ኢዴፓ በአራት ከተሞች ሕዝባዊ ስብሰባ ያካሂዳል

በመጪው ቅዳሜ እና ዕሑድ በሀገሪቱ ደቡባዊ አካባቢዎች በወላይታ ሶዶ፣ በአርባ ምንጭ፣ በሐዋሳ እና በአለታ ወንዶ ከተሞች ስብሰባዎቹ እንደሚካሄዱ የዜና ምንጩ ጠቅሶ፣ ለዚሁም ዝግጅት የፓርቲው አመራር አባላት በሁለት ቡድን ተደራጅተው ወደ ስፍራው መንቀሳቀሳቸውን አስታውቋል።
ይህ በዚህ እንዳለ፤ በገዥው ፓርቲ እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የሚካሄደው 8ኛ የክርክር መድረክ ዛሬ እንደሚደረግ ከስፍራው የደረሰን ተጨማሪ ዜና አመለከተ። በኢንዱስትሪና በከተማ ልማት ዙሪያ በሚደረገው ክርክር ኢዴፓን በመወከል የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ሙሼ ሰሙ እና ወ/ሪት ሣራ ይስሃቅ እንደሚገኙ ታውቋል።
i think what you are doing is right thing for this coutry.our country needs you.i wish you win in this election.
Well done EDP! You are the hope of Ethiopian people.
Bravo EDP.
Lidetu is a very wise man.Now every one copying what you said long a time a go.
Now let them fight each other . You just do your jobb.
EDP is our hope!!!
BRAVO!!!