Logo

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ማኔጅሜንት ለፈረንሳይ ኩባንያ መሰጠቱ ታወቀ

Ethiopian-Telecommunications-Corporation-logo
December 2, 2010

በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት የተጀመረው ይኸው የስልክ አገልግሎት፣ በወቅቱ በነበሩ መኳንንት “ሰይጣን ነው” በሚል ምክንያት ሥራ ላይ ለማዋል አስቸጋሪ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ንጉሱ በወሰዱት አቋም አግልግሎቱ ቀጥሎ፣ በ1900 ዓ.ም ከተቋቋሙት አስራ ሁለት የሚንስቴር መስሪያ ቤቶች አንዱ በሆነው የፖስታና ቴሌኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር እንዲመራ ተደርጓል፡፡

በዚህ መልኩ ከዛሬ አንድ መቶ ዓመታት በፊት የተጀመረው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከምኒልክ በኋላ በመጡ መንግስታት በተለያዩ አስተዳደራዊ አደረጃጀቶች ሲመራ ቆይቶ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ በኮርፖሬሽን ደረጃ እንዲዋቀር ተደርጓል፡፡

ይሁን እንጂ፣ እስከ አሁን ድረስ እየፈረሰ መገንባቱ ያላቋረጠውና በአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን፣ ከህዳር 20 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ የስም ለውጥ ማድረጉንና ማኔጅሜንቱም ለአንድ የፈረንሳይ ኩባንያ መሰጠቱን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው ዜና አመልክቷል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔና ባወጣው ደንብ መሰረት፣ ቀደም ሲል “የኢትዮጵያ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን” ሲባል የነበረው መንግስታዊ ድርጅት “ኢትዮ ቴሌኮም” በሚል ስያሜ ለቀጣይ አራት ዓመታት በፈረንሳይ የቴሌኮም ኩባንያ እንደሚተዳደር ታውቋል።
ይህ የአደረጃጀት ለውጥ “ግልጽነት የጎደለው ነው” የሚል ትችት በኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች እየቀረበበት ሲሆን፤ የማኔጅመንት ኮንትራቱን የተረከበው የፈረንሳይ ኩባንያ በበኩሉ ቴሌ አሁን ያለውን የሰው ኃይል በአንድ ሶስተኛ የሚቀንስ መሆኑም እየተነገረ ነው። ይህ ሁኔታ ደግሞ ሰራተኞቹ ከስራ ገበታችን ላይ እንፈናቀላለን የሚል ስጋት ፈጥሯል ተብሏል።

እንደተባለው የፈረንሳዩ ኩባንያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ከስራ የሚያፈናቅል ከሆነና እያንዳንዱ ሰራተኛ በአማካይ አምስት ቤተሰቦች ቢኖሩት፣ በድምሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የርሃብ አደጋ ላይ እንደሚወድቁና እየተባባሰ ከመጣው የኑሮ ውድነት ጋር ሲደመር ሊፈጠር የሚችለው ማህበራዊ ቀውስ በቀላሉ እንደማይታይ አስተያየት ሰጪዎች ግምታቸውን ገልጸዋል።

በኢህአዴግ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት በየጊዜው በመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ እየወሰደ ባለው የመዋቅር ማሻሻያ ምክንያት በርካታ ዜጎች ከስራ ገበታቸው ላይ ሲፈናቀሉ እንደነበርና ላለፉት ሃያ ዓመታት ከስጋት ነፃ የሆኑበት ወቅት እንዳልነበር ዘገባው አስታውሶ፣ በቴሌ ላይ እየተወሰደ ያለውም እርምጃ የዚሁ ቀጣይ ክፍል ነው ሲል ጨምሮ ገልጿል።

በተያያዘ ዜና፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ረገድ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች እንደሚሉት ከሆነ፤ መንግስት አንዳንድ የውጭ ሀገራት ኩባንያዎችን ለተለያዩ ዘርፎች የመደልደል አቅጣጫን እየተከተለ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ በዚህም መሰረት፤

•    የቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽንን ለፈረንሳይ ኩባንያ፣
•    መብራት ኃይልን ለጣሊያን ኩባንያ፣
•    የመንገድ ልማትን ለቻይና ኩባንያ፣
•    ነባር የባቡር ሐዲድ ጥገናን ለጣሊያን ኩባንያ፣
•    አዲስ የባቡር ሐዲድ ዝርጋታን ለህንድ ኩባንያ፣
•    የመስኖ ልማትን ለሳዑዲ ዓረቢያ ኩባንያ፣
•    ውሃን ለእንግሊዝ ኩባንያዎች፣
•    ትልልቅ ድልድዮችን ለጃፓን ኩባንያ፣

ሰጥቷል በማለት ያስረዳሉ። እንዲህ ዓይነቱ አሰራር ደግሞ ከንግድ ህግጋትና ከመንግስት የግዥ ስርዓት አሰራር ውጪ የሆነና ለሙስና የተጋለጠ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎቹ ጨምረው ገልጸዋል።

Share

6 comments on “የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ማኔጅሜንት ለፈረንሳይ ኩባንያ መሰጠቱ ታወቀ

  1. The fall of the Tele management to the French may herald a some form of new indepndence from the regime’s undue pressure. Tele might benefit from the French Orange telephone giant company in the long run.

  2. Adios Ethiopianisation! Then again we do not expect anything Ethiopian from this government. Woy mekatel!.

  3. The take over of ETC managemenet by France telecom is a good news. You guys have to think clearly. Etc has been fastly expanding its services around ethiopia and the management was not able to coup up with the expanstion and provide good services to the people. I am hoping the france telecom will greatly improve the service and teach the us how to do it. Another great decisson by the government of ethiopia.
    I have a comment on the write of this news, I am sure you are not professional journalist. you are just giving us your opinion. This is not a news. Try to do a balanced news in the future.

  4. To kebed,

    If ETC can’t provide good services, why not it is privatized? The other thing is, unless one begins being amature, he will not be professional. Try to think twice kebed!

  5. ETC had been lagging behind and it is not a bad idea that the management has been outsourced to Orange. I am sure Orange would inject new management techniques to drag the ETC in to narrow the digital divide. Ethiopia can not afford to miss this digital revolution.

Comments are closed