VOA – የዶ/ር መረራ እስር በተቃዋሚዎችና በገዥው ፓርቲ የተደረሰውን መግባባት የጣሰ ነው ሲል መድረክ ገለፀ
መሪው ዶ/ር መረራ ጉዲና በአስቸኳይ እንዲፈቱ እና መንግሥት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይትና ድርድር እንዲጀምር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ጥሪ አሰምቷል፡፡
ዶ/ር መረራ የታሠሩበትን ምክንያት ሰንካላ ሠበብ ነው ያለው መድረክ በተቃዋሚዎችና በገዥው ፓርቲ የተደረሰውን መግባባትን የጣሰ እንደሆነ በመግለፅ ከሷል፡፡
የዶ/ር መረራ መታሠር የሀገሪቱን ሠላምና መረጋጋትም አደጋ ውስጥ ሊከተው እንደሚችል ያለውን ስጋት መድረክ ገልጿል፡፡