Logo

የሳምንቱ ጋዜጦች ዳሰሳ

January 26, 2011

የኑሮ ውድነትን በተመለከተ፤

በሳምንቱ መጀመሪያ አካባቢ የወጣው ሳምንታዊው መሰናዘሪያ ጋዜጣ በፊት ለፊት ገጹ “የዘይት ዋጋ ጨመረ” በሚል ርእስ ይጀምራል። ጋዜጣው መንግስት ያወጣውን የሸቀጦች ዋጋ ዝርዝርም ለአንባብያን ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ በውስጥ ገጹ ላይ አትሟል።

በየሳምንቱ ረቡዕ የሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ በበኩሉ፣ “የዋጋ ተመኑ በሌሎች ሸቀጦች ላይም ይቀጥላል” በሚል ርእስ የንግድ ሚኒስቴርን በመጥቀስ የዜና ዘገባ አቅርቧል። መንግስት በሀገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር የጀመረውን ስራ በመቀጠል በቅርቡ የዋጋ ዝርዝራቸው እንዲወጣ ካደረጋቸው ሸቀጦች በተጨማሪ በሌሎች ሸቀጦች ላይም የዋጋ ተመን የሚያወጣ መሆኑን ጋዜጣው ዘግቧል።

ጋዜጣው ከዚህ በተጨማሪ ለጡረተኞች የሚከፈለው አበል እንዲሻሻል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ማሳለፉን ገልፆ “የጡረተኞች ትንሳዔ” ሲል ጽፏል። ቀደም ሲል ለጡረተኞች ሲከፈል የነበረው 160.00 ብር እንደነበር ጋዜጣው አስታውሶ፣ በአዲሱ ማስተካከያ ይህ ክፍያ ወደ ብር 294.00 ከፍ እንደሚል አብራርቷል። ጋዜጣው ይህንን ይበል እንጂ ይህ የተሻሻለው የአበል መጠን እንኳን ቤተሰብን ለማስተዳደር አንድን ግለሰብ ከአንድ ሳምንት በላይ መቀለብ አይችልም ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ነጋድራስ፣ ኢትዮ-ቻናል፣ አዲስ አድማስ እና ሪፖርተር ጋዜጦች በበኩላቸው፣ በበርካታ የንግድ እቃዎች ላይ አዲስ የዋጋ ተመን የወጣ ቢሆንም ገበያው ግን ሊረጋጋ አለመቻሉን የሚገልጽ አስተያየትና የዜና ዘገባ ይዘው ወጥተዋል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በተመለከተ፤

መንግስት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት በሚል ሰበብ የዋጋ ተመንና የጡረታ አበል መጨመርን የመሳሰሉ እርምጃዎችን ሲወስድ በዝምታ ሲመለከቱ የሰነበቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተቃውሞ ድምፅ ማሰማት የጀመሩት በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በዚህ ረገድ ኢዴፓ እና መድረክ መግለጫዎችን በማውጣት መንግስት እየወሰደው ያለውን እርምጃ አውግዘዋል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደሚሉት ከሆነ የመንግስት እርምጃ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን የሚጻረር ከመሆኑም ባሻገር ዘላቂ መፍትሄም አይሆንም የሚል ትችት ሰንዝረዋል።

በሳምንቱ ውስጥ የወጡት ጋዜጦች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያወጡትን መግለጫ ማተም ብቻ ሳይሆን፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የውስጥ ሽኩቻ የሚዳስስ ዜናና ትንታኔዎችንም አቅርበዋል። በዚህም መሰረት ረቡዕ ዕለት የታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ “የአንድነት ፓርቲ የእርቅ ሂደት እየተጓተተ ነው” በሚል ርእስ ባወጣው ዜና በአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት መካከል ተከስቶ የቆየውን አለመግባባት ለመፍታት የተጀመረው ‘ቤተሰባዊ የእርቅ ሂደት’ እየተጓተተ መሆኑን የእርቅ ኮሚቴውን አባላት ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ኢትዮ-ቻናል ጋዜጣ በበኩሉ፣ “የአንድነት ፓርቲ ‘የመርህ ይከበር’ አባላትን በተመለከተ ‘የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን ውሳኔ ተቀብለው በተራ አባልነት መቀጠል ይችላሉ’ የሚል ውሳኔ ማስተላለፉንና በፓርቲው ውስጥ ያለው ሁኔታ መስከን ሳይሁን ይበልጥ መወሳሰብ መቀጠሉን አብራርቷል።

በየሳምንቱ ቅዳሜ የሚታተመው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ደግሞ “መኢአድ ለሁለት የመከፈል አደጋ ተጋርጦበታል፤ ምክትል ፕሬዝዳንቱና ዋና ፀሐፊው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል” በሚል ርእስ ሰፋ ያለ የዜና ዘገባ አቅርቧል። ይኸው ጋዜጣ አያይዞም፣ የመኢአድ ዋና ፀሐፊ አቶ ማሙሸት አማረና ጓደኞቻቸው የመኢአድን ማህተምና ባለ ዓርማ የደብዳቤ መጻጻፊያ መሰወራቸውን ገልጿል። ኢ/ር ኃይሉ በበኩላቸው እነ ማሙሸትን በማገድ አዲስ ማህተም ማስቀረፃቸውን አብራርቶ፣ መኢአድ የመከፋፈል አደጋ የተጋረጠበት መሆኑን አስነብቧል።

“የወይዘሪት ብርቱካን ‘የዝምታ ፖለቲካ’ መቼ ይቋጫል?”

ሰንደቅ ጋዜጣ በውስጥ ገጹ “የወ/ሪት ብርቱካን ‘የዝምታ ፖለቲካ’ መቼ ይቋጫል?” በሚል ርእስ ሰፋ ያለ ትንታኔ አስነብቧል። “የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር ወ/ሪት ብርቱካ ሚደቅሳ መንግስትን በድጋሚ ይቅርታ በመጠየቅ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከወጡ ዛሬ 105 ቀናት ይደፍናሉ” ይላል የሰንደቅ ጋዜጣ ጽሁፉን ሲጀምር። በመቀጠልም “ወ/ሪት ብርቱካን 646 ቀናት በእስር ካሳለፉ በኋላ ‘እረፍት ያስፈልገኛል’ ብለው ከፓርቲ እንቅስቃሴ ርቀው ቆይተዋል። ይህም ርቀታቸው የተለያዩ ስሜቶችን ፈጥሯል። ከነዚህም ውስጥ ‘ወ/ሪት ብርቱካ ፖለቲካ ያቆማሉ ወይስ ይቀጥላሉ?’ የሚለው ይገኝበታል” ይላል ጋዜጣው ሀተታውን በማራዘም።

“በወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በኩል የተሰጠ ምንም ዓይነት አስተያየት አለመኖሩም በእርሳቸው ዙሪያ እውነትም ሆኑ እውነትም ያልሆኑ አስተያየቶች እንዲሰጡ በር ከፍቷል። እርሳቸው ስለፖለቲካ ተሳትፏቸው ፍንጭ ያልሰጡት ለመገናኛ ብዙሃን ብቻ ሳይሆን ለትግል አጋሮቻቸው” ጭምር መሆኑን ጋዜጣው ገልፆ፣ ሁኔታውን “አጓጊ” ነው ብሎታል።

“ወ/ሪት ብርቱካን በተፈቱ በማግስቱ 3 ጊዜ ጽ/ቤቱን ወደቀየረው የፓርቲያቸው ቢሮ በመሄድ ከፓርቲው አመራሮች ጋር 40 ደቂቃ የፈጀ ውይይት ካደረጉ በኋላ ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ተመልሰው አያውቁም” የሚል ሃሳብም አስፍሯል ጋዜጣው። አንዳንድ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ‘በግልም አናገኛትም’ ማለታቸውን ጭምር ሰንደቅ ጋዜጣ ባቀረበው ሀተታ ገልፆ፣ ወ/ሪት ብርቱካን ከፓርቲያቸው ጋር መደበኛ ግንኙነት ያቆሙ መሆኑን አብራርቷል።

አንዳንድ የአንድነት ፓርቲ አባላት በዚህ የወ/ሪት ብርቱካን ድርጊት በመበሳጨት “ወይዘሪት ብርቱካን ከፖለቲካ ትግሉ ገሸሽ ብትል ከማንም በላይ የምትጎዳው እሷ ነች። የፖለቲካ ትግሉ ሌላ ጀግና ማፍራቱ እንደሁ አይቀርም” ማለታቸውን ጋዜጣው ጽፏል። “በሌላ በኩል አንዳንድ የፓርቲው አመራር አባላት የወ/ሪት ብርቱካንን መመለስ እንደ ስጋት ያዩታል። ‘እርሷ የአመራር ልምድ የላትም’ በማለት የወ/ሪት ብርቱካንን ለትግሉ አለመመጠን ይናገራሉ” ሲል ሰንደቅ ጽፏል።

በወ/ሪት ብርቱካን ‘የዝምታ ፖለቲካ’ ግራ የተጋቡት የአንድነት ፓርቲ አባላት ብቻ አለመሆናቸውን ጋዜጣው ገልፆ፣ “በውጪ የሚኖሩ ደጋፊያቸውም ቁርጣችንን ንገሪን እያሉ ነው” ይላል። “አንዳንዶቹም ወ/ሪት ብርቱካንን ከእስር ለማስፈታት ያልማሰኑትን ያህል ከተፈታች በኋላ የያዘችው ዝምታ አስደንግጧቸው ያቋቋሙትን ድረ-ገጽ እስከ መዝጋት ደርሰዋል” ሲል ጨምሮ ገልጿል።

ሰንደቅ ጋዜጣ በመጨረሻም፣ “በአጠቃላይ የወ/ሪት ብርቱካን የፖለቲካ ተሳትፎ ቀጣይነት ጉዳይ ለብዙዎች አጓጊነቱ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ሰሞኑን ከወ/ሪት ብርቱካን አካባቢ አንድ ነገር ይሰማል። ይኸውም ወ/ሪት ብርቱካን በቅርቡ አቋማቸውን እንደሚያሳውቁና በመጪው የካትት ወር ወደ ሰሜን አሜሪካ እንደሚያቀኑ እየተገለጸ ነው” በማለት ሰንደቅ ጋዜጣ ሀተታውን ይደመድማል።

Share

10 comments on “የሳምንቱ ጋዜጦች ዳሰሳ

 1. ብርቱካን ወደ ፖለቲካው ዘው ብላ የገባችው በዶ/ር ብርሃኑ አማካይነት ነው፡፡ እሱ ደግሞ ዓላማው ከስራ አስፈጻሚነት ወርዶ የላእላይ ምክር ቤት (የማእከላዊ ኮሚቴ) አባል ሆኖ ስራ አስፈጻሚውን በእሷ አማካይነት ለመቆጣጠር ነበር፡፡ እናም ብርቱካ በቅንጅት ውስጥ የብርሃኑ ጉዳይ አስፈጻሚ ከመሆን የዘለለ ሚና አልነበራትም፡፡ በአጭሩ ብርቱካን የፖለቲካ ብቃትም፣ ብስለትም፣ በቂ ግንዛቤም አልነበራትም፡፡ እሷ ዝም ብላ ጥሩ አገር ወዳድ ናት፡፡ የፖለቲካ ብስለቱ፣ ብቃቱና ግንዛቤው ቢኖራት ኖሮ ቢያንስ ቢያንስ ለሁለተኛ ጊዜ ከርቸሌ አትወርድም ነበር፡፡ አሁንም የሚሻላት ወይ የጥብቅና ስራዋን እየሰራች ባላት ትርፍ ጊዜ በማንበብ ራሷን ማብቃት፤ አሊያም እንደተባለው ወደ ሰሜን አሜሪካ በማቅናት የግንቦት ሰባትን አርበኞች መቀላቀልና ከዶ/ር ብርሃኑ ጋር ጀምራው የነበረውን “ነገር” መቀጠል ነው፡፡

 2. Thank you Aba jihad
  The truth is there . Birtukan join the oppostion politics after the may 8 kinijit demonstration and she was hand picked by Birhanu and supported by Prof. Mesfin (Birhanu and Prof. Mesfin were one and the same that time)She has no the ability and exprience to lead an office leave alone a sick political party. She was´´elected´´ as vise presedent in september and arrested in october ,and again after they released she did nothing to reorganise UDJ . The fact was the KINijit MPS in the parliament were organised and they were attacked by diaspora as rubbur stamp, they badly wanted some one from Kaliti to avoid accusations and they welcomed her to and she took that advantage with some others who were released from kaliti. If you we talk the truth her experience is only sitting in prision (kaliti experience) . As a vice chair of Kinijt, she did noting different she was 100 % loyal to Birhanu. She allowed him to sit in the excutive committe meeting with out being elected and meet Meles Zenawi with being represented.She never act as per kinijt law.Even as a lay man it is just illega.When she was challenged to kick him(Birhau )she left the meeting every hour to get decsion from Birhau. These are few examples.Here was what your lawer doing. Now it is the real challenge to test her leadership skill. If she has the ability to organise and lead a party ,this is the time!!!!! If not weating favourable condition is just cheating the public .Weating for ready made party like KINIJIT 2006 and take advantage of others is to be pure opportunist nothing more and it doesn´t work now.

 3. Birtukan knows that she can´t lead a party. I think she is weating to see which wing of UDJ groups winns or get more support ,then she will join the strongest one. No priciple no truth nothing but only advantage like in the prevous days.kkkkkkkkk This is the action of a wise leaderkkkkkkk

 4. Ayeee yalteyaze giligil yawkal alu?min tadrig new yemitlut .Bemin akmwa new en Gizachewn yemitachenifew?

 5. She knows what has been done against few true and brave Ethiopians . May be she came to her mind and wanted to accept the tuth as a real Bitukan . Not the arificial Birtukan made by Birahnu et.el diaspora who were cheated selfish politicans

 6. She did her own share. It wise to avoid the vocal diaspora who build and destroy personalitie with in a month with out conferming things. I appriciate her decsion.Just ignore them.They are good for nothing.

 7. Judge Burtukan needs to have her own political party if she wants to continue in politics. It is unlikely the power hungry Eng. Gizachew & Co let her function smoothly if she decides to continue with them.
  Regarding exprience and maturity that you mentioned, she is much better than the majority of UDJ’s CC members

 8. Ben,
  Are you sure that she is better? In what? would you please tell us by enumerating her strength? By the way I have worked with both of them. አንድ የፖለቲካ ሰው ሞቅ ሞቅ ሲልና አለሁ አለሁ ባዩ ሲበዛ ብቻ አደለም የትግሉ የመጀመሪያ ረድፍ ላይ መገኘት ያለበት፡፡ በጭንቅ ወቅትም ከትግሉ ሜዳ ላይ ሳይለይ፣ ከዜሮ ጀምሮ እስከ መታገል ካልሄደ ምኑን ፖለቲከኛ ሆነ? ሌላውን እንተወውና ብርቱካን ይህንን (ትንሹን ነገር) አድርጋለች? ቢያንስ ቢያንስ ልደቱ ይህንን ፈተና ያለፈ መሆኑን እመሰክራለሁ፡፡

Comments are closed