Logo

ከጋዜጦች ዘገባ በጥቂቱ

January 5, 2011

በግንቦት ወር 2002 ዓ.ም በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ከቦንጋ ወረዳ አሸንፈው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው የተመረጡት የግል ተወዳዳሪው ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የእስከ አሁኑ የፓርላማ ቆይታቸው እንደተመቻቸው ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ በሰጡት ሰፊ ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።

“አሁን ያለው ፓርላማ አስቀድሞ ከነበሩት በብዙ ለውጥና መሻሻል በዳበረ ደረጃ ላይ ነው። እንደ ዱሮው ሰዓት ሳይገደብ፣ አምስት ደቂቃ ምናምን ሳይባል የፈለግነውን ያህል ሰዓት ወስደን የምንናገርበት መድረክ ሆኗል። እያንዳንዱ የፓርላማ አባል በሚያቀርባቸው ጥያቄዎችና ሃሳቦች ለውይይት ሁሉንም መጋበዝ የሚችልበት ስርዓት ሰፍኖበታል። የገዢው ፓርቲ አባላትም ቢሆኑ ብዙውን ጊዜ ሲወያዩና ሲመካከሩ በነፃነት እንደሆነ ታዝቢያለሁ” ያሉት ዶ/ር አሸብር፣ በቴሌቪዥን የሚቀርበው ግን ሁሉንም የስብሰባ ሂደት አያሳይም ቢሉም እውነታው ከዚህ የተለየ መሆኑን የሚገነዘቡ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች የዶ/ር አሸብርን ቃለ ምልልስ “አስተዛዛቢ” ብለውታል።

ሳምንታዊው መሰናዘሪያ ጋዜጣ ደግሞ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝዳንት ከሆኑት ከአቶ ልደቱ አያሌው ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። አቶ ልደቱ ለመሰናዘሪያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ ስለ ንግዱ ማህበረሰብ፣ ስለ ኑሮ ውድነት፣ ስለ መንግስት ሰራተኛው የደመወዝ ጭማሪ አስፈላጊነት፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እርሳቸውን አስመልክቶ በቅርቡ ስለሰጡት አስተያየትና ስለመሳሰሉት ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

“ህብረተሰቡ ተስፋ መቁረጥን እንደ አማራጭ አድርጎ ማየት የለበትም” ያሉት አቶ ልደቱ አያሌው፣ የኢዴፓ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔ መጋቢት 11 ቀን 2003 ዓ.ም እንደሚካሄድና እርሳቸውም የፓርቲ ስልጣናቸውን በዚያው ጉባዔ ላይ እንደሚያስረክቡ መግለጻቸውን የመሰናዘሪያ ጋዜጣ በቃለ ምልልስ ዓምዱ አስነብቧል።

የአደጋ ዘገባዎች፤
በሳምንት ሁለት ጊዜ ረቡዕ እና እሑድ የሚታተመው አንጋፋው ሪፖርተር ጋዜጣ ሶስት የአደጋ ዜናዎችን አስነብቧል። በዚሁ መሰረት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከቡርኪናፋሶ ዋና ከተማ ከኡጋዱጉ ወደ አዲስ አበባ ተሳፍረውበት የነበረው አውሮፕላን አደጋ ገጥሞት እንደነበር ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ታኅሣሥ 10 ቀን 2003 ዓ.ም. የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ብሌስ ኮምፓኦሬ ባደረጉት በዓለ ሲመት ላይ መገኘታቸውን ሪፖርተር ጠቅሶ፤ የሁለት ቀናት ቆይታ አድርገው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላን የፊት ለፊት መስታወት ሙሉ ለሙሉ በመሰነጣጠቁና ይህም ለጉዞው አደገኛ በመሆኑ፣ አውሮፕላኑ ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ ተመልሶ አርፏል ብሏል ሪፖርተር በዘገባው፡፡

አውሮፕላኑ በ8000 ጫማ ላይ ይበር የነበረ በመሆኑ አደጋ ሳይገጥመው በሰላም ማረፍ ችሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም አውሮፕላኑ እንዳረፈ ወርደው ወደ ኡጋዱጉ ሒልተን ሆቴል ማምራታቸውንና ከስድስት ሰዓታት ቆይታ በኋላ በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የነበረ ሌላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 የመንገደኞች አውሮፕላን ጠቅላይ ሚኒስትሩን አሳፍሮ ወደ አዲስ አበባ መመለሱን ሪፖርተር ዘግቧል።

በሌላ ዜና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱ ቦይንግ 777 በኤምሬትስ አውሮፕላን የተገጨ መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል። “ብሉ ናይል” የተባለው ይኸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ የገዛው አውሮፕላን በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በቆመበት፣ በኤሜሬትስ አየር መንገድ መገጨቱ ታውቋል፡፡ የኤሜሬትስ ኤርባስ A340 አውሮፕላን ከዱባይ ተነስቶ አዲስ አበባ ካረፈ በኋላ ወደ ኢንቴቤ ለመሄድ በሚያኮበኩብበት ወቅት፣ ቆሞ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777 አውሮፕላንን ገጭቶታል ብሏል ሪፖርተር፡፡

ሪፖርተር በሌላ ዘገባው ደግሞ የኢንጂነር ኃይሉ ሻውል የመጀመሪያ ልጅ ዶ/ር ሻውል ኃይሉ ከፍተኛ የመኪና አደጋ የደረሰባቸው መሆኑን አስነብቧል፡፡ ዶ/ር ሻውል አደጋው የደረሰባቸው በቅሎ ቤት አካባቢ የሚገኘው ዳሸን ባንክ ፊት ለፊት መኪናቸውን አቁመው ወደ ባንኩ ለመግባት ከመኪናቸው ሊወርዱ ሲሉ፣ ከመሿለኪያ ወደ ሳሪስ የሚጓዝ አውቶቡስ ገጭቷቸው መሆኑን ሪፖርተር በረቡ እለት እትሙ አስነብቧል፡፡

ሰንደቅ ጋዜጣ በበኩሉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየም ሊግ ክለቦች አባል የሆነው የአዳማ ከነማ የእግር ኳስ ቡድን አባላት ትግራይ ላይ ተጫውተው ሲመለሱ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ለሞትና ለከፋ የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን በስፖርት ዓምዱ አስነብቧል።

ሕግ ነክ ዘገባዎች፤

“ጌቱ ገለቴን ከወንጀል ክስ አለአግባብ ነፃ አድርገዋል የተባሉ ዳኛ ከስራቸው ተሰናበቱ” በማለት የዘገበው ደግሞ ሰንደቅ ጋዜጣ ነው። እንደ ሰንደቅ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ፣ ጌትአስ ኢንተርናሽናል የተባለ ኩባንያ ባለቤት የሆኑት አቶ ጌቱ ገለቴ የተባሉ ታዋቂ ባለሀብት ከቀረበባቸው የወንጅል ክስ በፍርድ ቤት በነፃ ያሰናበቷቸው ዳኛ የመንግስትን ፍላጎት ስላላሟሉ ከዳኝነት ስራቸው እንዲነሱ ተደርጓል ተብሏል። ይህም እርምጃ የፍትህ ስርዓቱ ገለልተኛ ሆኖ ስራውን እንዳይሰራ የሚያሸማቅቅ እርምጃ መሆኑን ጋዜጣው በዜና ዘገባው ላይ አትቷል።

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ባወጣው ሌላ ህግ ነክ ዘገባው ደግሞ፣ “ባለቤቱ ፊት ላይ አሲድ የደፋ ግለሰብ በሁለት ዓመት ከአስር ወር እስራት እንዲቀጣ የተፈረደበት መሆኑን አስነብቧል። የችሎቱ ታዳሚዎች ይህ ቅጣት በቂ አደለም የሚል አስተያየት መስጠታቸውን አዲስ አድማስ ገልፆ፣ አሲዱ የተደፋባት ግለሰብ ግን በአካሏ ላይ የደረሰውን ጉዳት ከምንም ባለመቁጠር ጉዳት ያደረባት ባሏ በነፃ እንዲለቀቅ ፍላጎት እንዳላት ጋዜጣው ጨምሮ ገልጿል።

Share

7 comments on “ከጋዜጦች ዘገባ በጥቂቱ

  1. በትግራይ ውስጥ ያለነው ፀሓፊዎች በደል እየደረሰብን ነው ይህም ማለት ፀሓፊ ሁነን የሰራነው ስራ ልምዳችን 25 ዓመት በላይና ትምህርታችን ዲግሪ ይዘን ኣንድ ባለስልጣን ለፀሓፊዎች ያወጣውን ሴርኩላር እንዲስተካከልልን ያለንን ፀሓፊዎች ፊርማ በማሰባሰብና በተናጠልም ቢሆን በየ መ/ቤታችን ቅሬታችን ስንገልፅ ቆይተናል ይህም ሰሚ ኣጥተናል ምክንያቱ ኣንድ ባለስልጣን የፀፈው ፅሑፍ ከማስተካከል ለእኛ መበደል መርጠዋል ስለዚህ ይህን ጉዳይ ለፊደራልን ሲቪል ሰርቪስና ጠ/ሚኒስቴር በትግራይ ያለውን የፀሓፊዎች የወጣውን ጠይቓችሁ ይህን እንዲስተካከልንን ኣደራ ጭምር ነው

  2. i am sorry, asid yedefabaten balwa keser yelekek yalechew sate atrebam becouse she dosn’t have confidunce.

  3. asid yedefabaten balwan keser yilikeke yalechew tikike nech mikiniyatum higu astemari silalhone beyanis lijochu siyadigu yiweqsutala yenesu kitat yibeltal higu waga yelewim elalehu bene emenet

Comments are closed