Logo

“እነ ኢንጅነር ግዛቸው አዲስ የተመረጡትን 11 የአንድነት አመራር አስደብድበው አሳሰሩ”

April 28, 2010

pdf

From

ZIM ANILIM

ሚያዝያ 20/2002
እነ ኢንጅነር ግዛቸው አዲስ የተመረጡትን 11 የአንድነት አመራር አስደብድበው አሳሰሩ፡፡
አዲስ የተመረጠው አመራር በመስራች ምክር ቤት አባላት ውሳኔ መሰረት አስቀድሞ የዕቃና ንብረት ርክክቡን በተመለከተ ደብዳቤ ለኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ለማድረስ ከትናንት በስቲያ ማክሰኛ ዕለት ወደ ጽ/ቤቱ አዲስ የተመረጡት አባላት ቢሄዱም ኢንጅነር ግዛቸው ደብዳቤውን አልቀበልም በማለት እምቢታቸውን ከመግለጻቸውም ባሻገር ጽ/ቤቱም እንዳይቀበል አዘዙ፡፡

የሄዱት ተመራጭ አባላትም  የእምቢታው ውሳኔ አግባብነት የሌለው ቢሆንም በማክበር ከግቢው ለመውጣት መንገድ ሲጀምሩ ዘለፋና ዛቻ በማሰማት ትንኮሳ ቢኮረኩሩም ተወካዮቹ ግን ሰላማዊና ስነ ስርአታዊ በሆነ ታጋሽነት ከግቢ ወጥተዋል፡፡ ምንም እንኳን ኢንጅነር አልቀበልም ቢሉና አቶ አስራትና፤አቶ አንዱ ዓለም፤ አቶ ንጉሴ(የድርጅቱ ጠበቃ) አቶ ብሩ በርመጃና ምክትል ጸሃፊው አቶ መስፍን፤ እመውጫው ድረስ እየተከተሉ በማንጓጠጥና በስድብ ነገር ለመቆስቆስ ቢጥሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ይህም በተወካይ አዲስ ተመራጮች ያውም ወጣቶች፤ ጠብ ቢጀምሩ አንድም ሰው ላይተርፍ እንደሚችል ቢያውቁም የአንድነትን ስም ለመጠበቅና በእስር ያለችውን መሪ ክብር ላለማጉደፍ በማሰብ ተሰድበውና ተዘልፈው መውጣትን መርጠዋል፡፡

ዛሬም እንደገና በፖስታ የተላከው የአደራ ደብዳቤ መድረሱን ካረጋገጡ በኋላ ለርክክቡ ወደ ግቢው ሲገቡ ኢንጅነር ግዛቸው ከግቢው በመውጣትና ለጥበቃውም አንድም ሰራተኛ እንዳይገባ መመርያ በመስጠት ከአካባቢው ተሰወሩ፡፡ጉዳዩ ያልገባቸው የአዲሱ አመራር ተመራጮች ወኪሎች፤ ኢንጅነር ሲመለሱ ካልተመለሱም ደብዳቤው የደረሰ በመሆኑ ከጽ/ቤቱ ቀጠሮ ለመቀበል ግቢው ውስጥ ገብተው በመጠበቅ ላይ እንዳሉ በድንገት በሩ ተከፍቶ አባላት ያልሆኑ ጎረምሶች ወደግቢው ገቡ፤ተከትለውም ኢንጅር ግዛቸውና አጋሮቻቸው በመኪና ሆነው በመግባት ኢንጅነር ግዛቸው ይዘዋቸው የመጡትን ጎረምሶች በሰላማዊ መንገድ ሲጠብቋቸው ወደ ነበሩት ተወካዮች እያመለከቱ ‹‹በሏቸው›› የሚል ትዕዛዝ ስለ ሰጡ ተዘጋጅቶ የተቀመጠውን አጣና እያወጡ በቅድሚያ አቶ ለሜሳ የተባሉትን የቀድሞም የመስራች ምክር ቤት አባል የአሁኑም ተመራጭ ግንባራቸውን ፈነከቱ፤ወኪሎቹ የሄዱበትን መኪና የፊት ለፊት መስታወት ሰባበሩ ከዚያ በኋላ ወጣቶቹን አንድም ነገር በጃቸው የሌለውን በአንድነት መርህ መሰረት ሰላማዊ ሆነው የሄዱትን በጫካና የአውሬ ሕግ የኢንጅነር ሎሌዎች የያዙት አጣና እስኪሰባበር አወረዱባቸው፡፡

እጅጉን የሚገርመው ግን ወኪሎቹ አንዳችም ስንዘራ አለማድረጋቸውና እየተደበደቡ መቆማቸውና በተደጋጋሚ ‹‹ሠላማዊ ትግል እያልን እንዴት ዱላ ታነሳላችሁ ደሞስ ዱላን ምን አመጣው›› ቢሉም ሰሚ ሳያገኙ እንደእባብ ተቀጥቅጠው አቶ ለሜሳም ደማቸውን እያፈሰሱ ወደ ሆስፒታል ሄዱ፡፡
እንግዲህ ሃገርና ሕዝብ እናስተዳድራለን ብሎ ምሎ የተገዘተ አመራር በሰላማዊ መንገድ ሊያልቅ የሚችለውን ጉዳይ በአዲሱ መድረክ አመራሮች ደንብና፤ መድረክ ከሕወሃት መንደር ካመጣው በለው ቀጥቅጠው መመርያ ለዚህ መብቃት የነኢንጅነር ግዛቸውን ዝቅጠትና የአመራር ብቃት ማነስ ነው የሚያሳየው፡፡
እጅጉን የሚገርመው ደግሞ ያ ቢሮ የአንድነት ሆኖ ሳለ፤ ኪራይም የሚከፈለው ለአንድነት ተብሎ ምንም ቢያንስ  ከሃገር ውስጥም ከአባላት በሚሰበሰብና አብላጫው ደግሞ ከዲየያስፖራው በሚገኝ መዋጮ ሲሆን ቢሮዎቹ ላይ በሙሉ ‹‹የአንድነት››››››››› የሚለው ተነስቶ ‹‹የመድረክ …….››በሚል ተለውጦ መታየቱ አንድነት ምን ያህል እየጠፋና በመድረክ እየተዋጠ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል፡፡

እነ ኢንጅነር ግዛቸው ወደ ዱላ የገቡበት ዋነኛ ምክንያት በየትም አካባቢ በከተሞችም በክልሎች ተቀባይነት በማጣታቸውና ቢሮዎች ሁሉ ‹‹ልቀቁ አዲስ አመራር ተመርጧል አስረክቡ የሚለው ግፊት ስለበዛባቸው በጀብደኝነትና በምስለኔ አገዛዝ ተስፋ ለማስቆረጥ የተደረገ ሙከራ ነው፡፡በስተመጨረሻው ገደማ በነኢንጅነር‹‹ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል››ዓይነት ደምወዝ እየተከፈላቸው የሚሰሩት የፓርቲ አባላት ድርጅቱ ስርአት የያዘ እንደሆነ አሁን የምናገኘው ጥቅማ ጥቅም ይቀርብናል በሚል ሰጋት ኡኡታ በማሰማታቸው ፖሊስ በመምጣቱ የተደባደቡት ጉልበተኛ ቅጥር ዱለኞች ግቢውን ለቀው ለመሰወር ሲሞክሩ ተደብዳቢዎቹ እንዳይወጡ አድርገው ፖሊስ በጉዳዩ ቢዘገይም ገብቶ የተጎዱትን ወደ ሆስፒታል ልኮ የተሰበረውንም መኪና በማስረጃነት መዝግቦና ቃል ተቀብሎ ሂደቱን በማጣራት ላይ ሳለ ንጉሴ ነውጤ የተባለው የአንድነት የልምድ ተቀጣሪ ጠበቃ ከሳሽ ሆኖ ተብዳቢዎችላይ ክስ መሰረተ፡፡ ለፖሶቹም የንጉሴን ክስ ተቀብለው በአካባቢ የነበሩትን ምስክሮች ቃል ተቀብለዋል፡፡ ምስክሮቹ በሙሉ እነ እንጅነር ደብዳቢዎች መሆናቸውን መስክረውባቸዋል፡፡ያም ሆኖ ግን እነስዬና ነጋሶ፤ገብሩ አስራትና አንዱዓለም እንዲሁም ሌሎች በስተመጨረሻው የጉዳዩ ባለቤት በመሆን ለፖሊስ አዛዦች በሰጡት ሃሳብ መሰረት ተደብዳቢ የሆኑትና ንብረታቸው የተሰባበረባቸው፤ 11 በመስራች የጉባኤ አባላት የተመረጡት አመራር ወኪሎች ታስረው እንዲያድሩና ደብዳቢዎቹና የህወሀት ወገንተኛ የሆኑት ወገኖች ደብድበውም ንብረት ሰብረውም በነጻ እንዲሄዱ ተደርጎ የአንድነት የመርህ ተሟጋቾችና በጠቅላላ ጉበኤው የተመረጡት ታስረው እንዲያድሩ ተደርጓል፡፡

እንግዲህ ቀደም ሲል ዝም አንልሞች በመንግሥት ይደገፋሉ እየተባሉ በሰሜን አሜሪካ የአንድነት የድጋፍ አሰባሳቢ አመራሮች ሲወነጀሉ የነበረው ለእስር ተዳረጉ፡፡የመድረክ አመራሮችና ደጋፊዎች ግን ወንጀል ሰርተው ፈንክተው ሰብረው በነጻ ወደቤታቸው በክብር ተሸኙ፡፡

ግርማ ካሣ የሚባለው የመድረክ በሰሜን አሜሪካ ሳይመረጥ በወዶ ገብነት የመድረክ አገልይና የአቶ አክሎግ አፈ ጉባኤ አንዳንድ የመርህ ይከበር አመራሮች የወያኔ/ኢህአዴግ አገልጋዮች ናቸው እያሉ ሲወነጅሉና መሰሎቻቸውምም ሲያናፍሱት የነበረው የሃሰት አሉባልታ ዕውነቱ አግጥጦ ወጣ!!
ማን ሆነ የወያኔ/ ኢህአዴግ ሎሌ ታዲያ!!!

11ንዱ የአመራር ተመራጮች በቅድሚያ በኡራኤል ፖሊስ ጣቢያ የተበዳይ ቃላቸውን እንዲሰጡ ሆኖ ወደ አመሻሹ ላይ ወደ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው ከማታው በ3 ሰአት ገደማ ደግሞ አዳራቸው ቄራ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ሆኖ ወደዚያው ተወስደው አዳራቻው እዚያ እንዲሆን ተወስኖ ገብተዋል፡፡

Share

12 comments on ““እነ ኢንጅነር ግዛቸው አዲስ የተመረጡትን 11 የአንድነት አመራር አስደብድበው አሳሰሩ”

 1. I am sorry for Ato Lemesa and for the rest of the youth who became the victims of Engeener Gizachew’s gang. As the same time, I am dismayed, if the story is true, by City of Addis Ababa police for arresting the wrong people. I hope the police will investigate the matter and bring the culprits to justice.

 2. Amazing news I heared ever before,I ask my self what is going on in Ethiopian politics,There is something wrong that will come out one day.Andinet and Birtukan will live togather along with Ethiopians after all.With out Birtukan,I used say she should be First Lady of Ethiopia.Ethiopia will be one .Thank you Professor and followers,go ahead!

 3. No surprise MEDREK is deploying weyane gangs to arrest
  the loyal UDJ fighters.

  Cos MEDREK was engineered to recycle TPLF by Siye using
  the cum engineer Gizachew.

  Keep on da fight ,bros… u are the real ones

 4. What a shame to see Prof. Mesfin playing a childish game at this adge. He is just helping Weyanne. My God, I’m just lost all the respect I had on him. Shame! Shame! Shame!

 5. I think it high time Engineer Gizachew retired from politics. Whereever he is there is problem.

 6. Eng. Gizachew was a member of EDP, AEUP, Kinijit, UDJ, Medrek and continuing. He should go by all means and retire. The crumbling of kinijit is still going on now UDJ will split. Dear God help us, we can’t take this anymore. They blamed the innocent Lidetu but by God’s grace he came back and they are crumbling by the day fighting each other. “Wei gud zendiro”

 7. Eng. Gizachew is the most dangerous person in Ethiopian politics. He has no ethnic; he is an opportunist. He lies and if he gets a chance I don’t doubt he can beat anyone.

 8. የሚያዝያ 21/2002 የፍርድ ቤት ውሎ
  አንድነት ታፈነ
  መድረክ ግዳይ ጣልኩ አለ ?
  ትላንት በተከሰተው ጉዳይ ላይ የወያኔ ኢህአዴግ ወገኖች የሆኑት እነ ስዬ፤ገብሩ፤ዓንዱዓለም አና የጦረ አበጋዝ የሆኑት ኢንጅነረ ግዛቸው ሰላማዊ የሆኑትን ሰዎች በሏቸው በማለት ካስደበደቡና መኪናቸውንም ካሰበሩ በኋላ እንደገና ባላቸው መስመር በመጠቀም እነሱ ደብድበው ንጹህ፤ አዲስ ተመራጮችና ቢሮ እንዲያስረክቡ ተወክለው የሄዱት ተደብዳቢዎች ወንጀለኞች፤ ሆነው በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር፡፡
  የመድረክ አመራሮች በሰጡት መመርያ መሰረት፤ ክሳቸውን ‹‹ምርጫውን ለማደናቀፍ የተደረገ›› በማለት አቤቱታቸውን አቅርበው ፍርድ ቤቱም የጉዳዩን ከምርጫ ጋር መያያዝ አስመልክቶ ከተመለከተው በኋላ፤ ለሚቀጥለው ሰኞ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የተመረጡት የምክር ቤት አባላትም እስከ ሰኞ በእስር እንዲቆዩ የዋስትና መብትም ተከልክለዋል፡፡
  ፕሮፌሰር መስፍንም ለተከሳሾቹ የዋስትና መብት ለማስፈቀድ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ሳለ፤ በጣቢያው ሃላፊ እሳቸውም ተከሳሸ መሆናቸው ተነግሯቸው ቀና ሹም አጋጥሟቸው በዋስ እንዲሄዱ ቢደረግም፤ ዋስ እስኪደርስላቸው ግን ታግተው ቆይተዋል፡፡ደግነቱ ዋስ ፈጥኖ በመምጣቱ ብዙ አልቆዩም፡፡
  ይህ አካሄድ እንግዲህ ቀደም ብሎ የተካሄደውን ምርጫ ህገ ወጥ ብለው የከፈቱት ክስ ስላልተሳካላቸውና ህጋዊነቱ ስለተረጋገጠባቸው ፕሮፌሰርንና ተመራጮቹን በማሳሰር ስልጣን እንደያዙ ለመክረም ያቀዱት ደባ ነው፡፡
  የመድረክ አመራሮችና ተመራጮች ከተነሳው ጥያቄ ጋር ጨርሶ የማይገናኘውን ክስ በመመስረት ገዢውን ፓርቲ ለማገልገል በገቡት ቃል መሰረት ድርሻቸውን በመወጣት ላይ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የመርህ ይከበር አባላትን ‹‹በወያኔ/ኢህአዴግ የሚደገፉ ናቸው፤ በወያኔ ኢህአዴግ እየተመሩ አንድነተን ለማዳከም የሚንቀሳቀሱ ናቸው ወዘተ…..›› በማለት ሲከሱና ጨርሶ በሃሰተ የተሞላ አሉባልታቸውን በማዛመት በተደጋጋሚ ተጠያቂ ሲያደርጓቸው ቆይተው፤ ትላንት አቡጊዳ ድህረ ገጽ ላይ ባሰፈሩት የተለመደው ቅጥፈትም እንደገና ካፈርኩ አይመልሰኝ እንዲሉ አሁንም በወያኔ/ኢህአዴግ እየተደገፈፉ የሚለውን ዜማቸውን አሰምተዋል፡፡
  ቀደም ሲል የነበረውም የደርግ አስተዳደር እንዲሁ አንዱን ኢህአፓ አንዱን ወያኔ ሌላውን ሻእቢያ እያለ ነበር የሚያስረውና የሚገለው፡፡ኢህአዴግም እንደ አቀባዩ ደርግ ሰውን ለማሰር ሲፈልግ ግለሰቡ ያልደረሰበትን ሁኔታ በላዩ ላይ በመለጠፍ ወንጅሎ ፍርድ ቤት አቅርቦ ያስፈርድበታል፡፡
  አሁንም እየተደረገ ያለው የዚያው ተመሳሳይ ነው፡፡‹‹ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለሁ›› ይሄ ነው፡፡ ከወያኔ/ኢህአዴግ ጉያ ወጥተው በመጡት ሰዎች ይህ ክስ መመስረቱ አላስገረመም፡፡ የመድረክ ባለስልጣናት የአንድነትን ግቢ ከወረሱና ስሙን ሁሉ ለውጠው መድረክ ካደረጉና በየቢሮው ላይ የመድረክ ም/ል…..፤ በሚል ከሞሉት በኋላ የአንድነትን መርህ በመጨፍለቅ የራሳቸውን ተግባራዊ ማድረግ ይዘዋል፡፡
  የአንድነት መሪ የወ/ት ብርቱካን አደራ ተቀብለናል ሲሉና መሪያችን ታስራ ምርጫ ብሎ ነገር አይሞከርም በማለት ሲምሉ ሲገዘቱ የነበሩት ፤ አሥራት የብርቱካንን መፈታት ቅድመ ሁኔታ አናደርግም ሲል ኢንጅነር ግዛቸው በሌላ ጎኑ እናደርጋለን ሲል፤ ከባህር ማዶ እነ አቶ አክሎግ መሪን አሳስሮ ምራጫ አይሞከርም ሲሉ፤ እነግርማ ካሳ እንዴት ተብሎ ብርቱካን ሳትፈታ ምርጫ እንዳላሉ አሁን ጭራሽ ያ ሁሉ ቃል ታጠፈና ጭርሱን የመርህ ይከበር አባላትን እንደምርጫ አደናቃፊ አድርገው ለእርድ ለማቅረብ ማረጃቸውን ሳሉ፡፡በዶሎዶመ እጀ የተሳለ ቢላዎ ግን ስለት እንዲያወጣ ሲታገሉት አራጁን ነው የሚያርደው፡፡
  በሰላ የተንኮል ሴራ ረቅቀው የሰለጠኑት የወያኔ ጀሌዎች ከእንቁላላችን ወጥተናልና የኢትዮጵያ ህዝብ ለይቅርታ መጠየቅ አልበቃም እንዳላሉና እንዳላፌዙ፤የአንድነት ባለአደራዎች አደራቸውን ቅርጥፍጥፍ አድርገው ከበሉ በኋላ ጠቅልለው ለመድረክ አስረክበው እነሱም አንድነትን በመድረክ አስውጠው የመድረክን ካባ ለብሰው ይሄው የጀሌነታቸውን ተልእኮ እየተወጡ ነው፡፡
  በሃገሪቱ ላይ ፍትህ የለም፤ ትግላችን ፍትህ ለማስፈን ነው፤ እያሉ በየቦታው የሚወተውቱት እነዚህ ሰዎች አሁን ደግሞ ሀሳባቸውን ለውጠው ፍትህ አለ በሚል ማረጋገጫ ወያኔ/ኢህአዴግን እየመሰከሩለት ነው፡፡የመርህ ይከበር አባላትም ከእንግዲህ እነሱ በሚያምኑት ፍርድ ቤት ክሳቸውን ቢመሰርቱ ጨርሶ ሊወቀሱ አይገባምና ወደፊት እናያለን፡፡
  ይህ ሁሉ ሲታይና አካሄዳቸው ሲመረመር ታዲያ ማነው ከወያኔ/ኢህአዴግ ጉያ ገብቶ ሕዝብን የከዳ፡፡ መርህ ይከበር ብሎ ለአንድነት ፓረቲ የቆመ፤ ለመሪያችን ራዕይ ተገዢ የሆነ ወይስ ፓርቲውንም መሪያችንንም ክዶ ለራስ ጥቅም የቆመና ለገዢው ፓርቲ አገልጋይ የሆነ?
  ‹‹ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል›› አይነት ይሄው አሁን ቁስላቸው ሲነካና ጠቅላላ ጉባኤው በቃችሁ ሲላቸው ከጅምሩ ‹‹ሴት አትመራንም›› በኋላም ደግሞ ለእስር በተዳረገችበት ወቅት ‹‹የራሷ ጉዳይ ነው፤እንደገባች ትውጣው፤ እኛን አያገባንም›› ባሉበት ወቅት አሁን መርህ ይከበር ያሉት አባላት ነበሩ ‹‹እምቢ ካላችሁንና መግለጫ በፓርቲው ስም ከላወጣችሁ ፔቲሽን አስፈርመን እንፋረዳችኋለን ብሎ የግድ መግለጫ ያሰወጣቸው፡፡ በዚያን ጊዜ ነው የመጀመርያው ቂም በወጣት የመርህ ይከበር ባዮች ላይ መያዝ የተጀመረው፡፡
  አሁን ደግሞ መርሀ ይከበር ብሎ ያደረሱትን ጥፋት ዘርዝሮ ስላወጣባቸውና በርካታ አባላትና የመስራች ጉባኤ አባላት፤ በየክልሉ ያሉ አራሮች ድርጊቱን በማውገዝ ስለሞገቷቸውና ምርጫም ተጠርቶ በቃችሁ በመባላቸው የቀድሞውንም የአሁኑንም ሂደት ለመቀበል ብቃቱ ስለጠፋቸውና ስልጣንንም እንደ ዘልአለማዊ ሹመት ስለሚያስቡት ያለፈ ቁርሸዋቸውን መወጫ አድርገው ወያኔ/ኢህአዴግ በሚቀበለው መልኩ የሃሰት ወንጀል ፈጥረው ‹‹ምርጫን ለማደናቀፍ የሚል ኢህአዴግ ጆሮ ፈጥኖ የሚገባ ክስ መስርተው ንጹኃንን አሣሠሩ፡፡በዚህም መድረክ ግዳይ ጥሎ ጉሮ ወሸባዬ አለ፤ አንድነትም በመድረክ ተውጦ አባላቱ ለእስር ተዳረጉ፡፡
  ታዲያ ከዚህ በመነሳት ሲታይ ማነው ለወያኔ/ኢህአዴግ አገልጋይና ሆኖ የተገኘው? ሕዝብ ሁኔታውን አገናዝቦ ይፈርዳል!!!
  ኢትዮጵያ በነጻነቷ ለዘልአለም ትኑር!!
  መሪያችን ብርቱካን ሚዴቅሳ ትፈታ!!
  በእስር ላይ ያሉት አባልትም
  1.ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በክሱ ላይ ዛሬ የተካተቱና በዋስ የተለቀቁ
  2.ብርሃኑ መሰለ
  3.ስለሺ ፈይሳ
  4.ይልቃል ጌትነት
  5.ለሜሳ በየዬቻ
  6.ልዑል አየሁ ሰላም
  7.ዓለማየሁ በቀለ
  8.እንደሻው እምሻው
  9.ደርቤ አስራት
  10.ሃብታሙ ደመቀ
  11.አንተነህ ማስረሻ
  12.ታምራት ታረቀኝ ናቸው፡፡

 9. Engineer Gizachew is the most dangerous man in the world. He never hesitate to kill people to hang on Power.

  I know him for a longtime, he is very dangerous man

 10. All of you who hae posted the aboe comments are criminals who are running from one corner to another corner to support ethiopia’s canncerious enemy weyanes and full your bloody and big belly. eng gezachew is the most modern democrate in the current politics aganist the firegn agents.

 11. All what is being heard is not a failure or blame for a single party or entity.In my view it is a generational failure for we all Ethiopians.It is a disgraceful moment and time for Ethiopia and Ethiopians in history.Surprisingly i do not have any trust on any party,except Almighty God.In a country and society where the slightest political civility(even the Ethioan civility) is absent,i do not see any good futurity or hope out of this bizzare.
  Rather than talking about such non-sense election or democracy why not we pray for God to bring something good for this poor country and people.
  For me, as Ethiopians we have all failed.And hence it is better to do our other prelimenary homeworks than badly playing with such stupid political election.
  Let Almighty God protect this poor country and its people.
  Only innocent and sincere Ethiopians who love their country,with the help of Almighty God, will save this country from failure,not selfish and short-sighted politicians.
  God knows all what is good for this country and will appoint someone destined to save this country from chaos.
  Ethiopia is a blessed country where the name of Almighty God is blessed 24 hours a day and seven days a week,and hence shall not bee simply abandoned in to chaos.God will protect Ethiopia for the sake of his own name and his poor peoples who have a deeper faith in him,not for the sake of selfish and secular politicians.

  Let God Bless Ethiopia and its Peoples

 12. It all a failure as Ethiopians
  Generational Failure in general.
  We all failed as Ethiopians.
  Let God bless and protect Ethiopia and its Peoples.

Comments are closed