Logo

ኢህአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተፈራረሙ

October 31, 2009

የአራቱ ፓርቲዎች ሊቀ መንበሮች ከፊርማው ስነ-ስርዓት በኋላ አጠር አጠር ያለ ንግግር አድርገዋል፡፡ በዚሁ መሰረት የመኢአድ ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ባደረጉት ንግግር፤ “… በድርድሩ ላይ ተካፋይ የነበሩ አባሎቻችን ድርድሩን ሲጀምሩ አይተዋወቁም ነበር፡፡ ሲጨርሱ ግን ወዳጆች ሆነዋል፡፡ በድርድሩ ሂደት ብዙ ተወያይተናል፣ ተዋውቀናልም፡፡ እናም ዛሬ የጎሪጥ መተያየት ቀርቶ ወዳጆች ሆነናል፡፡ ይህ ትልቅ እመርታ ነው፡፡ ከሰላማዊ ትግል ውጭ ሌላ አማራጭ አለ የሚል ካለ ተሳስቷል፡፡ …ዛሬ እኛ ይህንን ደንብ መፈራረማችንን አንዳንዶች እንዲህ ነው እንዲያ ነው እያሉ እንደሚያጣጥሉት እናውቃለን፡፡ ለህዝብ የሚበጀው ሰላም ነው፡፡ ከሰላም ውጭ ያለ ነገር አይጠቅምም፡፡ በዚያ ሂደት እኛም ነበርንበት፡፡ ያ ሁሉ ስህተት መሆኑን አይተን ተምረን ተመልሰናል፡፡ ችግሮቻችንን ሁሉ ተወያይተን መፍትሄ መስጠት አለብን፡፡ ሕዝቡም በሩን መዝጋት የለበትም፡፡ በተዘጋ በር ዴሞክራሲ አይገባም፡፡…” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አቶ ልደቱ በበኩላቸው፤ “ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘታቸው የተሰማኝን ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ የመኢአድ ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ሐይሉ እና የቅንጅት ፕሬዝዳንት አቶ አየለ ድርድሩ ውጤታማ እንዲሆን ለሰጡት አመራር ያለኝን ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ በድርድሩ ሂደት በርካታ አጨቃጫቂ ሁኔታዎች ገጥመውን ነበር፡፡ ነገር ግን ሁሉም ነገር በጋራ ስምምነት የተቋጨ በመሆኑ የድርድሩ ውጤት አንዱን የበላይ ሌላውን የበታች አላደረገም፡፡… በሀገራችን የኩርፊያ ፖለቲካ እየመሸበት ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ወራት ባደረግነው ድርድር የታየው የመቻቻል መንፈስ ከቀጠለ የዘንድሮው ምርጫ ብቻ ሳይሆን በመጪዎቹ ዓመታት የሚካሄዱ ምርጫዎች የግጭት ሳይሆን ሰላማዊ የተስፋ ምንጭ ይሆናሉ፡፡…” በማለት ገልጸዋል፡፡

የቅንጅት ፕሬዝዳንት አቶ አየለ ጫሚሶም እንዲሁ፤ “ድርድሩ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናከረ ነው፡፡ የተስማማንበትን ደንብ ሁላችንም ተግባራዊ ካደረግነው መጪው ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ይሆናል፡፡… ከድርድሩ ሂደት ራሳቸውን ያገለሉ አንዳንድ ፓርቲዎች ለሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ያላቸው ታማኝነት አጠራጣሪ ነው፡፡ ስለሆነም ያፈነገጡት ሁሉ ወደ ሰላማዊ ድርድሩ እንዲመለሱ ጥሪያችንን እናቀርባለን…” የሚል መልእክታቸውን አቅርበዋል፡፡

የመጨረሻው ተናጋሪ የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ በበኩላቸው ፓርቲዎቹ የተፈራረሙት ደንብ በመጪው ምርጫ ሰፊ የውድድር መድረክ እንደሚፈጥርና ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ መስፈርትን ባሟላ መልኩ ለመፈጸም እንደሚያስችል ገልጸዋል ሲል የዜና ምንጫችን አስታውቋል፡፡

Share

7 comments on “ኢህአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተፈራረሙ

  1. የመቻቻል ፖለቲካ ለሀገራችን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ስለሆነም ፓርቲዎቹ ሁለት ወራት ያህል ተደራድረው በመጨረሻም ከስምምነት ላይ መድረሳቸው በጣም ደስ የሚልና ተስፋ ሰጪም ነው፡፡

  2. ዶር (ጄኔራል) ብርሀኑን ግን ምንድነው እንደዚህ ያነጨረጨራቸው? አይናቸውን በማጉረጥረጥ’ መብረቅ የወረደ በሚመስል ድምፅ የቪኦኤው ሰለሞን ክፍሌን “የምን ምርጫ” ብለው ሲመልሱለት ጋዜጠኛውን ትንሽ ሳይስደነግጡት አልቀሩም፡፡

  3. Bravo and weldone! I hope the next election will be peaceful. Although I don’t expect a free and fair election, the agreement between the opposition parties and EPRDF is probably the beginning of our long march to true democracy and bright future.

  4. Weldone, it is possible to have tolerant, democratic and prosperous society. Dialogue is the only way. We have wasted 40 years in slogan mongering, posturing and cannibalising to each other. Keep it up!

  5. a great achievement for Meles and his cronies in hoodwinking the outside world with this brazen charade.But this farce will be exposed for what it is, a superfluous lie and pure propaganda.

  6. በአጭር ጊዜ እድሜው ሳያልፍበት ስልጣን ለመጨበጥ የሚፈልግ ሰው ካልሆነ በስተቀር የወደፊትዋን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚያልም ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት ይህንን ስምምነት በምንም መልኩ ሊቃወመው አይችልም፡፡ የ2002 ዓ.ም ምርጫ ዘላለማዊ ምርጫ አይደለም፡፡

  7. In a peaceful struggle, one can not shy away from dialogue. What matters most is the outcome not who sits with who or who handsakes with who.That is very trivial which should be placed in a history book soon.

    Thus, it is a right step forward.

Comments are closed