Logo

የማሙሸት ቡድን ማህተም ይዞ ተሰወረ፤ ኢ/ር ኃይሉ ሌላ ማህተም አስቀረጹ

January 23, 2011

መኢአድ በአሁኑ ወቅት በለየለት መልኩ ለሁለት የተከፈለ መሆኑን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ በትናንትና እትሙ ባቀረበው ዘገባ አመልክቷል። በዚህም መሰረት በአንድ በኩል በኢ/ር ኃይሉና በአቶ ያዕቆብ ልኬ የሚመራ ቡድን እየጎላ የመጣ መሆኑንና ይኸው ቡድን ሰሞኑን በወሰደው እርምጃ እነ ማሙሸት አማረ የሰወሩትን ማህተም የሚተካ አዲስ ማህተም አስቀርጿል። ለዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ፣ ለአቶ ገ/ጻዲቅ ኃ/ማሪያም እና ለአቶ ማሙሸት አማረ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፉም ታውቋል።

ፓርቲውን በመተርተር ሁለተኛውን ቡድን በመምራት እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙት አቶ ማሙሸት አማረ፣ ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለና ለአቶ ገ/ጻዲቅ ኃ/ማሪያም መሆናቸው የታወቀ ሲሆን፣ ይህ ቡድን ሰሞኑን በመሰደው እርምጃ የፓርቲውን ማህተም እና ባለ ዓርማ የደብዳቤ መጻጻፊያ ወረቅት (Letter Head) ይዞ መሰወሩ ታውቋል።

የእነ ማሙሸት አማረ ቡድን ተቃውሞ በዋናነት ያነጣጠረው ከጠቅላላ ጉባዔው በኋላ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡት በአቶ ያዕቆብ ልኬ ላይ ሲሆን፣ “ምክትል ፕሬዝዳንቱ አቶ ያዕቆብ ልኬ በላዕላይ ምክር ቤት በኩል መመረጥ ሲገባቸው በኢ/ር ኃይሉ መሰየማቸው ተገቢ አደለም” የሚል አቋም እያራመዱ መሆኑን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ያስረዳሉ።

የዚህ ቡድን አንቀሳቃሽ መሆናቸው የሚነገርላቸውና ባለፉት ዓመታት ከመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንቶች አንዱ የነበሩት አቶ ገ/ጻዲቅ ኃ/ማሪያም “ኢ/ር ኃይሉን ፕሬዝዳንት አድርገን የመረጥነው እንዲበትነንና እንዲከፋፍለን ሳይሆን እንዲያስተዳድረን ነበር። ኢ/ር ኃይሉ ከፈለገ የራሱን የንግድ ድርጅት እንዲመራለት አቶ ያዕቆብን መመደብ ይችላል። እኔ ፓርቲውን የቆረቆርኩ ነኝ። ኢ/ር ኃይሉ ሊያግደኝ አይችልም” ማለታቸውን አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘግቧል።

ከመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንቶች አንዱ የነበሩት ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ በበኩላቸው “እኔ ሳልሻር በላየ ላይ ሌላ ምክትል ፕሬዝዳንት መሾሙ አግባብ አደለም። አቶ ያዕቆብን በምክትል ፕሬዝዳንትነት መሾም የተፈለገው ከኢ/ር ኃይሉ ጋር ያለውን የጋብቻ ዝምድና ለማጠናከር እንጂ ሰውየው ለፓርቲው የሚጠቅሙ በመሆናቸው አደለም” መለታቸውን ጋዜጣው ጨምሮ ገልጿል።

ኢ/ር ኃይሉ ሻውል ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “እነዚህ ሰዎች የሚናገሩት ሁሉ ሀሰት ነው። ምክትል ፕሬዝዳንት እንድመርጥ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ይፈቅዳል። በዚያ መሰረት ፈጽሜአለሁ። ከአቶ ያዕቆብም ጋር ምንም ዓይነት የጋብቻ ዝምድናም የለኝም። ፓርቲውን ለማፍረስ በጣሩት ላይ የእገዳ ደብዳቤ ተጽፏል። ጉዳያቸው በኮሚቴ እየታየ ነው። እስከዚያ ድረስ ቤቱን እንዳይረብሹ ገለል ተደርገዋል።… ማህተሙንም አንዱን ግለሰብ ይዘህ ጥፋ አሉት። ይሄ የምርጫ ቦርድ ሲስተም መሆኑ ስለገባን ከነሱ ጋር ላለመነታረክ አዲስ ማህተም አስቀረጽን” ማለታቸው ታውቋል።

ከሁለቱ የመኢአድ አንጃዎች ሌላ በማን እንደሚመራ ባይታወቅም፣ ራሱን “የመኢአድ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ” በማለት የሚጠራ ሶስተኛ አንጃም እንቅስቃሴ የሚያደርግ መሆኑን ለአንዳንድ ጋዜጦች ከሚበትነው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል። በውጪ አገር የሚገኙ የመኢአድ ድጋፍ ሰጪ አባላትና አካላት ከየትኛው ወገን ጋር እንዳሉ ባይታወቅም የመኢአድ አራተኛ አንጃ ተደርገው ሊወሰዱ እንደሚችሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ያስረዳሉ።

በ1997ቱ ምርጫ የነበረውን “ቅንጅት” ከመሰረቱት ፓርቲዎች ውስጥ አንዱ የነበረው የኢዴፓ ዋና ፀሐፊ የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው በፓርቲዎቹ የውህደት ስምምነት ሰነድ ላይ ማህተም አላደርግም ብለው ማህተም ይዘው ጠፍተዋል በሚል እስከ አሁን ድረስ ያላባራ ውግዘት የሚወርድባቸው መሆኑን የሪፖርተራችን ዘገባ አስታውሶ፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ አቶ ልደቱን በመክሰስና በመውቀስ የሚታወቁት አቶ ማሙሸት አማረ ዛሬ የመኢአድን ማህተም መሰወራቸው እጅግ የሚገርም አጋጣሚ ነው ብሏል።

Share

11 comments on “የማሙሸት ቡድን ማህተም ይዞ ተሰወረ፤ ኢ/ር ኃይሉ ሌላ ማህተም አስቀረጹ

 1. Keep on MEaD !! Keep on ANDINET !! How lovely you are. I wish I could witness after you take over power. In fact, no no no I don’t wish.
  Midre derek, gegema, minamintie, kwakwatie hula.

 2. ገና የልደቱ ግፍ ያናቁርሻል ህዝበ-ዓዳም ሁሉ፡፡ ሆዳሞች እስቲ በቃችሁ ለተተኪው ትውልድ ቦታውን ልቀቁ፡፡

 3. ይገርማል! ኢ/ር ኃይሉ አሁን ገና ባነኑ፡፡ ቅንጅትንም ያፈረሱት እነዚህ (እነ መቶ አለቃ ማሙሸት) የሸዋ ሴረኞች ነበሩ፡፡ ልደቱ ወሎየ ስለሆነ ነበር ያን ያህል የአሉባልታ ናዳ ያወረዱበት፡፡ አላህ የጃቸውን አላሳጣቸውም፣ እነሆ እርስ በርስ ያናክሳቸው ጀመር፡፡ ይህ ክፍፍል የመኢአድ የመጨረሻው መጨረሻ ለመሆኑ አልጠራጠርም፡፡
  አባ ጂሐድ ሙሔ

 4. Yene Lidetu enba feso alkerem. Lidetu yantena yenath enba >Ehizer dej derese. Enquan yemamushetn huneta baynih asayeh!!!! Egziabher yimesgen.Ewnet yeyze mashenfu ayikerim.Edme yistih hulum yikirta yityikhal.

 5. Man¨mushet was the source of false propoganda against Lidetu.Now he got his own punishment.Beseferut kuna mesefer Ayikrim.Haloe luya

 6. Thank you ethiofact. Mamushet has a mission, i.e, to dismantle AEUP. His recent action hiding property of the party exposes the true identity of the individual. AEUP led by engineer hailu has my full support.

 7. This is our true democracy!! Fighting, being rude for the other person, dream to be a leader…. oh my God they are wrong what a shameful ediot AEUP politician…..
  Wow it was the Hailu shawel and most of his paty members were working hard inorder to attack lidetu and drag him down from politics but…
  i have witnessed that Lidetu was the right person eventough the majority of the opposition party members were against him….
  It is time to admit that Lidetu is a genious, brilliant, smart, chariasmatic politician. A man who can shift our coutry in to prosperity
  PROUD OF YOU LIDETU!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!11

 8. The article is not about Lidetu but AEUP. By the way EDP is not a one-man party as some here are, probably mockingly, trying to tell us. Unlike other parties, policy formulation involve not only CC memebers but also ordinary members of the party.

 9. Forgive me Lidetu. Forgive me Lidetu. You are the truth. Shabia tricked me and made me their slaves. Mamushet Amare was our inside arbegna agent. Mamushet and the other anjas all are arbegna agents financed by shabia through the diaspora. By the way, please send us your $500.00 to get your G7 arbegna certificate. When you pay your $500 Asmara will take a note and would stop organizing demo against you in the diaspora.

Comments are closed