Logo

3 comments on “ድርድሩን አስመልክቶ ከመኢአድ የተሰጠ መግለጫ

  1. አይ ተቀዋሚ፡፡ ለራስ ስልጣን እያደላደሉ ህዝብን ለማስፈጀት የሚረዳ ስነምግባር ማርቀቅ፡፡ ዘንድሮም አልሞ ንፁህ ሰውን መግደል፡ በቁዋንቁዋ ተግባብቶ ፀጥታ የማየያስከብር ተኩዋሽ ማሰማራት ለተቀዋሚዎች የጠራ ስነምግባር ነው ማለት ነው! ሃሃሃሃ

  2. 8ቱ መስፍርቶች በየትኞቹ የስነምግባሩ አንቀጾች ነው የፈጻሙት፡ ደጋፊዎቻችሁ እንዳለፈው በጥይት እንደማይደበደቡ (አስግኘነው ብላችሁ በ (ለ) ስር የገለፃችሁት) በየትኛው አንቀፅላይ ነው ያስከበራችሁት፡ 35ቱም አንቀፅ እኮ ስለናንተ ደህንነት እንጂ በግልፅ ስለደጋፊዎቻችሁ አይናገሩም፡፡

  3. በባለፈው ምርጫም እንደዚሁ በደመ ነፍስ ተስማማን ብላችሁ (ቅሬታው ውጤት 2 ለ 1 -ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ ባንድ ገጎነን ሁለት ድምፅ ማለቴ ነው)ዳግም ምርጫውንና ቅሬታ ማሰማቱን የህግ ቀዳዳ አስፈጥራችሁ አስደበደባችሁን፡፡ እናንተ በፖለቲካ ወዳጅነት ኖራችሁ እኛ የማታ ዳቦ ያጠረብንን አስገደላችሁ፡፡ አሁንም የስነምግባር ህግ ማውጣት ጥሩ ሆኖ አወጣን ብላችሁ የምትፎክሩብንና የምታደነቁሩን ግን ያለፈውን የኢህዴግ የስነምግባር ግድፈት ያላገናዘበ፡ ሊመጣ የሚችለውን ችግር ግምት ውስጥ ያላስገባ፡ ግልፅነት የጎደለውና የተድበሰበሰ ለፓርቲዎች ደህንነት ብቻ የቆመ ነው፡፡ ይሔን ችግር በግልፅ የሚያሳይ ደንብ አውጥታችሁ፡ 8ቱ መስፈርቶች ተፈፀሙ፡ በደል አይደርስባችሁም፡ ባለፈው ስናጠፋ ኮርኮም ተደረግን፡… እያሉ እኛን ማጃጃልና በማይመስል መልኩ አፈ-ቀላጤ መሆን እኛን መናቅና ነገ ያሰባችሁትን የፖለቲካ ትርፍ ስታጡ ዘራፍ ለማለት ነውና አሁኑኑ ብታስቡበት መልካም ነው እላለሁ፡፡

Comments are closed