አንድነት ፓርቲ የብርቱካንን ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ሊወስድ ነው
በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ በወዳጅ ዘመዶቻቸው የመጎብኘት መብታቸው እንዲጠበቅላቸው በሚል ፍርድ ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ ባለመከበሩ፣ ፓርቲው ጉዳዩን በድጋሚ ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ መወሰኑን የፓርቲው ዋና ጸሐፊ አስታወቁ፡፡ ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (ሪፖርተር)
ሰዎቹ በመሰሪ ተግባራቸው “ልጂቱን” ገፋፍተው፣ ገፋፍተው ከርቸሌ ካወረዷት በኋላ አሁን ደግሞ የአዞ እንባ ማፍሰሳቸው አይገርምም? ነው ከነሱ በስተቀር ሁሉም ሰው (በዙሪያቸው እንደተሰባሰቡት ከንቱዎች) “ገልቱ” ይመስላቸዋል? ሰሞኑን ደግሞ “የልጂቱን” ፎቶግራፍ በትልቁ አስነስተው በምረጡኝ ቅስቀሳ በመኪና ላይ ጭነው የሚዞሩትና በየስብሰባ አዳራሹ ፊት ለፊታቸው የሚገትሩት በእሷ ስም ለመመረጥ ነው? አዎ! ለነገሩ የሚሸጥ ሃሳብ የላቸውም። እሷኑ ይዘው ቢቀርቡ ይሻላል።… ከዚህ ሁሉ ማፈሪያ ተግባር ግን ፖለቲካው ቢቀርባቸው ምናለ?