Logo

የመኢአድ ጉድ ቀጥሏል፤ ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ታገዱ!

January 26, 2011

የእገዳ እርምጃውን በቅድሚያ የወሰደው የኢ/ር ኃይሉ ቡድን ሲሆን፣ ኢ/ር ኃይሉ ራሳቸው ጥር 13 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፉት ደብዳቤ አራት የስራ አስፈጻሚ እና አስር የላዕላይ ምክር ቤት፣ በድምሩ 14 የፓርቲውን ከፍተኛ አመራር አባላት ማገዳቸውን አስታውቀዋል።

ኢ/ር ኃይሉ ይህንን የእገዳ እርምጃ የወሰዱት አስራ አራቱ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት አባሪ ተባባሪ በመሆን ከጉባዔው በፊት፣ በጉባዔው ወቅትና ከጉባዔው በኋላ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ውጪ ጠቅላላ ጉባዔው ያሳለፈውን ውሳኔ ባለመቀበል፣ በየዞኑ ስልክ እየደወሉ የፓርቲውን አባላት በመከፋፈልና አሉባልታ በማናፈሳቸው መሆኑ በደብዳቤው ላይ ተገልጿል።

በተጨማሪም እነዚህ የፓርቲው አመራር አባላት ላለፉት ሶስት ዓመት ተኩል ጊዜ ያባከኑት የፓርቲው የገንዘብና የንብረት ወጪና ገቢ ሂሳብ ተጣርቶ ሪፖርት እንዳይቀርብ ማድረጋቸው፣ ለፓርቲው ፕሬዝዳንት ውሳኔ ተገዢ አለመሆናቸውና አምባጓሮና ፀብ በማስነሳታቸው መታገዳቸውን ኢ/ር ኃይሉ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ገልጸዋል።
የመኢአድ ዋና ፀሐፊ የአቶ ማሙሸት አማረ እና የምክትል ፕሬዝዳንቱ የዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ ቡድን በበኩሉ፣ ጥር 15 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ኢ/ር ኃይሉ ሻውልንና ምክትላቸውን አቶ ያዕቆብ ልኬን እንዲሁም ሌሎች ሁለት የአመራር አባላትን ማገዳቸውን አስታውቀዋል።

የእነ ማሙሸት ቡድን እነ ኢ/ር ኃይሉን ያገደበትን ምክንያት ሲያብራራ፤ “የፓርቲውን ደንብ አንቀጽ 20/2 እና 20/4 በመጣስ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሾምዎ፣ 18ቱን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሰብስበው የስራ ድልድል ባለማድረግዎና የስራ አስፈጻሚ አባል ያልሆነን ሰው በመሾምዎ፣ የፓርቲውን እንቅስቃሴ በማዳከምዎ፣ በህገ ወጥ መንገድ አዲስ ማህተም በማስቀረጽዎ፣ የፓርቲውን አባላት በመናቅ የፓርቲውን ክብር በማዋረድዎ እና የፓርቲውን ወጣት አባላት አሸባሪ በማለት ለፖሊስ በማስመዝገብዎ” በማለት ዘርዝረዋል።

በኢ/ር ኃይሉ የታገዱት እነ ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ “የታገድነው በህገ ወጥ ማህተም ስለሆነ አንቀበለውም። የፓርቲውን ፋይናንስ በተመለከተ በራሳቸው በአቶ ያዕቆብ ልኬ የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተጣራ ነው” ማለታቸውንና ይህንኑ ሃሳባቸውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና በየዞኑ ላሉ የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማስታወቃቸውን የኢትዮ-ፋክት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ የላከልን ዘገባ አመልክቷል። እነ ኢ/ር ኃይሉ ደብዳቤ ጽፈው ከመበተንና በፓርቲው ጽ/ቤት ቦርድ ላይ ከመለጠፍ ውጪ ማንንም ጋዜጠኛ ለማነጋገር ፈቀደኛ አለመሆናቸውንም ዘጋቢያችን ጨምሮ ገልጿል።

ለመኢአድ ቅርበት ያላቸው ወገኖች፤ “አሁን በመኢአድ ውስጥ እየሆነ ያለው ሁኔታ በኢትዮጵያ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ ታይቶ የማያውቅ ድርጊት ነው” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። (በሁለቱ ወገኖች የተጻፉት ደብዳቤዎች ተያይዘው ቀርበዋል)

Share

6 comments on “የመኢአድ ጉድ ቀጥሏል፤ ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ታገዱ!

 1. ha ha ha ha ha!!! Please enginers and doctors of MEaD, don’t you know we are waiting for you to lead the country next? Stop your bulshit ASAP!! Andignawin tebwaxuna settle adirgut. Ante Mamushet, enginerun (shebawin) manafet yakitehal endie? Angechagichewina astegnaw weyim erasih tegnana tegelagel. …eeeech, ahunis abezachihut.

 2. Good Job Mamushet. We are G7 and we are everywhere. Do not discount us because we are in Asmara. We have all our members of G7 and EPPF as a majority in every party in Ethiopia. Our aim is to stop the peaceful struggle by sending money and buy members via diaspora satellite offices. I will fly soon over there as Mohamed Alberadie did to Cairo few days ago. Please EDP members join us under our other name protected by Eritrea dehininet at http://www.nitroethiopians.org or http://nitroethiopians.org/Home.html P.S. Please do not forget to send us your $500.00 and get your patriot certificate.

 3. Dear parties,
  SHAME ON YOU!!!
  You’re no where to lead this country. I deceided right when I convinced my self thet you’re too immature to lead a kidergarten when I opted not to vote for you. If you want to participate in politics you need to be smarter and learn from Woyane than give up to their simple tricks. Laughable gyus.

  Dear Dr. Birhanu,
  I trust your education should have taught you that you don’t need a PhD in economics to be a leader. Look at Obama, Mandela and all world renouned leaders. They did not master economics to lead such huge countries.

 4. Funny of all,
  You giveup to Isayas, number 1 enemy of the concept of Ethiopia. You humble yourselves into his shoes. Into a personality that managed to sow hatred between the two brothers. AGAIN SHAME ON YOU!!!

 5. kkkk etthio politics…. is that the way they fought there enemy? Before 5 years ago they were discredit young political leder ato Ledettu by fals acusation. Now here you go guys still fighting b/n each others kkkkkk!

Comments are closed