በትግራይ ክልል ከተሞች ከተለጠፉ ማስታወቂያዎች 27 በመቶ ብቻ በትግርኛ ቋንቋ ተጽፈዋል
Source Walta Thursday, 29 January 2009 |
|
መቀሌ ጥር 21/2001/ዋኢማ/ በትግራይ ክልል ስድስት ከተሞች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ከተጻፉ የስም ማስታወቂያ ታፔላዎች ውስጥ 27 በመቶ ብቻ የትግርኛ ቋንቋ መሆናቸውን አንድ ጥናት አመለከተ ።
በመቀሌ ከተማ “ያልተስተካከለ የትግርኛ ቋንቋ አጠቃቀም” በሚል ርዕስ ዛሬ ለግማሽ ቀን በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በከተማው ንግድና ኢንዱስትሪ ፅሕፈት ቤት የአገር በቀል ባህላዊ ዕውቀት ጥናት ማስታወቂያ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ ብርሃኑ ወልደሚካኤል ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ ፤ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ከተጠኑ 1ሺ157 ማስታወቂያዎች ውስጥ 308 ማስታወቂያዎች ብቻ በትግርኛ ቋንቋ መጻፋቸው ተረጋግጧል።
አንዳንድ የንግድ ድርጅቶች ማስታወቂያቸውን ለምን በትግርኛ ቋንቋ እንዳልጻፉ ተጠይቀውም በማንኛውም ቋንቋ ቢጻፍ ምን ችግር አለው የሚል አስገራሚ መልስ ማግኘታቸውን አስረድተዋል ። ይህም የትግራይን ህዝብ በቋንቋው የመጻፍና የመግለጽ ህገ መንግሥታዊ መብቱን የሚጥስ በመሆኑ የቋንቋውን ደህንነት ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም መረባረብ እንደሚገባው አቶ ብርሃኑ ጠቁመዋል ። ከክልሉ መንግሥት፣ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ፣ከሚዲያዎችና ከሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት የተውጣጡ ተሳታፊዎች ቋንቋውን ለማጎልበት የሚቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል። |
It is a futile effort to force people to use a certain language.
TPLF if it has a brain should learn a lot from this.
So even in Tigray, TPLF could not rally the public around its divisive policy.
Divisive is our thought and the masked aim behind it- Not languages or administrative boundaries.