Logo

እነ ፕ/ር መስፍን ይቅርታ እንዲጠይቁና የአንድነት ፓርቲ ‘ተራ አባል’ ሆነው እንዲቀጥሉ ሃሳብ መቅረቡ ታወቀ

January 23, 2011

የእነ ፕሮፌሰር መስፍን ቡድን በዚህ ሳይወሰን “የፓርቲው ህጋዊ ባለቤቶች እኛ ስለሆንን የፓርቲውን ንብረትና ጽ/ቤት አስረክቡን” የሚል አታካሮ በመፍጠር በፓርቲው ላይ የተጋረጠውን አደጋ ወደተወሳሰበና ደም አፋሳሽ ሁኔታ ያሸጋገረው መሆኑም ይታወሳል።

በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የተቀሰቀሰው ሁኔታ በዚህ ደረጃ ላይ እንዳለ ወ/ሪት ብርቱካን ከእስር በመፈታታቸው የሁለቱ ባላንጣ ቡድኖች አመራር አባላት በወ/ሪት ብርቱካን መኖሪያ ቤት በድንገት በተገናኙበት ወቅት ሰላምታ ከመለዋወጥ ጀምሮ መልካም ሁኔታን በማሳየታቸው፣ ሁለቱን ቡድኖች የማስታረቅ ሃሳብ መጸነሱን የኢትዮ-ፋክት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ የላከው መረጃ አመልክቷል።

በዚሁ መሰረት፣ በኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የሚመራው የአንድነት ፓርቲ አመራር አካል ሰሞኑን ባደረገው ስብሰባ ‘መርህ ይከበር’ በሚለው ቡድን ዙሪያ ውይይት ያደረገ ሲሆን፤ ይህንን ጉዳይ አጥንቶ የመነሻ ሃሳብ እንዲያቀርብ የተቋቋመ ኮሚቴ ያቀረበለትን አንድ “የማስማሚያ” ሰነድ በዝርዝር መመልከቱ ታውቋል።

ይህንኑ “የማስማሚያ” ሰነድ አዘጋጅቶ ያቀረበው ቡድን አባላት ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ አቶ አስራት ጣሴ እና አቶ ንጉሴ ነውጤን ያካተተ እንደነበር የሪፖርተራችን ዘገባ አመልክቶ፤ በዚህ ሰነድ ላይ ከተጠቀሱት ዋና ዋና ነጥቦች ውስጥ “የመርህ ይከበር አባላት ፓርቲው ከዚህ በፊት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ሙሉ በሙሉ ይቀበሉ፣ በዲስፕሊን ተቀጥተው ስለነበር ይቅርታ ይጠይቁ፣ ወደ ፓርቲው ሲመለሱ ተራ አባል ሆነው ይቀጥሉ፣…” የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው ብሏል። በነዚህ ነጥቦች ላይ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት የተከፋፈለ አቋም ይዞ የተካረረ ሙግት ቢያካሂድም መጨረሻ ላይ ሰነዱ በብዙሃኑ አመራር ተቀባይነት ያገኘ መሆኑ ታውቋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ኢትዮ-ቻናል የተሰኘ ጋዜጣ ባቀረበው ዘገባ “በሰነዱ ላይ የተገለጸውን በሙሉ ሃያ ሁለቱም ‘የመርህ ይከበር’ አባላት የግድ መቀበል አለባቸው። በሰነዱ ላይ መፈረምም አለባቸው ወይም በሶስት ወኪሎቻቸው አማካይነት ሰነዱን መቀበላቸውን ማረጋገጥ አለባቸው” ብሏል። ከሃያ ሁለቱ ‘የመርህ ይከበር’ አባላት ውስጥ የአቶ ታምራት ታረቀኝ ጉዳይ “ከሌሎቹ ጋር አንድ ላይ መታየት የለበትም” የሚል ውሳኔ መተላለፉንም ጋዜጣው ጨምሮ ገልጿል።

የመርህ ይከበር አባላት በበኩላቸው በፕ/ር መስፍን መኖሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ መክረው “እነ ኢ/ር ግዛቸው የተጀመረውን ውይይት ለማደናቀፍ እየሞከሩ በመሆናቸው ስለመስማማታችን ስጋት አለን” የሚል አቋም ላይ መድረሳቸውን ኢትዮ ቻናል ጨምሮ ገልጿል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው “የአንድነት ፓርቲ አመራር ከመርህ ይከበር አባላት ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ሰነድ እስከማዘጋጀት የደረሰ ስራ ያከናወነው ከእስር የተፈቱት ፕሬዝዳንቷ ወ/ሪት ብርቱካንን ‘ይኸው ፓርቲው ሰላም ሰፍኖበታል። ይምጡና ይምሩን’ የሚል ማባበያ ለማቅረብ የታለመ ይመስለኛል” ሲሉ አዲስ አበባ ለሚገኘው የኢትዮ-ፋክት ዘጋቢ ገልጸዋል።

በሌላ ዜና፣ አንድነት ፓርቲ በአቶ ሙላት ጣሰው ከሚመራው ከብርሃን ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ እተደራደረ ነው ተብሏል። አንድነት የውስጥ ችግሩን ሳይፈታና የፕሬዝዳንቷን የወ/ሪት ብርቱካንን ወደ ፓርቲው የመመለስ ጉዳይ እልባት ሳያበጅ ከብርሃንና ከመኢአድ ጋር ውህደት ለመፍጠር የሚያደርገው መጣደፍ የፓርቲውን ችግር ወደ ባሰ ውስብስብነት ከማሸጋገር የዘለለ ጥንካሬን ሊያመጣለት እንደማይችልም አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

Share

5 comments on “እነ ፕ/ር መስፍን ይቅርታ እንዲጠይቁና የአንድነት ፓርቲ ‘ተራ አባል’ ሆነው እንዲቀጥሉ ሃሳብ መቅረቡ ታወቀ

 1. thank you Andinet for your effortless and non enging entertainment like ETV’s Ihud meznagna. I am enjoying you all. Ethio-fact ant Ethio Channel seem to be jelous of Andinet’s entertaining shows, Why?

 2. I doubt Burtukan will resume politcal activity especially in such messy situation that udj is in. But let them keep praying.

 3. ፕሮፌሰር መስፍን ለብርቱካን እንደነፍስ አባት ናቸው። መካሪዋና አማካሪዋ ናቸው። የኢር ግዛቸው እንቅስቃሴ እስከዛሬ ድረስ እስር ቤት በመሆኗ ዝናዋ ለጥማታቸው (ambition) እንቅፋት እየሆነ ያስቸገራቸውን ሁለት ወፍ በአንድ ባላ ለመምታት የተዘጋጁ ይመስላሉ።
  ታዲያ ጥያቄው ብርቱካን ምን ምርጫ አላት፤ ካላትም ምርጫዎች የትኛውን ታነሳለች? ነው። በዶር ብርሃኑና ባቶ ልደቱ፣ በዶር ብርሃኑና በኢር ሃይሉ መሃከል በነበረው ሽኩቻ ወድዳውም ይሁን ምርጫ ሳይኖራት ዶር ብርሃኑ ብርቱካንን በተሳካ ሁኔታ መጠቀሚያ እንዳደረጋት የታወቀ ነው። በወቅቱ ብርቱካን የነበራት የፖሊቲካ ሰውነት ክብደት ስላልነበረው፣ እንደ ዶር ብርሃኑ የመሳሰለ ጠንከር ያለ የፖሊቲካ ማዕበል ይዞ የሚመጣን ሰው መንገድ ላይ መቆምና መቋቋም ስለማትችል ከማዕበሉ ጋር አብራ ለመሄድ ተገድዳ ሊሆን ይችላል።
  አሁንስ ጥንካሬው አላት ወይ? ካላትስ ያንን ጥንካሬ ለመጠቀም ድፍረቱን ተለማምዳለች ወይ? እነዚህን ጥያቄዎች እንግዲህ በቅርብ ጊዜ ሲመለሱ አናያቸዋለን።

  ከዚያ በፊት ግን እኛ ሊሆን ይችላል ወይም አይችልም የምንለውን መላ መምታት ትክክል ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በመነሳት የሚቀጥለውን መላ መታሁ።

  ከእስር ቤት ከወጣች በኋላ ሁኔታዎችን እንዲያስተካክሉላት እጇን ለማስገባት ባለመፈለጉዋ ምን አልባት እነ ኢር ግዛቸውን የበለጠ አጠናክራቸው ይሆናልም። ብዙ ጊዜ ያስተዋልነው ነገር የተቃዋሚው አባላት ከገዥው ፓርቲ ጋር ይልቅ ከሌላው ተቃዋሚ ጋር በሚያደርጉት ፍጥቻ ከፍተኛ ጭካኔን ያሳያሉ። ገዢው ፓርቲ ላይ የሚሰነዝሯቸው ቃላት በአብዛኛው የማሻሸት ዓይነት ሲሆን የተቃዋሚውን አባል ግን በጥርሳቸው ይገቡበታል። በተለይ የተወሰኑቱ ስልጣን ለኔ ይገባኛል የሚል ከፍተኛ እምነት ያላቸው (እንደ ስህተት አልቆጥረውም) የሚጠቀሟቸው ዘዴዎች ግብረገባዊነት የጎደላቸው እንደሆኑ አይተናል። በተለይ ስምን በሃሰት ማጥፋት ብዙም ወጪና ጊዜ ሳይጠይቃቸው ጠላታቸውን ከመንገዳቸው ላይ እንደሚጠርግልቸው ስላወቁ በሚገባ፣ ህሊናቸውን ሳይቆረቁራቸው ይጠቀሙበታል። ክፋቱ ታዲያ ይህ ብዙ ወጭ የማያስወጣ ርካሽ መርዝ የኅብረተሰብን መተማመን፣ ክብር፣ እውነትን አልፎ ተርፎም ወኔን አብሮ ስለሚገል ለትግሉ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ከቅንጅት ያየነው ነው።
  በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ ጨዋታ ያልተካኑት ወይ ሲሞክሩ እንዳልሆነ ይሆንና የባሰ ያስገምታቸዋል (ልደቱ አያሌውን ይመለከቷል) ወይም ህሊናቸው ስለማይፈቅድ ግራ ገብቷቸው አንድ ቦታ እየተሽመደመዱ እንዲቆሙ ያደርጋቸዋል (የብርቱካን እጣ ፈንታ ምን ዓልባት)። ወይም ደግሞ እንደ ፕሮፌሰር መስፍን አይሞቱ አያድጉ ሙጭኝ ብለው አስርት አመታትን በዙሪያቸው አንዱ ሲነሳ አንዱ ሲወድቅ ለተዓምር ያስቀምጣቸዋል።
  የብርቱካን ጎዳና የቱ ይሆን? እንደ ልደቱ እልህ ገብታ ትቀል ይሆን። እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ቀርጭጫ 80 ዓመት ይሞላት ይሆን ወይስ እውነትን ተላበሳ፣ ህሊናዋን ሳትሸጥ፣ ግን በብልህ አመራር ምርታማ ሆና፣ እንደ አበባ አብባ፣ ፍሬ ሰጥታ፣ ብዙ ብርቱካኖችን አፍርታ ለነፃነት ታበቃን ይሆ?? እንደው ወደፊትን የሚያሳይ መነጽር ቢኖር ሳልበላ ሳልጠጣ ገዥቼ የሚሆነውን ነገር አይቼ እነግራችሁ ነበር። ግን የለምና፣ እኔም እናንተም ቁጭ ብለን (ወይም ቆመን) ጊዜ እንደመጽሃፍ እየገለጸ እስኪያሳየን ድረስ እጁን ወደኋላ ፊጥኝ እንደታሰረ መጠበቅ ነው። ያውም ሞት ቀድሞ ካልጠለፈን

 4. Berhanu Nega is simple ordinary liar.He want to exploit ethiopia with his garbage family to be rich and powerful in ehiopia that is his wish but itis bad dream.Berhanue’s properties in afew years how many assets the government nationalized? find the fact yoursel? Berhanue is now trying to organzied the Guraga to use as a weapon in ethiopiia in demostraion to over through the government by gathering in U.S.A against tigrans that is the goal of Berhane N.and his followers.

 5. That is funny.Leave alone the yesterdays Birtukan others couldn´t lead Andnet it simply the name.Bikefet telba.

Comments are closed