የቤይሩት አውሮፕላን አደጋ መርማሪ ቡድን አየር መንገዱን ሲመረምር ሰነበተ
በቃለየሱስ በቀለ
ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ የገባው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን አደጋ መርማሪ ቡድን፣ እስከ ረቡዕ ዕለት ድረስ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ኃላፊዎችና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወካዮች ጋር ስብሰባ ሲያካሂድ ከቆየ በኋላ፣ በሁለቱ ተቋማት ላይ ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱ ታወቀ፡፡