Logo

2 comments on “Ethiopian Democratic Party (EDP) denounces MEDREK

  1. የኢዴፓን መግለጫ አነበብኩት። ሁሉም ነገር ልክና መጠን አለው። እነ ገብሩ አስራት የኢህአዴግ ባለስልጣን በነበሩበት ወቅት ትግራይ ውስጥ አንድም ነፃ ፕሬስ አይገባም ነበር። ዛሬ እነሱ ከኢዴፓ በላይ የዴሞክራሲ ጠበቃ ሆነው ኢዴፓ በተገኘበት አልገኝም ማለት ያው የዱሮ አፋኝነታቸውን ከማረጋገጥ የዘለለ ትርጉም የለውም። እነ ስዬ፣ ዶ/ር ነጋሶ፣ ዶ/ር በየነ (የትምህርት ምክትል ሚኒስትር የነበሩ)፣ ኢ/ር ግዛቸው (የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክትል ኮሚሽነር የነበሩ ዋና ኮሚሽነር ካልሆንኩ ብለው የወጡ) ሁሉም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ነበሩ። እነሱ “ወያኔ” ያልተባሉ የኢዴፓ ልጆች ወያኔ የሚያስብላቸው አንድም መሰረታዊ ምክንያት የለም።

  2. የትውልዶች የአስተሳሰብ ልዩነት ሂደትን በጉልህ የሚያንፀባርቅ ነው እየተስተዋለ ያለው። በመድረክ ሥር የተሰባሰቡት በሙሉ ትናንት የሶሻሊስት/ኮሚኒስት ሥርዓትን ካልመሠረትን እያሉ በዚህ ወይም በዚያኛው ወገን ሆነው ሲጨፋጨፉና ሕዝብን ሲያስጨፈጨፉ የነበሩ ናቸው። አሁን ደግሞ ሌላ ርዕዮት አምጥተው የጎሳ ወኪሎች ነን ይላሉ። በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ያሉ ሽማግሌዎችም ሆኑ፤ ለኦሮሞ ወይም ለደቡብ ብሔረተኝነት ቆመናል የሚሉት እነ ነጋሦ፣ ቡልቻ፣ በየነና፣ መረራ ያሉት፤ ወይም የአረናዎቹ እነ ገብሩና ስየ በደርግም ሆነ በኢሕአዴግ ጊዜ በስልጣን ላይ ሆነው የዲሞክራሲና የአገር አንድነት ትግሉን ለማኮላሸት ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩ ናቸው። አሁንም መድረክ በሚል ስያሜ ኢዴፓን ለማግለል ያደረጉት ሙከራ ወደፊት ምን አይነት በጣም አደገኛ ድርጅት እየተሰባሰበ እንደሆነ በትክክል የሚያረጋግጥ ስለሆነ ምን ጊዜም ሃሳቡን በግልጽና በድፍረት ለሕዝብ በማቅረብ የሚታወቀው ኢዴፓ ጉዳዩን እንድንረዳው ማውጣቱ በጣም የሚያስመሰግነው ነው። ኢዴፓ ባለፉትም ሆነ በአሁኑ የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ በአንድ ወይም በሌላ መልክ በሥልጣን ተዘፍቆ የቆየ ሳይሆን ንፁሃንና የወደፊቱን አርቆ ተመልካቾች የሆኑ ወጣቶችን ያሰባሰበ ስለሆነ እውነትም መጪዋን ኢትዮጵያ የሚወክል ፓርቲ ነው። እነ ስየና ገብሩ ከወያኔ የተለየ አስተሳሰብ የላቸውም። በስጥ የስልጣን ሽኩቻ ስላልተስማሙ እንደወጡ ይታወቃል። ዶ/ር ነጋሦም በስልጣን ጥቅማ ጥቅሞች ተጣልቶ እንደወጣ እንጂ ሌላ አገራዊ የተለየ አመለካከት የለውም። ዶ/ር በየነም በመጨረሻው ያገሪቱ ፕሬዚደንት ለመሆን ያደረገውን ማመልከቻ ኢሕአዴግ ስላልተቀበለው እስካኮረፈበት ጊዜ ድረስ ብዙ የተለየ አገራዊ አጀንዳ እንዳልነበረው የታወቀ ነው። አሁንም የአስር ድርጅቶች ባለቤት ሆኖ እያምታታ የሚኖር ነው። ሰሞኑን የድጋፍ መደቤ ነው በሚለው በሃዋሳ ኢዴፓ ያን ያሕል ደማቅ ስብሰባና ከፍተኛ ድጋፍ ስላገኘ ፕሮፌሰሩ የሚይይዘውን የሚለቀውን ማየት ተስኖታል። የኢንዢነር ግዛቸውም ታሪክ ተመሳሳይ ነው። በመሰረቱ ግዛቸው እንኳን ለፖለቲካ መሪነት ለግል ጓደኝነትም ብቃት የሌለው ተራ አሉባልተኛ ለመሆኑ በጣም ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።

    አሁን እነዚሕ የአሮጌው አስተሳሰብ ወኪሎች የሆኑ እድሜ-ጠገቦች ኢዴፓ ላቀረበው ግልፅ ክርክር መልስ መስጠት የሚችሉ አይመስለኝም። ከእንግዲህ ውስጥ ውስጡን አሉባልታ እያዛመቱ መቀመጥ የለም። ኢዴፓ እንዳለፈው ጊዜ ሳይሆን ችግሮችን ወደ ሕዝቡ እያመጣ እንደዚህ ግልጽ ውይይት እንዲደረግበት ማድረጉን መቀጠል አለበት። ሕዝብ አሉባልታ ሰልችቶታል። የሰለጠነ ፖለቲካ ማለት ሃሳብን ፊት ለፊት በአደባባይ አውጥቶ መነጋገርና መከራከር ስለሆነ ኢደፓን መሞገት የሚፈልግ ጊዜው ያለፈበትን ሃሜት በጓዳ ከማሰራጨት በፊት ለፊት ከአመራሩ ጋር ክርክር በማድረግ ሕዝብን ለመስተማር ቢሞክር ይሻላል። የኢዴፓ መስመር ትክክለኛና ተቀባይነት ያለው ለመሆኑ በአዲስ አበባና በሃዋሳ የተካሄዱት ሕዝባዊ ስብሰባዎች ማረጋገጫዎች ስለሆኑ ኢዴፓዎች በልበ ሙሉነት ትግላቸውን ማጠናከር አለባቸው።

Comments are closed