍ በቅጽ 1፣ ቁጥር 01፣ ጥቅምት 22 ቀን 2007 ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣው፣ ቢንያም ከበደ በሚያዘጋጀውና እኔም ጭምር በዓምደኛነት በምሳተፍበት “ኅብረ-ብዕር” መጽሔት ላይ ታትሟል፡፡ መጽሔቱን የማያገኙ፣ በተለይም በውጭ ሀገር ያሉ ዜጎች ሁሉ ቢያነቡት ‘ይጠቅማል፤ ለመወያያም መነሻ ሊሆን ይችላል’ በሚል መንፈስ በዚህ ድረ-ገጽ በኩል እንዲታተም ተልኳል፡፡)
መንደርደሪያ
በዓለም ላይ የዴሞክራሲ ስርዓት የመሰረቱ ሀገሮች ሕዝቦች የፖለቲካ መሪዎችንና የመንግሥት ባለስልጣናትን በኃላፊነት ቦታ ላይ ለማስቀመጥ (ለመሾም) ሙሉ በሙሉ የተቀበሉትና በተግባር የሚያውሉት አሰራር ቢኖር ምርጫ ነው፡፡ ይሁን እንጂ፤ በምርጫና በዴሞክራሲ መካከል ምንጊዜም የማይነጠል ግንኙነት አለ ብሎ ማሰብ ተገቢ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም፤ ተዘውታሪ ምርጫ (Periodic Election) በሚካሄድባው ሀገሮች የምርጫ ስርዓት ስላለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን ሆኗል ለማለት አይቻልምና ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፤ በሚያስተዳድሩት ሀገርና ሕዝብ ላይ አምባገነን፣ ዘረኛና ጨካኝ የአገዛዝ ስርዓት እንዳሰፈኑ ዓለም የሚያውቃቸው የፖለቲካ መሪዎችና ፓርቲዎች ጭምር ፀረ-ዴሞክራሲ ተግባራቸውንና የጎደፈ ስማቸውን ለመደበቅ ይረዳናል በሚል መንፈስ ጊዜ ጠብቀው የተጭበረበሩ ምርጫዎችን ሲያካሂዱ የሚታዩ እድሜ ጠገብ አምባገነኖች በዓለም ላይ ለዘመናት ሲታዩ ኖረዋል::

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Share