Logo

የዶ/ር ያዕቆብ የይቅርታ ጥያቄ መለወጥ፣ ጸጸት ወይስ ሴረኝነትና ወላዋይነት? (ከልደቱ አያሌው)

December 27, 2009

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Share

25 comments on “የዶ/ር ያዕቆብ የይቅርታ ጥያቄ መለወጥ፣ ጸጸት ወይስ ሴረኝነትና ወላዋይነት? (ከልደቱ አያሌው)

 1. ሶሰቱም ነው፡፡ ሴረኝነትም ወላዋይነትም ጸጸትም ይመስለኛል፡፡ ጸጸቱ ምናልባት “ኢዴፓን ባልለቅ ኖሮ” የሚል ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ “ቀስተደመና ከመግባት ወደ መኢአድ ጠጋ ብል ኖሮ” ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡

  በተረፈ የአቶ ልደቱ ምላሽ በጣም ተገቢና እንዲያውም ፓርቲው ከዚህ በፊት ይሰራው የነበረ ስህተትና ወደፊት ግን ማረም ያለበት ነገር ማለትም አሉባልታና የመሳሰሉት በጋዜጦች ወይም በህዝብ መገናኛ ላይ ሲወጡ ሳይዘገዩ በአፋጣኝ መልስ መስጠት ነው፡፡ እንደዚያ ሲሆን ነው የተሰራ አፍራሾችና አሉባልተኞች (በአጠቃላይ የአእምሮ ልክፍተኞች እላቸዋለሁ) ቦታ ቦታቸውን የሚይዙት፡፡

 2. የዶክቶር ያዕቆብ ነገር “ቀን ሰው መስሎ ማታ ጅራት አብቅሎ” አይነት ነገር ነው፡፡ ተለዋዋጭ ጠባይ ነው ያላቸው፡፡

 3. አይ ልደቱ፡

  ለምን መጀመሪያ ያንተን ስህተት ተናዘህ ይቅርታ አትጠ ይቅም፤ “በቤታችሁ ዋሉ” የመጀመሪያ የአመ ጽ ጥሪ መቅረት የለበትም፤ ህዝብን ለአመፅ አነሳስቶ የምን ወደሁዋላ ብለህ በወሬ ለገላጋይ ስታስቸግር፤ ፅፈት ቤቴ ዙሪያውን በወያኔ ተከቡዋል፣ ምናልባት ይሔ የመጨ ረሻ ድምጼ ይሆናል እያልክ በቪኦኤ ሰውን ስታስለቅስ፤ አሁን ደግሞ ከመንግስት በወቅቱ የአመጽ ሂደት የለሁበትም ብለህ ተለማምጠ ህ ተጠግተህ፣ ተቃዋሚዎች የፈለግነውን አጀንዳ ማስያዝ የመቻል እድል አለን እያልክ ታደነቁረናለህ፡፡ ደግነቱ ኢህአዲግና መቅላይ ሚኒስቴር ያንተን ጥቅምና ጉዳተ በጥንቃቄ የማስላትና የማወራረድ ችሎታቸው የመጠቀ ስለሆን ‹ቆይ ተው ገና ህጻን ነህ…› የሚሉበትና የሚያስደስቱን ጊዜ ይመጣል፡፡

  አቶ ልደቱ፣

  ጥሩ ተናጋሪና የመፃፍም ችሎታ ያለህ ሰው ነህ፣ ከምክር ቤት ውስጥ ምናልባት በዚህ ችሎታ ሁለተኛው ልትሆን ተችላለህ፡፡ አሁን የያዘከውም ሶስተኛ አማራጭ ለኔ እና ለኢትዮጵያ ቀሽት ይመስለኛል፡፡ ግን ግን ይሄ ሁሉ ጥሩ ጎን፣ ጀምሮ ዞር በሚልና ይቅርታን በሚ ጠ የፍ ልደቱ ላይ ሲለበስ ውጤ ቱ ስለሚታወቅ ያስጠ ላል፤ይደብራል፡፡

  አቶ ልደቱ፣ እስቲ አንተም ከደፈርክ ጥያቄዎች ልጠ ይቅህና መልስ፡

  1.እውን አድማ በመቀስቀስ ‹‹በቤታችሁ ዋሉ› የመጀመሪያ የአመ ጽ ጥሪ መቅረት የለበትም፤ ህዝብን ለአመፅ አነሳስቶ የምን ወደሁዋላ ብለህ”፣ ህዝብ ሆ ብሎ የደገፈውን ድርጅት ዶግ አመድ በማድረግ፣ በኢዴፓ ስብሰባ ላይ የውሸት እንባ በማነባት፣ በምክር ቤት ቆይታህ ቁልፍ የህዝብንና የኢህአዴግን ቁስል በአጀንዳ ባለማስያዝህ… ህዝብን ይቅርታ የሚያስጠይቅ በደልና የምታሻሻሽለው ህፀፅ የለብህም? እንደምትለው ፍጹም ቅዱስ ነህ?
  2.እንደምታውራው በወር አነዴ የፈለከውን አጀንዳ በፓርላማ ማስያዝ ከቻልክ፣ በፊት በምርጫ ጊዜ ታነሳቸው የነበሩ (እንደ ኢፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ‹ኢንተር ሀምዌ ያሰኘህን›፣ የወደብና የድንበር ጥያቄ (የኢትዮጵያ የኖረ ሉአላዊነት በህገ-መንግስት ችምር ቸል የተባለበትን)፣ የፓርቲ የንግድ ድርግቶች የተድበሰበሰ ኑሮን፣ የፍርድ ቤትና የማረሚያ ቤቶች ድክመትን)፣ የፖሊስ የስነምግባርና ችሎታ ማጣትን (ተራ ሌብነትና ሙስናን መከታተል ያለመቻል ግን በሆነ አጋጣሚ መንገድ ላይ ከፋኝ ብሎ የሚጮህ ዜጋን መግድል፣ በቆመጥ መቀጥቀጥ፣ እና በገፍ ለማሰር መትጋትን)፣ በተለይ ካድሬዎችና ሹማምንቶች የከተማ ቦታን በመቸርቸርና በማስቸርቸር ሲዘፈቁ በዚህ የምክር ቤት ቆይታህ አለማንሳትህ ቢያንስ የህሊና ተጠያቂ አያደርግህም? በሚቀጥለው ምርጫ እነዚህን ዋና ነገሮች ለመፎካከሪያ ማንሳቱና “እህአዴግን ውሃ ውሃ አሰኛለሁ” እያሉ መፎከሩ አያሳፍርህም? ለዚህም ነው “ጥሩ ቢሆንም ባንተ ላይ ሲለበስ ” ያስጠላል ያልኩት፡፡
  3.አሉባልታንና የመጠፋፋት ፖለቲካን ከጠላህ ከላይ ያነሳሁዋቸውን አንገብጋቢ አንትን የሚመለከቱ ጉዳዮች ቸል ብለህ ጊዜህን በአለፉና ባሉባልታ ማነፍንፍ ለምን ታጠፋለህ (ምሳሌ የዶ/ር ያቆብ ኢህአፓነት፣ ቤት ማግኘትን፣ ሰው ለቅንጅት መንፈስ ግንባሩን ለጥይት ስጥቱዋል፣ ቤት ተዘግቱዋል አንተ ስሜ ጠፋ እያልክ 5 ዓመት አጀንዳ ያዝክብን… )?

  ፍኖተ-ኢትዮጵያ

  ከአዲስ አበባ

 4. Dr Yacob is letting himself down by changing his account day after day absurdly. When i read his first article, i said tomyself Dr Yacob meant business.However,when i read his second article,i said to myself,as the old adage goes,old habis does not die easily.

 5. Let the revolutionary generation leave the political platform to the new and clean generation. We had had enough of the revolutionary generation.

 6. እኔም በዚህ ሰሞን ምነው ዶክተር ያቆብ ያለወትሮአቸው ቶሎ ቶሎ መጻፍ ጀመሩ፡፡ በዛ ላይ ተንበርክኬ ምናምን የሚለው ነገር ያልተለመደ ጸባይ ነው፡፡ በዚህ በሁለተኛው መጣጥፋቸው ላይ የጻፉት በአብዛኛው አሉሽ አሉሽና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ስንት በሺህ የሚቆጠር መመዘኛ ተፈትኖና ብዙ አመት የስራ ልምድ ካካበተ ግለሰብ የማይጠበቅ ነው፡፡

  እዚህ በውጭ አገር ውስጥ ፓልቶክ በሚባል መገናኛ እቤታቸው ውስጥ ተንዘርፍጠው ያንንም ይሄንንም ፍሬከርስኪ ሲያወሩ ውለው ሲያወሩ ከሚያመሹና በስሜት ከሚነዱ አንዳንድ ሰዎች ሰዎች እሳቸውን ለመለየት በጣም ተቸግሬአለሁ፡፡
  ኧረ ደ/ር ያቆብ አያምርቦትም!!

 7. Lidtu you are so human with ámazing capacity.
  Welsaid !!Articulated
  That is what yaekob deservs. There are live witness what he said when he was att kaliti. Yaekob is useless person .He was one of the fabricater of lie against you . ( feri, wolaway ,worada selehon yigebawal ).
  Please write it what you know . They are killers of our peaceful struggle.Why you are so human to them?Yaekob is useless

 8. Kibe yatetal melsu.ewnetm asa gorguari zendo yawetal!
  Maferya ”dr” bimot yishalewal.sayiteyikuy meleflef 10 sew sidewul yalewn mekad . Ai mihur bayimar biker .
  Yetureta gizewn besiltan lemasalef yaleme diros min aquam alew

 9. Dear Readers

  Please don’t be sensitive and partial. All of them (KINJIT LEADERS including Lidetu) have doing wrong and they are unfit for the generation. ALUBALTA is drived from former generation. Today is the generation who riches in information and negotiation.

  Other KINJIT leaders were already died leaving their spirit of true democracy and humanity for this generation. Some of the spirit is assimilated and practiced in EPRDF like MELKAM ASTEDADER and BPR with in this 5 year. However, Lidetu has doing nothing with in the parliament with in these years. If you support Lidetu, who is in between death and life, point at his weaknesses and let him admit them before going a step forward.

  I tried to list above in Amharic.

  Finot

 10. አቶ/ወ/ሮ/ወ/ሪት ፍኖተ ኢትዮጵያ የተባሉ ጸሐፊ የሰጡትን አስተያየት አነበብኩት። ጸሐፊው በውስጣቸው ያደረን ስሜት በሰለጠነ መንገድ በጽሁፍ ለመግለጽ መሞከራቸው የሚያስመሰግናቸው ነው። ይሁን እንጂ፣ የጽሁፉ ይዘት ሲበራይና ሲፈተሽ፤ ጸሐፊው ለአቶ ልደቱ ያላቸውን የመጠቀና የጠለቀ ጥላቻ ከማንጸባረቅ ውጭ አንድም ፍሬ ነገር አላገኘሁበትም። ለወደፊቱም ጥላቻንና በመረጃ ላይ ያልተመሰረተ ለአንድ ወገን ያጋደለ አካሁድን በማስቀረት በሰከነ መንፈስ ፍሬ ያለው ነገር በመጻፍ ልደቱን ብቻ ሳይሆን ጽሁፋቸውን የሚያነብን ሁሉ እንዲያስምሩ ይመከራሉ። ይህ ጥቅል አስተያየቴ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በጽሁፋቸው ላይ ላነሷቸው አንዳንድ የተሳሳቱ ስሜታዊ ሃሳቦች በኢዴፓ አባልነቴ ከማውቀው ሀቅ በመነሳት የሚከተለውን ምላሽ አቀርባለሁ።

  1.ጸሐፊው “ልደቱ በቅድሚያ አንተ ይቅርታ ጠይቅ” ያሉትን ሃሳብ በተመለከተ፤ በቅድሚያ ጥቅምት 16 ቀን 1998 ዓ.ም በተደረገ የቅንጅት ላዕላይ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በመገኘት ልደቱና ከኢዴፓ የተወከሉ 5 አባላት እየተሄደበት ያለው መንገድ ትክክል እንዳልሆነ አስረዱ። ጊዜው፣ እንደ ፍኖተ ያሉ (ማን እንደላካቸው የማይታወቁ) በስሜት የሚነዱ አባላትና ደጋፊዎች ‘እኛ አለንላችሁ’ እያሉ የሚደሰኩሩበት የውዥንብር ወቅት ስለነበር የእነ ልደቱን ሀሳብ የሚሰማ ልብ ጠፋና የሚሆነው ሆነ። እነ ልደቱ እንደጉድ ከሚከንፈው የቅንጅት ካሚዎን ላይ “በአርፋ” ወረዱና ለወሬ ነጋሪ ተረፉ። … ወደ ፓርቲያቸው ተመለሱ… የኢዴፓን ጉባዔ አደረጉና አመራራቸውን መረጡ። በጉባዔው ውሳኔ መሰረት ፓርላማ ገቡ። ከዚያ ለሦስት ሳምንታት ቁጭ አሉና የመጡበትን ሂደት ገመገሙ። ስህተታቸውን ነቅሰው አወጡ። የግምገማቸውን ውጤትም ለህዝብ ይፋ አድርገው “ትልቁ ስተታችን ቅንጅትን ከመሰረቱ ለወቅቱ የሚመጥን ዴሞክራሲ ያልገባቸው ኃይሎች ጋር አብረን እንሰራለን ብለን ጥምረት መፍጠራችን ነው” በማለት ይቅርታ ጠየቁ። እናም የኢዴፓ አባላት ከማንም በፊት ችግሮችን አፍረጥርጠው ካወጡ በኋላ ነው “3ኛ አማራጭ” የሚለውን የአሰራር መርህ አጉልተው በማውጣት እነ ዶ/ር ያዕቆብና ዶ/ር ብርሃኑ ከያሉበት ተጠራርተው መጥተው አፈር ከድቤ ያስጋጡትን ትግል እንደገና “ሀ” ብለው የጀመሩት፡፡ ስለሆነም ልደቱም ሆነ ኢዴፓ ይቅርታን አይጠየፉም የሚለውን ፍኖት ቢገነዘቡት መልካም ነው።

  2.ጸሐፊ ፍኖት ‘በቤታችሁ ዋሉ ብለህ ስትቀሰቅስ የነበርከው አንተ አልነበርክም ወይ?’ የሚል መንፈስ ያለው ሃሳብ አቅርበው አቶ ልደቱን ከሰዋል። “በቤታችሁ ዋሉም” ሆነ ሌላ የሰላማዊ አመጽ ጥሪ የተላለፈው በጥቅምት ወር 1998 ነው። ኢዴፓና ልደቱ ግን ነሀሴ 17 ቀን 1997 ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ውጤት በይፋ ከገለጸ በኋላ፤ የተገለጸው ውጤት ትክክለኛ አለመሆኑን ቢያውቁም ከዚያ ጊዜ በኋላ ምንም ዓይነት ህዝብ ቀስቃሽ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት ትክክል አለመሆኑን ተገንዝበው አቋም ይዘዋል። በዚያ የአመፅ መንገድ የሄዱትም ከእልቂት በስተቀር ምንም ዓይነት ተዓምር ሲፈጥሩ አልታየም። ስለሆንም፣ አቶ ልደቱም ሆነ ኢዴፓ ባላወጁት የአመጽ አዋጅ ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር ሊኖር አይችልም የሚለውን ፍኖት ቢገነዘቡት አሁንም መልካም ነው እላለሁ።

  3.ሌላው የጸሐፊው መልዕክት “ልደቱ በፓርላማ ጠቃሚ አጀንዳ አላቀረብክም” የሚል መንፈስ አለው። በመጀመሪያ ደረጃ ጸሐፊው የምረጡኝ ቅስቀሳ እና ፓርላማን ለይተው የሚያውቁ አልመሰለኝም። በምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት ፓርቲዎች ሕዝብን ከጎናቸው ለማሰለፍ አያሌ ስሜት ቀስቃሽ ሃሳቦችን በማቅረብ ‘እኔን ምረጡኝ’ ይላሉ። በዚህ የቅስቀሳ ወቅት አንዳንድ ጊዜ የሕዝብ ስሜት ከመለኪያ በላይ ይወጣና ለአደጋም የሚዳርግበት ሁኔታ ሰላለ ምርጫው እንደተጠናቀቀ ያን ስሜት ለማርገብና ለማቀዝቀዝ ጥረት ማድረግ ተገቢ ነው። ቅንጅት ያን ባለማድረጉና “የተደራጀ ኃይል አለ” እያለ ኃላፊነት በማይሰማው መልኩ የህዝብን ስሜት ይበልጥ በማባባሱ የደረሰውን ሁላችንም አይተናል። ፓርላማ እንደ ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሁሉን ነገር እንደፈለግን እያቀረብን የምንወራጭበትና የምንፏልልበት መድረክ አይደለም። ፓርላማ የተለያየ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበት ሥፍራ በመሆኑ ስራውን የሚያካሂድበት ደንብ፣ መመሪያ፣ ማንዋልና የአሰራር ስርዓት አለው። በአንዳንድ ሀገሮች (ለምሳሌ ህንድ) የፓርላማ አባላት የሚናገሯቸውና የማይናገሯቸው ቃላት ጭምር በደንብ ላይ በዝርዝር ይቀመጣሉ። ከዚያ ውጭ ምንም ነገር ማድረግ አይቻልም። በእኛም ሀገር ፓርላማ እንዲሁ ህግ አለ። ልደቱም ከዚያ ህግ ውጭ ምንም ነገር ማድረግ አይችልም። በፓርላማው ህግ ማቅረብ የሚፈቀደውን ግን ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተሻለ መልኩ እየተጠቀመበት ያለው ኢዴፓ ነው። ከዚህ በላይ በፓርላማ ያሉ የኢዴፓ አባላት ከአፈ-ጉባኤው ጋር ግብግብ ሊገጥሙ አይችሉም። ጸሀፊ ፍኖት የሚፈልጉት አቶ ልደቱ አቶ መለስን በፓርላማ እንዲወግሯቸው ከሆነ፣ ፍኖት በዘንድሮው ምርጫ ተወዳድረው ያሽንፉና ፓርላማ ገብተው ማድረግ የሚፈልጉትን ሁሉ ይሞክሩት። ኢዴፓ ግን አቶ ልደቱ ይህንን እንዲያደርጉ አላዘዛቸውም፣ አይፈቅድላውምም።

  4.ጸሀፊ ፍኖተ እላይ የጠቀሱትን እታች እየናዱ ሃሳባቸውን እርስ በርሱ በማዋቃት “የአዋቂ አጥፊ” ሆነው የታዩበትም ሁኔታ በዚሁ ጽሁፋቸው ላይ ይታያል። በጽሁፋቸው ተራ ቁጥር 2 ላይ አንዳንድ አጀንዳዎች ለምን በፓርላማው አልቀረቡም ብለው ከጠቃቀሱ በኋላ፣ ‘እነዚህን አጀንዳዎች በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት አቅርበህ ኢህአዴግን ውሃ ውሃ ለማሰኘት ነው ወይ?’ የሚል መንፈስ ያለው ሃሳብ በማቅረብ አቶ ልደቱን ለመሞገት ይዳዳቸዋል። ፍኖተ፤ “ምን መቼና የት” መቅረብ እንዳለበት ጠንቅቀው እያወቁ መልሰው ልደቱን ምንም አልሰራህም ብለው መክሰሳቸው ነው “የአዋቂ አጥፊ” እንድላቸው ያስገደደኝ። ለማንኛውም የምርጫ ቅስቀሳው በቅጡ ሲጀመር ሁሉንም ነገር ይደርሱበታልና እስከዚያው ይታገሱ!

  በመጨረሻ አንድ ነጥብ ለጨምርና ጽሁፌን ልቋጭ። ጸሀፊ ፍኖተም ሆኑ ሌላ ወገን እንዲገነዘብልን የምንሻው አንድ ጉዳይ አለ። አመናችሁም አላመናችሁ፣ ተቀበላችሁትም አልተቀበላችሁ፣ ወደዳችሁም ጠላችሁ፣ … ልደቱ (ከነ ድክመቶቹ) ከትውልዳችን “ጀግኖች” አንዱ ነው። በሀገሪቱ እያንዳንዱ ትውልድ የራሱ ጀግኖች ነበሩት። በተለምዶ ያየነው ግን የየትውልዱ ጀግኖች የሚሰማቸው እያጡ፣ ስሜታዊ በሆነ እርምጃ ሲመክኑ ነው። እኛ ግን ልደቱን የሚተካ ሌላ ጀግና ሳናዘጋጅ በስሜት ተነሳስተን አናዋርደውም፣ አናባርረውም ወይም አንገድለውም። ባይሆን ልደቱ ሰው ነውና ሲሳሳት እናርመዋለን፣ እንመክረዋለን። አቅጣጫ ሲስት እናስተካክለዋለን። በአሉባልታ ከማዋከብ ይልቅ ከጎኑ ሆነን እናርቀዋለን። ጊዜው ሲደርስ ደግሞ ከእርሱ በተሻለ ሌላ ጀግና ተክተን እሱን መርቀንና አመስግነን እንሸኘዋለን እንጂ ትንሽ ጥፋት በታየበት ቁጥር ለዘመናት የሰራውን በጎ ነገር ሁሉ በዜሮ አባዝተን በውርደት አናባርረውም። ተግባባን ፍኖተ – ኢቶብያ?
  ፍቅሩ አየለ በላይ፤ ከሸበል በረንታ

 11. Finot, We are educated using this internet technolgy. We should have to speak or write based on evidences or information. Therefore, what are your evidences that make you to say that “Lidetu is between life and death”? If you do not forwarded your substantive evidences, it is you who is “senstive and partial”. When you point one of your fingers, the other four are pointing to you.
  Timerga Mohamed Hagos

 12. Thank you Timerga
  EDP is the future. Lidetu is a wise and smart leadr wheather you like it or not he has the truth and he will winn all old dogs.you who wrote that Lidetu is between life and death you have to tell us that all others Mederk or udj are already dead if so . Visit EDPs web site and learn what Lidetu and EDP doing.

 13. ውድ ፍቅሩ እና ቲመርጋ፣

  በመጀመሪያ ጊዜ ሰጥታችሁ መልእክቴን ስላነበባችሁልኝና መልስ ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ፤ ስሜቴን የጎዳ የሀገር ጉዳይ በመሆኑና እነዳላችሁት በዘዴ በህይወት የተረፈ የቅንጅት ቁራጭ ኢዴፓና ልደቱ በመሆናቸው፡፡

  በመቀጠል፡

  1.ፍቅሩ የተለመደና የኖርነበትን ስህተት ባትደግም ደስ ይለኛል፤ ትልቅ ሃላፊነት ላይ ያለህ ሰው ስለመሰለከኝ ያነተ ስህተት ከኔ ከተራው ተማሪ የበለጠ ሁላችንንም ይጎዳልና፡፡ ለዚህ ስህተትህ ማስረጃዬ፤ በመጠቀና በጠለቀ መለኩ ፃፍከው ያልከኝንና በሌለህ ጊዜ ነጥሞና አንብበህ መልስ የሰጠህበትን ጉዳይ (ፍሬ የሌለው) ማለቱ ከራስህና ከስራህ ጋራ ያጣላሃል፡፡ወረድ ብለህ (ማን እንደላካቸው የማይታወቅ…) ያልከው ደግሞ ህዝብንማክበር፣ የሀገር ስሜትን መንከባከብ፣ በድርድርና በሶስተኛ አማርጭ በሰከነ መልኩ መመራትንና ከአሉባልታ መራቅ የሚለው የጠራ መርህህ ጋር ያጋጭህና ወደ እነ ዶር. ያእቆብ ጎራ (የኖርንበት የሁላችን ስህተት ነው) ገፍትሮ ይጥልሃል፡፡ በፓርላማ ወደብንና ፍትሃዊ የሃብት አጠቃቀምን የመሰሉ ባለፈው ምርጫ ስታነሱዋቸውና ህዝቡን ሆ ስታሰኙት የነበረ ወሳኝ ጉዳይ ፓርላማው ፈቀደልን ባላችሁት ህግ ልክ ባለማቅረባቸሁ ላነሳሁት ጥያቄ መሰል አስተያየት ከሰፈ ጉባኤው ጋር ግብ ግብ አንፈጥርም፤ መለስን አንወግርም… በሚሉ ቃላቶችህ (ገብተህ ሞክረው አይነት ሳፋጣ) መመለስህ አንተንም፣ ድርጅትህንም ጊዜው ደረሰበትን ደረጃም አይወክልም፡፡ አፈ-ጉባኤው ንና ከብር ሚኒስትሩን መውገርና ግብግብ መግጠም እንኩዋን ፓርላማው አብዛኛው ኢትዮጵያዊም አንፈቅደውምና፤ ክብራችንን ስለሚነካ፡፡ ልደቱን ሊሞግቱ ይዳዳቸዋል ላልከኝ ለምን ጥፋቱ ከሆነ አልሞግተው ብልህ ልቦናህ ትክክለኛውን መልስ አይሰጥህ ይሆን፤ በሃሳብ ለመሞጋገት መዳዳት እኮ የዘመኑ ምርጥ መግባባት መሆኑን አልተረዱም እንዴ፡ ስለዚህ አቶ ፍቅሩና መስል ችግር ያለብን ሁሉ፣ ብናስተካክለው አይነጅምን
  2.አሉባለታና መረጃ፣ በመረጃ የሚወራና ያለመረጃ የሚገመት ቁም ነገር፣ መልስ የሚሻ መቃሚ አሉባልታና ተንቆ የሚተው አሉባልታ፣ አሉባለታ እጠላለሁ በሚል አታካራ ቁም ነገርን መሸሽ መሳሰሉት ኢዴፓ (ልደቱን) ወጥረው የያዙ ችግሮች ይመስሉኛል፡፡ ፊት ለፊት መናገርና መፃፍ በማንችልበት፣ መረጃ ማግኘት ምጥ በሆነበት ሃገር መረጃ አልባ ብዙ ቁም ነገሮችን እነዳንፅፍ፣ እንዳናነብና እንዳንጠያየቅ ባታስገድዱን ጥሩ ነው፤ አማራጭ የለንምና፡፡ እናነት መረጃ ካላችሁና በመረጃ ብቻ የመስራት እድሉን ካገኛችሁ ስድብና ውግዘት ሳትቀላቅሉ ውሸታችንን በፍጥነት እርቃኑን ካስቀራችሁት የወቅቱ ጀግና ተሆናላችሁ፡፡ ለዚህ ማስለጃዬ ልደቱና ኢዴፓም እንደሌሎቹ ሁሉ ለህዝቡ ደበቁትን የመፈራረስና የማፈራረስ ሃቅ ካላወጣችሁ አወጣዋለሁ እያለን ሰንብቱዋል፡፡

 14. 3.እኔ እንደማነኛውም ከፓርቲ ውጪ እንደምኖር ኢተዮጵያዊ ተማሪ፣ ነሃሴ 17፣97 ኢዴፓ ተገልሎ ወጣ፣… እያልኩ በማጣያቀስ መከራከር አይጠበቅብኝም፤ ማጣቀስ አለመቻሌ ግን አያሸልመኘም፡፡ ግን ግን የህዝቡን ስሜት በድህረ-ምርጫ ሰማይ ካወጡትና ከምርጫ በሁዋላ ህዝቡ ህይወን እንዲሰጥ ካደረጉት ክስተቶች አንዱና ዋነኛው የልደቱ በድህረ-ምርጫ የሀገሪቱ ቁልፍ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው፣ ከምርቻ በሁዋላም በቢሮዬ በወያኔ ተከብቤያለሁ፣ ከአሁን በሁዋላ ላንገናኝ እንችላለን፣ የምን ህዝብን አነሳስቶ ወደ ሁዋላ ነው፣ የህወሃት የንግድ ድረጅቶች የትግራይ በጅት… ከሌሎቹ የበልጣል… (ምንጭ በወቅቱ የልደቱ ቃለ-ምልልስ በቪኦኤና ድህረ-ምርጫ-97 ቅስቀሳ) እና የመሳሰሉት ወነኞቹ እንደነበሩ ብናገር አሉባልታ እነደማይባል እንስማማለን፡፡ በኔ በኩል ልደቱም መናገሩ ህዝቡም መነሳሳቱ ስህተት አይደለም፤ በኢህአዴግ ፈፁም ስህተት፤ በልደቱና በኢዴፓ በፊት ትክክል ከነሐሤ 17፣ 97 በሁዋላ የአመፅ ማነሳሳት ቢባልም፡፡ ብዙ የቅንጅት ሰዎች መታሰራቸው፤ ገሚሶቹ ፓርላማ መግባታቸውም በኔ ግምት ትክክል ነበር፤ በያሉበት የቅንጅትን መንፈስ እስካልከዱና የህዝብና የህግን የበላይነት እስካልከዱ ድረስ፡፡ ነገሩ ግን የተገላቢጦሽ ሆነ፡፡ ስለዚህ አቶ ፍቅሩ፣ በነበረው ችግር ኢዴፓና ልደቱ ቅርታ ይጠይቁ ስል ድምር የ97ድህረ-መርጫ፣ ከምረጫ በሁዋላና የኢዴፓ የፓርላማ ዘመን ተመልክቼ፣ ስህተቱን አምኖ ካስተካከለ ኢዴፓም ሆን ልደቱ በቁም ከሞቱት የድሮ ቅንጅት ኣካላት የተሻለ እድል እንዳለው ተስፋ በማድረግ እነጂ እንደርሶና እንደቲመርጋ የጎሽ ጎሽ ድጋፍ (በዘመኑ አነጋገር መርዶ ነጋሪና ልማት አብሳሪ ፅንፈኝነት) ተቆራንቶኝ አየደለም፡፡
  4.ዋናው ያነሱት የምርጫና የፓርላማ ለዩነት እኔ እንደሚገባኝ የጊዜና የአፈፃፀም እነጂ እርሶ እናዳሉት አየደለም፡፡ ፓርቲዎች ዋና ሊሰሩትና ሊያስተካክሉት የሚፋለጉትን አጀንዳ በምርጫ ጊዜ ያቀርባሉ፤ ህዝብ ከፍለገ በማስተዋል (ወይም እርሶ እንዳሉት በስሜት) ይደግፋቸዋል፤ ይመርጣቸዋል፡፡ ቅንጅት (እና ልደቱ) የወደብ፣ የግለሰቦች መብት፣ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል፣ ሃሳብን (በፓርላማ ጭምር ለድምጽ) በነፃ ማቅረብ አጀንዳ አቀረቡ፤ ህዘቡ በማስተዋልና በስሜት እስከሞት ደገፋቸው፤ መረጣቸው፡፡ ልደቱ (ኢዴፓ) ተመረጠ፣ ፓርላማ ገባ፣ ሃሳቡን ህግ በሚፈቅደው መሰረት አጀንዳ ማስያዝ መብት አግንቼ ነበር አለን፡፡ ግን ዋና ዋናዎቹ የተመረጠበትን አላማ ወደጎን ትቶት አምስት አመታት ነጎዱ፡፡ እንግዲህ ይሔ አሉባልታ አይደለም፤ ሌሎች የተሰሩ አናሳ ነገሮች የሉም ማለቴም አየደለም፤ ጠቅላይ ሚንስትሩን ከመውገር ጋርም አይያያዙም፡፡ አቶ ፍቅሩ ወይ ጥያቄውን ፍለፊት መልሱት፤ አለበለዛ ይቅርታ በሉና ለሚቀጥለው ለማሻሻል ተወዳደሩ፤ ካልሆነ ግን በስሜት የሚነዱ፣ የአዋቂ አጥፊ፣ ማን እንደላካቸው የማይታወቁ… እያሉ መስደቡና ዙሪያ ጥምጥም መሄዱ ሆድ ያስብሰናል፤ ዘመኑ የሚፍልገውን ጀግና ያሳጣናል፡፡ አሁን የፓርላማ እድሉን ገጥሙዋቸው የታዩና አዲስ የተመስረቱ ፓርቲዎች እኛ ከፓርቲ ውጪ ያለን ሰዎች መለኪያ ሜትራችን ምን እንደሆን ብታውቁት ዴግ ነው፡፡
  5.አቶ ፍቅሩ፣ ህዝብ ቀስቃሽ እነቅስቃሴ ትክክል እንዳልሆነ፣ በቅስቀሳው የሄዱት እንዳለቁ፡ ኢዴፓ ለመርዶ ነጋሪ እንደቀረ ለመግለጽ ሞክረሁዋል፡፡ ህዝብን ያልፍለገውን እንዳይመርጥ፣ ተቃውሞውን እንዲያሰማ መቀስቀስ እኮ ትክክል ነው፤ ዲሞክራሲያዊ ምርጫና መብት ያለዚህ የለምና፡፡ በቅስቀሳው ሄዶ ማለቅ ትክክል ነው አይደለም ማለት ባይቻልም፣ የሄዱትን መጨረስ ግን የምንታገልለት ስህተት ነው፡፡ ኢዴፓ ባልቀሰቀሰው አመጽ አይጠየቅም ላሉት፣ እርሶ እንዳሉትና እኛም በእሳቱ እንደተቃጠልነው ህዝቦች እነዳነው ቅስቀሳው የተስራውና የተጠናቀቀው ገና በድህረ-ምርጫው የቅንጅት (በተለይ የልደቱ) ቅስቀሳ ነበር፡፡ እና በምን ሂሳብ ነው እኛ በማናውቀው ልደቱና እናንተ በምተረዱዋት ነሐሤ 17፣ 97 አንዱ ከደሙ ንፅህ ሌላው አሉባልተኛና መርዶ ነጋሪ ሳይሆን የሚቀረው፡፡
  6.በቅስቀሳ ኢህአዴግን ውሃ ውሃ ልታሰኙ ነው ወይ ብዬ ሰልጠየኩም፤በደንብ ሰንብቡት፡፡ እናሰኛለን ያለው ልደቱ ነው በቪኦኤና በፓልቶክ፡፡ ይሄን መረጃ ይዤ ግን ጥያቄዬ የነበረው በምርጫ ጊዜ ያቀዱትን ዋና ዋና ዓላማ ለ5 ዓመታት ወደጎን ብሎ ይቅርታን ትቶ ምርጫ ላይ ለመፎከር መአጋጀት አይደብርም ወይ ነበር፡፡ መልስዎ በተዘዋዋሪም ቢሆን ምርጫና ፓርላማ የተለዩ መሆኑን ያላወኩ ጀዝባ እንደሆንኩ አድርገው ለማስረዳታ ለመስላቅ ሞክረዋል፡፡ 100 በ100 የምርጫ እቅድና የፓርላማ ትግበራ አንድ እንደማየሆኑ ጠንቅቄ አውቃለው፡፡ ግን ግን እረሶ እንደሚሉትና ኢዴፓና ልደቱ ባለፍው ዘመናችን እነዳሳለፉት አይነት ለዩነት ማንም እንደማይቀነለው ስናገር አሉባልታ አየሆንብኝም፤ ከምርጫ በፊት ኢፍትሃዊ የሃባት ክፍፍልን፡ ወደብ አልባነትን መዋጋት፣ ህዝብን ማስተባበር፣ መቀስቀስ፣ ታግሎ ማታግል፣ ህዝቡ ሃሳቡን እንዲግልፅ ማደረልግ፣ በፓርላማ ትግበራ ግን ከነሐሤ 17፣97 በፊት የቆሙለትን ዓላማ ውጉዝ ማለት፣ 3ኛና ጥሩ አማራጭን ብቻ በማነብነብ 5 ዓመታት ማሳለፍ፡፡
  7.ውድ ፍቅሩና መስል አባላትና ደጋፊዎች፡ ኢዴፓና ልደቱ ብዙ ጥሩ ነገር እነዳላቸው ሁሉ መንገዳቸውን ኮረኮንች ያረገባቸው ብዙ ጥፋቶችና ስህተቶች አሉዋቸው፡፡ ያቅሜን በተወለጋገደ ፅሁፌ ለመገላለጽ ምክሬያለሁ፡፡ ዋናው ግን ለተገደሉ ሰዎች ዋና ተጠያቂ ሌላ ቢሆንም (አሉባልታ ሳይሆን ወንጀል አንዳይሆንብኝ ነው ሌላ ያለኩት) ኢዴፓና ልደቱ ለነበራቸው አስተዋፅኦ፡ እንዲሁም ነሐሤ 17 በሚል የማናውቀውና 3ኛ አማራጭ በሚል ጥሩ ቲዮሪ ነገሮች ብቻ 5 አመታት መስራት የሚገባውን ባለመስራቱ ይቅርታ ሊጠይቅና ወደፊት ሊያስተካክል ይገበዋል፡፡ ኢትዮጵያ ጀግና ካጣች 3 መንግስታት አለፉ፡፡ ቲዮድሮስና ሚኒሊክ የኢትዮጵያን ጀግንነት ጀምረውት አለፉ (ዳር ድንበርን ከልለው ማስከበርና ውስጡን ማልማት)፡፡ ቀጣዮቹ መንግስታት እነርሱ የጀመሩትን ጀግንነት በጅምር ለማስቀረት የፈጣሪ፣ የአብዮት፣ የዘር፣ የፓርቲ ጀግና ሆኑብን፡፡ ልደቱም ገና ከዚህኛው የከረመብን ጀግንነት ስላልወጣ እንደ አቶ ፍቅሩ የሚያደነቁር ጀግንነት ብታምኑም ባታምኑም እያላችሁ ባታደነቁሩኝ ደስ ይለኛል (ይቅርታ አብራኝ ያደገች ብእሬ አንዳንድ ብሶት ላይ ዘለፍ እያለችብኝ ነው ባታደነቁሩኝ ያለኩት)፡፡ ለኔ ጀግና የተከለለውን የኢተዮጵያን ወሰን ምልክት አድርጎ፣ በውስጡ ያሉትን ሓበቶች እኩል አልምቶ፣ ሙስናን የሚጠየፍና የሚያዋርድ የተማረ ዜጋ ገንበቶ፣ ዜጎችዋ ዳር እስከዳር ለብሰው የሚያጌጡባትን ቀመር አስልቶ፣ በጉልነትና በጥይት አረር ሳይሆን በእውቀትና በፍቅር የሚመራ ነው የኢትዮጵያ ጀግና፤ የዘመኑ ጅግና፡፡ ይሔ ጀግና ቅንጅት ውስጥ ሞልቱዋል ብለን ከነፍን ልናጀግነው፤ ይሔን ጅግና የሚጠሉም ከነፉ በጅምር መቅደላ ሊያስቀሩት፡፡ ጀግናው ግን የኢትዮጵያን የጀግንነት ካባም ለመልበስ ሳይመኝ የመቅደላም ተራራ ድረስ ሳያስደክም አእምሮው ውስጥ ሳይወለድ በሰበሰ፡፡ ከፓርቲ ጅግንነት ውጪ ሆኜ ሳየው፣ አቶ ፍቅሩ፣ ልደቱ ከነዚህ ውስጥ የቱጋ እንዳለ ለማወቅ ይከብዳል፡፡ ወደፊት ግን ሊሆን ይችላል እነደረሶ አይነት የተለምዶ መልካም ብቻ አብሳሪ ደጋፊ ቸል ብሎ ችግሮቹን አስተካክሎ ከሔደ፡፡ ለበለዚያ የርሶ ጀግና ብቻ ሆኖ ይቀራል፤ እንደማንናውም የሰማእታት ሀውልት በማሰራት የድሓ ገንዘባችንን እንደጨረሱ ያለፉ ጅግኖች ሁሉ፡፡

  ተግባባን አቶ ፍቅርና ቲመርጋ፡፡

  ከፍኖተ-ኢትዮጵያ

 15. ፍኖተ – ኢትዮጵያ፤
  ሃባ ፍሬ ለሌለው ጽሑፍዎ ውድ ጊዜየን መስዋዕት አድርጌ መልስ የጻፍኩልዎ፤ ዘለፋና አሉባልታም ቢሆን ጽሁፉን ለማዘጋጀት ቢያንስ ጊዜና ጉልበት አባክነዋልና ብዕረ-መንገዴን ከማውቀው ሀቅ ጨልፌ ለእርስዎም ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ሃሳብ ለመፈንጠቅ ነበር። እርስዎ የፈለጉት ግን ተልካሻ ነገሮችን እያነሱ አታካሮ መግጠም እንጂ ትምህርት (ግንዛቤ) ለማግኘት አለመሆኑን በሚገባ ተረድቻለሁ። ሥራ እንዳንሰራ በማድረግ “አቅጣጫ ለማሳት” አስበው ከሆነም አይልፉ! ይህ የተነቃበት “ታክቲክ” ስለሆነ ሌላ ዘዴ ይሞክሩ! እርስዎ ጋር እንካ ስላንቲያ በመግጠም የማሳልፈውን ጊዜ በደቡብ ገረሴ ወረዳ ወይም በአማራ አቸፈር ወይም በአፋር መተሃራ ላይ የኢህአዴግ ካድሬ የሚያሳድዳቸውን የኢዴፓ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ጉዳይ ብከታተል ይሻላል። ብቻ … ለእርስዎም አምባጓሮና አታካሮ የሚወድ ሰው እንዲገጥምዎ በፆም በጸሎት አልለይዎትም። አዲሱ የፈረንጆች ዓመት መልካም የንትርክ ዘመን ይሁንልዎ!
  ፍቅሩ አየለ በላይ፤ ከሸበል በረንታ

 16. የእኔም ስም ከአቶ ፍቅሩ አየለ ጋር ተዳብሎ የተገለጸበት ሁኔታ ስላለ እኔም የበኩሌን አስተያየት ልግለጽ። ፍኖተ ኢትዮጵያ በተከታታይ የጻፏቸውን “አስተያየቶች” አይቻቼዋለሁ። ለአንድ ጉዳይ እንኳ መረጃ መጥቀስ አልቻሉም። መረጃ ያልታከለበት አስተያየት ደግሞ “አሉባልታ” ካልሆነ በስተቀር ሌላ ስያሜ ሊሰጠው አይችልም። ጽሁፋቸው ከመነሻው ጀምሮ “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ” ዓይነት ነው። ይኸውም፤ አቶ ልደቱ የጻፉት ዶ/ር ያቆብ “ቅንጅትን ያፈረሰው ልደቱ ነው” ብለው ለጻፉት የሚሆን መልስ ነው። ፍኖተ ይህንን የልደቱን ጽሁፍ አንብበው “እዚህ ላይ እንዲህ የተባለው እንዲህ ቢሆን ወይም ስህተቱ ቢታረም ወዘተ.” በሚል መንፈስ አስተያየታቸውን መጻፍ ሲገባቸው፣ አቶ ልደቱ በጽሁፋቸው ያላነሱትን ስለየፓርላማ አጀንዳ ጉዳይ ምናምን ያነሳሉ። እሱም በመረጃ የተደገፈ አለመሆኑ ከፋ። እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ ምን ይባላል ታዲያ?… በአጭሩ፣ በፍኖተ ጽሁፍ ውስጥ ቁም ነገር ልፈልግ ብለው ቢሞክሩ፣ በአንድ ክምር ገለባ ውስጥ አንዲት ቅንጣት ፍሬ ለማግኘት የሚደረግ ከንቱ ድካም ነው የሚሆን። …. እኔም የአቶ ፍቅሩ የመጨረሻ አስተያየት ተመችቶኛል።
  ቲመርጋ መሓመድ ሓጎስ

 17. ቡሴራ ዶ/ር ያቆብን ሰሞኑን ልደቱን እያነሱ ጻፍ ጻፍ ያሰኛቸው አንተ ከጠቀስካቸው ነገር ውስጥ ሴረኝነት የሚለው ነው የሚመስልኝ፡፡ ዶ/ር ያቆብ በተለይም ጀሌዎቻቸው እኮ በአብዛኛው ውጭ ሀገር ያሉት ኢዴፓ ሞቷል እንዴት ስለሞተ ነገር ሰው ያወራል፣ እነርሱን እንርሳቸው ሲሉ ነበር የቆዩት፡፡ አሁን እንደገና ያቆብና ተከታዮቻቸው ስለኢደፓ ጭንቅ ጥብብ የሚያደርጋቸው እንደገና ህዝቡ ከኢዴፓ ጋር ትስስር ፈጥሮ ከፍተኛ ድጋፍ ሊገኝ ነው ብለው በመስጋታቸው ነው፡፡

 18. Lidetu is right on responding and putting the facts clearly to the people. Dr. Yacob have been EPRP, Weyane supporter, EDP, Kestedemena, kinijt, UDJ, Medrek, God knows which party is next. dr. yacob in the first place is a big liar. Shame on him. He has no moral authority what so ever to critcize the honorable Lidetu using fabricated lies. dr yacob is a shameful person, He in 1992 was cheering Issayas and Meles and drinking whisky with them in Menlik palace while Eritrea , asseb our port, more importantly thousands of Ethiopian armed forces being dragged and massacred by Shabia in Ertirea. He now comes back and act like he is for asseb and all that crap . He is very dangerous but thank God the Ethiopian people are finally seeing the truth. We all know dr yacob is working with his cousin birrhanu nega, both master minders for the destruction of knijit and killing he aspiration of the Ethiopian people. time will clear all the rumors. Lidetu the most brilliant young politicans Ethiopia have ever seen in our times, no quesiton about that. Hope and pray EDP wins big in the coming elections. no more lies, no more lies.

 19. ፍቅሩና ቲመቸጋ

  እውነትም አሉባልታና መረጃ ምን እንደሆነ ገና ብዙ መማር አለባችሁ፡፡ እንኩዋን የልደቱን ጥፋት አይደለም ጥሩ ጎኑንም ጠነቅቃችሁ አላወቃችሁም፤ እና ለመደገፍም ሆነ ለመንቀፍ መለስ እንዳሉት ገና ህፃን ናችሁና ዝም በሉ፡፡ እናነተ ገና ልደቱ ለዶር. ያዕቆብ የፃፈውን ይህቺን ደበዳቤ ብቻ ነው የምታጣቅሱት፡፡ ስለዚህ ቪኦኤ፣ ፓልቶክ፣ ከፓርላማ፣ያለፍው ምርጫ ሒደት… የሚሉት ማስረጃዎቼ ለናንተ አሉባልታ ሆኑባችሁ፡፡ ወይ ጉድ ምንይነቶቹ ቢራ ገልባጮችና ያገርቤቱ በኤፍ ኤም አድናቂህ ነኝ የሚሉ በውጪው ፓልቶክ የሚራገሙ አንባቢን ገጠመኝ እቴ፡፡

  ለማንኛውም እንደናንተ ሳይሆን አዲሱ ዓመት ሰው የማይገደልበት ምርጫ ግን ሁሉም የስራውን የሚ ያገኝበት ያርጋልን፤ ጠሸበል በረንታ፣ አቸፈር፣ መተሃራና እዚህ እኔ ያለሁበት ወረታም ሆነ በመላው ኢትዮጵያ ላሉ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች (ኢዴፓን ጨ ምሮ) መልካም እድል እመኛለሁ፡፡ የነፍቅሩ ዌብ ሳየት ላይ የተለቀቀ የሃገር መ ርህ እንዲህ እንደኔ ደግ የሚመኝ መስለኝ፡፡

 20. Love him or hate him. He is absolutly dynamic.
  Nothing is far from the truth, what we have heard about Ato Lidetu is been a total lie and pure fabrication cooked up
  by EPRP and its news allies.
  Shame on them to undermine our understanding, and to take us for ride for so long.
  [b][/b][b][/b]

 21. “CUDP has now emerged more unified and powerful, receiving messages of continued support from the Ethiopian people.”
  [url]http://www.ethiomedia.com/fastpress/lidetu_ayalew_suspended.html[/url]

  This was from ethiomedia quoting Engineer Gizachew after former kinjit suspended Lidetu and Mushe.
  Now after 5 years Dr Yaqob is telling us kinjit’s split in to 7 pieces is because of Lidetu while engineer gizachew told us 5 years ago that Kinijit is more unifed and powerful by getting rid of lidetu.
  Of course we need to note that Engineer Gizachew lied big time when he said 75,000 signature were collected from Lideta woreda. It is shame when a person of his age tells a fabricated story to the public.(የአገሬ ሰው ቅሌታም የሚለው እንደዚህ አይነቱን ሰው ነው፡፡ )

Comments are closed