ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል
ላለፉት አስራ ስምንት ወራት በእስር ላይ የቆዩት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ዛሬ ያስተላልፉታል ተብሎ በሚጠበቀው ውሳኔ ወ/ት ብርቱካን ከእስር ይፈታሉ፡፡ ወ/ት ብርቱካን ከእስር የሚፈቱት በአደራዳሪ ሽማግሌዎች አማካኝነት ይሁን ወይም ራሳቸው በጠየቁት ይቅርታ አማካኝነት እስካሁን የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡ በጉዳዩ ላይ መንግሥት ዛሬ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡