Logo

ችግራችንን ለመፍታት ወይስ ይበልጥ ለማወሳሰብ?

February 6, 2010

የፕ/ር መሳይ ጽሁፍ ጃዋር ሲራጅ የተባለ ደራሲ ስለ ትግራይ ብሔርተኝነት የፃፋትን ጽሁፍ መነሻ በማድረግ አስተያየታቸውን ለማቅረብ ቢሆንም በሌሎች ጽሁፎቻቸው ደጋግመው ካንፀባረቋቸው ሀሳቦች በይዘት ያልተለዩ ግንዛቤዎች አንሸራሽረዋል፡፡ በዚህ ጽሁፋቸው ፕ/ር መሳይ ካነሷቸው ጉዳዬች ጋር በቀጥታ የሚያያዝ አንድ ሀሳብ በፕ/ር አለማየሁ ጽሁፍ ውስጥ ይገኛል፡፡ ይበልጥ ያስደነገጠኝ በፕ/ር አለማየሁ ጽሁፍ ውስጥ ያገኘሁት ይህ ሀሳብ ነው፡፡ የሁለቱም ፕሮፌሰሮች ጽሁፎች በአንድ አቅጣጫ አይቼ በዚህ መልክ ለመከራከር የፈለኩበትን ምክንያት ለአንባቢ ማስረዳቱ ብዙም ጠቃሚ አይደለም፡፡ ነገር ግን ክርክሬ የሀሳቦቹን ይዘት ተመሳሳይነትና መነሻዬን በበቂ ሁኔታ ማስረዳቱ አይቀርም፡፡ ስለዚህ በቀጥታ ወደ ሀሳቦቻቸው ላምራ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Share

3 comments on “ችግራችንን ለመፍታት ወይስ ይበልጥ ለማወሳሰብ?

 1. አመሰግናለሁ ሔኖክ፡፡

  በብዙ ሃሳቦችህ እስማማለሁ፡፡ ግን፣
  1.በህብረብሄር የተደራጁ ሲፈረካከሱ አይተናል የሚለው የተሳሳተ ነው፡፡ የተፈረካከሱት በህዝብ ድጋፍ ማጣት ወይንም በህብረ ብሄራዊነታቸው አልነበረም፡ በመሪዎቹ ግላዊ ባህሪና የስልጣን ሽኩቻ እነጂ፡፡ የ97 ምርጫና የኢህአዴግ የታላቂቱዋ ትግራይ የደደቢት ውጥንና የአሁኑ የሀገሪቱዋ መሪ የመሆን ሒደት ጥሩ ማመላከቻዎች ናቸው፡፡ በ97 ምርጫ እኔ በተወለድኩበት ዴራ የምርጫ ጣቢያ የድሮው የኢሰፓ ዋና አቀንቃኝ የነበረና የቅንጅት ተወዳዳሪ አቶ በረደድ ዘውድነህ ኦህዴድን፣ ኦፌዴንንና ኦኤልኤንፒን ሲያሸንፍ ጥሩ ኦሮሞ ሆኖ ወይንም የኦሮሞ ብሔረተኝነትን ደግፎ ወይንም የድሮ ፀባዩ ተሸሎ አልነበረም፡ ህዝቡ ህብረብሄራዊነት በ1984 በአካባቢው በኢህአዴግ ተለኩሶ ካቃጠለው አጉዋጉል የብሄረተኛ እሳት ስጋት ያላቅቀናል ከሚል ጉጉት እንጂ፡፡ ህውሃት ጉና ተራራ ላይ ታላቂቱዋ ትግራይን በኢህአዴግ መርህ ማጠናከሩና ለዚህ መብቃቱ ህብረብሄራዊነት በኢትዮጵያ መፈራረሱን አያመሳክርልህም፡፡

 2. 2.ድሮም አሁንም ሆነ በብዙሃኑ ህዝብ ስሳቤ እናንተ ፖለቲከኞች እንደምትሉት ፀረ ጎሰኝነትና አንድነት ተመሳስለው ተነግረው፣ ተፅፈውና ተተንትነው ኤውቁም፡፡ ድሮም ዛሬም ኢትዮጵያ ማለት ጎሳዎችዋ፣ ብሄሮቹዋና ህዝቡዋ እራሳቸው ሆ ብለው ከአውሮፓ ተቀራማቾች በደማቸው ባስከለሉዋት አለማቀፍ ድንበሩዋና የባህር በሩዋ የተከለለች ለሁሉም እኩል ማገልገል ያለባት የሃገርና የህዝብ መኖሪያ ቦታ ስያሜ ነበር ነውም፡፡ አሁን የምትጠሩዋት ባለብዙ የግጭት ድንበሩዋ የመሃል ክፍሉዋ ግን ሌላ ስያሜ ካልተሰጣችሁዋት በስተቀር ኢትዮጵያ ለማለት አስቸጋሪ መሪዋም የኢትዮጵያ መሪ ለመባል የማያስደፍር ነው (የአሁኑን ህገ መንግስት መድፈሬ እንዳልሆነ ይታውቅልኝና)፡፡

 3. 3.ብሔሩን ትቶ ኢትጵያዊነት እንኩዋን በፕሮፌሰርነት እሳቤ በደርግም ሆን መቼም አልነበረም፡፡ አይኖርምም፡፡ እንዳልከው በእውቀትና በጥበብ መምራት እጦት ላይ ብዕርህ ቢተባልን እንወሃለን፡፡
  4.የቡድንና ግለሰብን መብትም ገነጣጥሎ በፅንፍ መጉዋዙ ጊዜን መግደል ነው፡፡ የቡድን መብት አማራ ይውጣልን ብሎ ቢላዎ ከመሳል በመለስ ለኢትዮጵያዊነት በጣም አስፈላጊና ገና ብዙ የሚፃፍበትና የሚሰራበት ነው፡፡
  5.በአጠቃላይ ሔኖክ ከላይ ያነሳሁዋቸው የግል ጥርጣሬዎች በብዙን እውነታና የሃገር ልማት ቃኝተን ብናነብና ብንፅፍ ብዙ የምንጠቅም ይመስለኛል፡፡

  ከፍኖተ

Comments are closed