Logo

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ም/ሊ መንበር ሆነው ተመረጡ

April 20, 2010

source http://www.birtukale.org

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ( አንድነት ) በትላንትናው ዕለት ሚያዝያ 10 ቀን 2002 ዓ.ም ልዩና አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባኤ ያካሄደ ሲሆን በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በውሳኔውም መሰረት

1. መንግስት በመሪያችን ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ የፈፀመው እስር ህገወጥ በመሆኑ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እነዲፈታ ለመንግስት ጥያቄ እንዲቀርብ
2. ህገ-ወጡ የአንድነት አመራር በመሪያችን ላይ ክህደት ፈፅሟል፡፡ ይህም ስለሆነ ከአመራርነት አንዲነሱና በምትካቸው ሌላ አመራር እንዲመረጥ
3. አንድነት ከመድረክ ጋር ያለው ግንኙነት በደንብ ውይይት ያልተደረገበት በመሆኑ አዲስ የሚመረጠው ብሄራዊ ምክር ቤት ጉዳዩን በድጋሚ እንዲያጤነው እና ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም የፀደቀው የድርጅቱ ፕሮግራም እንዳለ ምንም ማሻሻያ ሳይደረግበት እንዲቀጥል፡፡
4. ህገ-ወጡ አመራር ቡድን የስልጣን ብልግና መፈፀሙን
5. ህገ-ወጡ የአመራር ቡድን በተለያዩ ጊዜያት የተገለፁትን የህግ ጥሰቶችና በስልጣን መባለግ ሊፈፅም የቻለባቸውከተለያዩ ምክንያቶች አነዱ መዋቅሩ ለዚህ አመቺ መሆኑ ጉባኤው በመገንዝብ በመዋቅሩን ላይ የቀረቡትን ማሻሻያዎች ብሄራዊ ምክር ቤቱ በደንብ ውስጥ እንዲያካትተው ሃላፊነት ሰጥቷል፡፡ በዚሁ መሰረት 30 የብሔራዊ ምክርቤት አባላትና 14 ተጠባባቂ አባላትን የመረጠ ሲሆን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የድርጅቱ ሊ/መ ሆነው እንዲቀጥሉ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ም/ሊ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡

አሁን በተሻሻለው የድርጅቱ መዋቅር መሰረት ም/ሊ መንበሩ ሌሎች አምስት አባላትን በመምረጥ የራሳቸውን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በማዋቀር ለምክርቤት የሚያፀድቁ ሲሆን የስራ ጊዜውም ሊ/መንበሩ ከእስር እስከሚፈቱበት ጊዜ ይሆናል፡፡
ሊ/መንበሩና ም/ሊ መንበሩ ሲቀሩ ሌሎች አምስት የስራ አስፈፃሚ አባላት የብሄራዊ ምክርቤት አባላት መሆን የማይችሉ ሲሆን ከብሄራዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ለሥ/አስፈፃሚ ኮሚቴ ቢመረጡ ወዲያውኑ የምክር ቤት መቀመጫቸውን በመልቀቅ በምትካቸው ከተጠባባቂ አበላት መካከል ባገኘቱ ድምፅ መሰረት እንደሚተኩ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በስተመጨረሻም በጉባኤው የአቋም መግለጫ ላይ እንደተንፀባረቀው ህገ-ወጡ የአመራር ቡድን በእጁ የሚገኙትን የድርጅቱን ንብረትና ሰነድ አዲስ ለተመረጠው አመራር እንዲያስረክብ ወስኗል፡፡

Share

7 comments on “ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ም/ሊ መንበር ሆነው ተመረጡ

 1. በስተርጅና ምንኩስና አሉ አበው! በወጣትነታቸው ከኋላ ሆነው “ግፋ በለው” እያሉ ስንቱን ወጣት እንዳላስጨረሱ ዛሬ ጀግንነቱ ከየት መጣ? እኮ የወንዶቹን ሱሪ ከየት አገኙት?

 2. Our old spend his entire life without understanding his beloved country. With his sge and knowledge he should have mentored, guide and advice his people. But he is famous and known for lekso and roro. tebelashe, tesebere, tetameme, gedel geba etc etc are what we have been listening from him for almost all his age. Professor mehe new enbe awaki shimagile agerwon yemyageleglut?????

 3. Prof.Mesfin did great job. He alwayes stands for the truth and one Ethiopia. If Birtukan released, for sure she will support the Prof.group because she knows very well what these power starved Gizachew and his cabine stand for.She has already said it during their meeting. Even she left the meeting because them.
  He will win with true Ethiopians.

 4. Prof. Mesfins group composed 177 founding members and they are the majority. They have the right to held a meeting.

  Sheme for Andnet !!! a party that could’t solve its simple inter-party problem.
  Andenet can’t solve the complicated problem of Ethiopia.

 5. Professor Mesfin did the right thing. I hope the new UDJ headed by Professor Mesfin will be endorsed by the election board and undo the damage done by a few self-centered individuals.

 6. Gambello፣ መነው ጭንቅላትህን አሰራው እንጂ! ፖለቲከኛ እኮ መነኩሴ አይደለም። እናም፤ የሚሰራው ለስልጣን እንጂ ለጽድቅ ሊሆን አይችልም። ለስልጣን መስራት ደግሞ ሀጢያትም ነውርም አይደለም። አንተ ያልገባህን ጉዳይ ለማወቅ ጠይቅ እንጂ አትራገም፣ አታውግዝ። በነገራችን ላይ አንተ ራስህ የፖለቲካ ጉዳይ (የስልጣን ጉዳይ) ያገባኛል ባትል ኖሮ ይህንን ዌብሳይት አትከታተልም ነበር። ወዳጄ፣ ጣትህን ሌሎች ላይ አትቀስር!!!

Comments are closed