የቤይሩት አውሮፕላን አደጋ ሪፖርት ይፋ ሊደረግ ነው
– መርማሪ ቡድኑ አዲስ አበባ ሊመጣ ነው– የሊባኖስ ባለሥልጣናት የተጠየቁትን መረጃዎች አልሰጡም
በቃለየሱስ በቀለ
ባለፈው ዓመት ጥር ወር ከቤይሩት ወደ አዲስ አበባ 82 መንገደኞችን አሳፍሮ በረራ ሲጀምር በሜዲትራኒያን ባሕር ላይ ድንገተኛ አደጋ በደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ላይ በመካሄድ ላይ ያለው ምርመራ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ጥር 17 ቀን 2003 ዓ.ም. ይፋ ይደረጋል፡፡