Logo

ዛሬም ይቻላል!!!

February 22, 2010

በግንቦት ወር አጋማሽ ለሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ በኢዴፓ የምርጫ ዘመቻ ማስተባበሪያ ግብረ ኃይል የተዘጋጀ

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Share

2 comments on “ዛሬም ይቻላል!!!

 1. It is good and EDP should continue in this way, but you have to now your basic weakness
  1. you have only less than three years with this alternative, so it is not enough to adminster the country with more than 80 mln. population and big divesity infact with opposing article 39 and land issues which are the main concern of more than 88% of the population.

  2. It is not very clear you role on the 2005 election and your relation with all previous so call ‘KINIJIT’ it seems there is something hidin which is your are not say it.

  3 your party looks like one man party everything is with Mr. Lidetu who have a criminal record on his life and then he became a politcian to avoid that record, but he can not avoid.

 2. Kebede/ከቤ፤
  እንደ ጥሩ ነገር አሉባልታና ለኢዴፓ ያለህን ጥላቻ ለመግለጽ ምን አጣደፈህ ጃል?! ሰው መጣደፍ ያለበት ለበጎ ነገር እንጂ ለከይሲ ተግባር መሆን የለበትም። ለማንኛውም፤

  1. “you have only less than three years” ያልከው አልገባኝም። ለምርጫው ከሆነ የቀረን 3 ወር እንጂ 3 ዓመት አይደለም። አንዱን ይዘህ አንዱን አንጠልጥለህ አትሩጥ። ሰከን በል። “የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል” ነው የሚባል። ኢዴፓ ወደ ምርቻ ድንገት የመጣ ፓርቲ አደለም። የኢዴፓ አማራጭ ፖሊሲ የቀረበው ከሰባት ዓመት በፊት፣ በሰኔ ወር 1995 ዓ.ም ጀምሮ ነው። ስድስቱም ቅጽ በፓርቲው ዌብሳይት ላይ አለልህ፣ አንብብ። ኢህአዴግ ሀገር የሚመራበትን ፖሊሲ ያወጣው ግን መንግስት ከሆነ በኋላ ነው። ኢዴፓ መንግስት እስከሚሆን አልጠበቀም። አንቀጽ 39 ሆነ የኢህአዴግ የመሬት ፖሊሲ ለሀገር እንደማይጠቅም በተግባር የተረጋገጠ፣ “የኢትዮጵያ ሕዝብ” የተጸየፋቸው መሆኑ ስለተረጋገጠ በዚህ ረገድ የሚያስጨንቀን ነገር የለም። ጭንቀቱ ያለው አንተና ኢህአዴግ ጋር ብቻ ይመስለኛል።

  2. “በ1997 ምርጫ ቅንጅት ጋር የነበራችሁ ሚና ግልጽ አደለም” ያልከውን በተመለከተ፤ አንድ ለምርጫ የቀረበ ፓርቲ አማራጭ ፖሊሲውን ያቀርባል እንጂ ባለፈው ምርጫ የነበረውን ሚና በመዘርዘር “ምረጡኝ” አይልም። የ97ቱ ምርጫ ቅዠት ሆኖ ለምን እንደሚያሰቃይህ ባይገባኝም፣ ኢዴፓ ምንም ዓይነት የማጭበርበርም ሆነ ሰውን የመግደል ተግባር ውስጥ ስላልተሳተፈ በዚያ ምርጫ የነበረውን ሚና ለመግለጽ የሚፈራው ነገር የለም። ለማንኛውም፤ ሁሉም ነገር በታሪክና በሕዝብ ፊት ተመዝግቦ ያለፈ ስለሆነ “የሚወራረድ ሂሳብ” ካለ እንዳስፈላጊነቱ ወደፊት አጀንዳ ከፍተን እንነጋገርበታለን።

  3.”ኢዴፓ የአንድ ሰው ፓርቲ ነው” ያልከውን በተመለከተ፤ ከኢዴፓ ይልቅ ኢህአዴግ እኮ ለ30 ዓመታት በአንድ ሰው እየተመራ ያለ የአንድ ሰው ፓርቲ ነው። መቼም፣ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ አባላትና 25 የማዕከላዊ ኮሚቴ ያለው ፓርቲ ሁሉም በአንድ ጊዜ ሊቀመንበር ሊሆኑ አይችሉም። አንዱ ተመርጦ ሊቀመንበር ይሆንና የሊቀመንበር ስራ ይሰራል። ሌሎቹ ደግሞ የየድርሻቸውን ይሰራሉ። ኢዴፓ የአንድ ሰው ፓርቲ ቢሆን ነው እንዴ በዘንድሮው ምርጫ በ305 ወረዳዎች ዕጩዎችን ያቀረበው? ልደቱ ወንጀለኛ/ገዳይ ነው ያልከውን በተመለከተ፣ ማስረጃ ካለህ መክሰስ ነው። ደግሞስ ወንጀለኛ ሰው ራሱን ይደብቃል እንጂ ሁልጊዜ አደባባይ ወደሚያወጣው ፖለቲካ ይገባል እንዴ? ለነገሩ አንድ ወይም ሁለት ሳይሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እየገደለና እያስገደለ ያለው ማን ነው? “ሆድ ይፍጀው” አለ ጥላሁን ገሠሠ! ከዚህም በላይ መጻፍ ይቻላል… ግን ይብቃኝ። ከተመለስክ እመለሳለሁ።
  ቲመርጋ መሓመድ ሓጎስ

Comments are closed