Logo

ሚኒስቴሩ የዋጋ ቁጥጥር የሚደረግባቸው መሠረታዊ የንግድ ዕቃዎች የጅምላና የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ አወጣ

January 17, 2011

በመሆኑም ከጥር 9 ቀን 2003 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የጅምላ መሸጫ ዋጋና የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከለሳ ተደርጎባቸዋል።

በዚሁ መሠረት አንደኛ ደረጃ ስንዴ ዱቄት ባለ50 ኪሎ ግራም ጅምላ 363ብር 65ሣንቲም፣ በችርቻሮ 378ብር 20 ሣንቲም፣ባለ 25 ኪሎ ግራም በጅምላ 183 ብር፣በችርቻሮ 190 ከ25 ሣንቲም፣ባለ 10 ኪሎ ግራም በጅምላ 74 ብር ከ40 ሣንቲም፣ በችርቻሮ 77 ብር ሲሆን፣ ባለ አምስት ኪሎ ግራም በጅምላ 38 ብር፣በችርቻሮ 39 ብር ከ45 ሣንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።

የአገር ውስጥ ፓስታና ማካሮኒ ቬራ 500 ግራም በጀምላ 8ብርከ50 ሣንቲም ሲሆን በችርቻሮ ዘጠኝ ብር፣ ሌሎች የፓስታ ዓይነቶች 500 ግራም በጅምላ7 ብር ከ25 ሣንቲም፣ በችርቻሮ 7ብር ከ75ሣንቲም፣ ቬራ ማካሮኒ በኪሎ ግራም በጅምላ 12 ብር፣ በችርቻሮ 13ብር፣ የታሸገ ማካሮኒ 500 ግራም በጅምላ 6ብር ከ25 ሣንቲም፣ በችርቻሮ 6ብር 75 ሲሆን፣ ሌሎች ያልታሸጉ የማካሮኒ ዓይነቶች በኪሎ ግራም በጅምላ 11ብር ከ20 ሣንቲም ፣በችርቻሮ 12 ብር እንዲሸጥ መወሰኑን ገልጿል።

በተጨማሪም ዳቦ (ኖርማል) ባለ91 ግራም በችርቻሮ አንድ ብር፣ ባለ 182 ግራም በችርቻሮ ሁለት ብር ሲሆን፣ባለ 350 ግራም በችርቻሮ 3ብር ከ85 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።

የአገር ውስጥ የልብስ ሣሙና ባለ 100 ግራም በነጠላ በጅምላ 2 ብር ከ70 ሣንቲም፣ በችርቻሮ 2ብር ከ80 ሣንቲም ሲሆን፣ ባለ 250 ግራም በጅምላ 6ብር ከ80 ሣንቲም፣ በነጠላ ሰባት ብር እንዲሸጥ ሆኗል።

የአገር ውስጥ የዱቄት /ዲተርጀንት/ ሣሙና ባለ30 ግራም በጅምላ አንዱ 85 ሣንቲም፣በችርቻሮ አንዱ 90 ሣንቲም ሲሆን፣ ባለ አምስት ሺህ ግራም በጅምላ አንዱ 144 ብር ከ20 ሣንቲም ሲሸጥ በጅምላ አንዱ 150 ብር እንዲሸጥ ተወስኗል።

የውጭ አገር የልብስ ሣሙና ባለ 250 ግራም በጅምላ አንዱ 6 ብር ከ80 ሣንቲም ሲሆን፣ በችርቻሮ 7ብር ከአምስት ሣንቲም፣ ባለ115 ግራም በጅምላ አንዱ 3ብር ከ10 ሣንቲም በችርቻሮ 3ብር ከ25 ሣንቲም ሲሆን፣ የውጭ አገር የዱቄት ሣሙና ባለ200 ግራም በፓኬት የታሸገ በጅምላ አንዱ 5 ብር ከ80 ሣንቲም፣ በችርቻሮ 6ብር ሆኗል።ባለ30 ግራም በፕላስቲክ የታሸገ በጅምላ አንዱ 1ብር ከ20 ሣንቲም፣ በችርቻሮ 1ብር ከ25 ሣንቲም እንዲሸጥ ዋጋ ወጥቶለታል።

የአዋቂ ዱቄት ወተቶች ኒዶ ባለ 400ግራም በጅምላ 61 ብር ከ80 ሣንቲም፣ በችርቻሮ 64 ብር 30 ሣንቲም ፣ የሕጻናት ዱቄት ወተት ኤስ 26 ጎልድ ባለ 400 ግራም በጅምላ አንዱ 114 ብር ከሁለት ሣንቲም፣በችርቻሮ አንዱ 118 ብር ከ60 ሣንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።

የፓልም ዘይት ባለ25 ሊትር በጀሪካን በጅምላ 505 ብር፣ በችርቻሮ 525 ብር ሲሆን፣ ባለ 20 ሊትር በጀሪካን በጅምላ 417 ብር በችርቻሮ 432ብር፣ ባለ 10 ሊትር በጀሪካን በጅምላ 213 ብር በችርቻሮ 221 ብር ከ50 ሣንቲም፣ ባለ እምስት ሊትር በጀሪካን በጅምላ 111 ብር በችርቻሮ 115 ብር፣ ባለ 3 ሊትር በጀሪካን በጅምላ 68 ብር ከ50 ሣንቲም፣ በችርቻሮ 71 ብር ከ25 ሣንቲም ሆኗል። ባለ አንድ ሊትር በጀሪካን በጅምላ 23 ብር ከ60 ሣንቲም፣ በችርቻሮ 24 ብር ከ50 ሣንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።

በዚህ ውስጥ ያልተገለፁ ሌሎች ምርቶችን ዋጋ በቅርብ ጊዜ እንደሚያሳውቅም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የቢራና የለስላሳ መጠጦችን አስመልክቶ ቀደም ሲል የወጣው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለ ኮከብ ሆቴሎችን፣ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን(ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ሎጆችና የባህል ምግብ ቤቶችን)እንደማይመለከት ገልጿል።

ዋጋው በክልል ከተሞች ተፈጻሚ የሚሆነው የጅምላ መሸጫ ዋጋ መነሻ በማድረግ ከአዲስ አበባ ወደ ሌሎች ከተሞች የሚሰራጩ የንግድ ዕቃዎች ዋጋ የትራንስፖርት፣የመጫኛና ማውረጃ ወጪዎችንና ሌሎች በሕግ ተቀባይነት ያላቸው ክፍያዎችን በማካተት እንደሚሰላም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ከአዲስ አበባ ወደ ክልሎች በማይጓጉዙ ዕቃዎች ላይ እንደ ክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታ የሚወሰኑ ሆኖ፤ የዋጋ ተመኑ ከመደረጉ በፊት የነበረ የመሸጫ ዋጋ አሁን ከተተመነው መብለጥ እንደሌለበትም መግለጫውን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

 

– ኢዜአ –

Share