Logo

በባቱ፣ሻሸመኔ እና አካባቢው የነበሩ ጥቃቶችን ተከትሎ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የተጠናቀረ ሪፖርት

Oromia atrocity
August 14, 2020

መግቢያ
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሌሊቱን እና በማግስቱ 23/10/12 የፀጥታ መደፍረስ ችግሮች ተከስተው በሰዎች ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡
ከኢትዮጵያ በጎ ፈቃደኛ ጋዜጠኞችና አርቲስቶች ሕብረት ጋር ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተርና ቡድናቸው በሐምሌ 27 እና 28 2012 ዓ.ም.በነበሩት ቀናት በባቱ እና ሻሸመኔ ከተሞች እና አካባቢ በተወሰነ መልኩ ተዘዋውረን የደረሰውን ጉዳት ለማየት ሙከራ አድርገናል፡፡
ባቱ ከተማ
አብነት ገለታው
እኛ አግኝተን ያናገርናችው ሶስት ወንድማማቾች ባቱ ከተማ ዘመድ ቤት ሀዘን ተቀምጠው ቢሆንም አምስት የቤተሰብ አባሎቻቸውን ማለትም አባታቸውን፡ እናታቸውን፡ ወንድም፣ እህታቸውን እና የአጎታቸውን ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ ያሳጣቸው ድርጊት ግን የተፈጸመው ከባቱ 7ኪ.ሜ ርቃ በምትገኘው አዳሚ ቱሉ ከተማ እንደነበር ነግረውናል፡፡
የሟቾች ስም ዝርዝር

  1. አቶ ገለታው አውላቸው   (አባት)  ዕድሜ 60
  2. ወ/ሮ ፀሀይ መንግስቴ      (እናት)  ዕድሜ 47
  3. ወጣት ሳሙኤል ገለታው   (ወንድም) ዕድሜ 24
  4. ወጣት ነፃነት ገለታው      (እህት) እድሜዋ 22
  5. ወጣት ዋሴ አግዜ                        (የአጎት ልጅ) እድሜ 21 ናቸው

ተጎጂዎቹ ጥቃቱ የደረሰባቸው በእምነታቸውና በማንነታቸው እንደሆነ የሚያምኑ ሲሆን ቤተሰቦቻቸውን ያጡት በድብቅ ሳይሆን ፖሊስ ባለበት ሀገር በቀን ቤታቸው ተሰብሮ ተገንጥሎ መስኮት በመሰባበር ገብተው በግፍ በአሰቃቂ ሁኔታ ቆራርጠው ነው የገደሏቸው ብለውናል፡፡

ሙሉውን ሪፖርት ለማንበብ ዚህ ይጫኑ

 

Share