ለባቡር የተሠራው መንገድ በየቀኑ እያደረሰ ያለው አደጋ ተባብሶል
በታምሩ ጽጌየአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ከመስቀል አደባባይ እስከ ሳሪስ ድረስ እያሠራው ያለው ባለ ሦስት ረድፍ (ሌን) መንገድ መሀሉ ለባቡር መተላለፊያ የተሠራ ቢሆንም፣ የባቡር ትራንስፖርት እስከሚጀምር ድረስ ለአውቶብሶች ክፍት በመደረጉ በየቀኑ በሰዎችና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ እያደረሰ በመሆኑ ነዋሪዎች በከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ዳግመኛ ገለጹ፡፡