የሰሞኑ የገበያ ውዥንብር
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ታኅሣሥ 28 ቀን 2003 ዓ.ም. በአገሪቷ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ናቸው የተባሉ 584 ነጋዴዎችን በጽሕፈት ቤታቸው አነጋግረዋቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለኅብረተሰቡ በጣም አስፈላጊ ነው ያሏቸውን 16 ምርቶች የሚሸጡባቸውን ዋጋ ለነጋዴዎቹ አሳውቀዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የዱቄት ወተት (450 ግራም) ቀድሞ ከሚሸጥበት 180 ብር፣ ቫትን ጨምሮ በ72.50 ብር እንዲሸጥ የዋጋ ጣሪያ ወጥቶለታል፡፡ በመሆኑም የዱቄት ወተት በ148.28 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ ይሁን እንጂ አስመጪዎች ለዱቄት ወተቱ የወጣው የዋጋ ጣሪያ ሁሉንም የዱቄት ወተቶች በአንድ ላይ የጨፈለቀ ነው ሲሉም ይደመጣሉ፡፡ አሁን እየሸጡ ያሉትም መንግሥትን ብቻ በመፍራት በኪሳራ መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ