የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የወንጀል ምርመራ ኃላፊዎች ታስረው ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ትእዛዝ ተሰጠ
በታምሩ ጽጌየኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፣ የእስረኞችና ሰነዶች ክትትል ኃላፊና የወንጀል ምርመራ ቡድን አስተባባሪ በተከሰሱበት የፍርድ ቤት ትእዛዝ አለማክበር ወንጀል ጥፋተኛ በመባላቸው፣ ከጥር 5 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ታስረው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡