Logo

እነ አቶ ገብሩ አስራት ከአረና ትግራይ ፓርቲ ተባረሩ ተባለ

gebru asrat
February 2, 2011

የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ ባለፈው ቅዳሜ ጥር 21 ቀን 2003 ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ በአቢሲኒያ ሜዲካል ኮሌጅ አዳራሽ የተደረገ ሲሆን፣ በዚሁ ስብሰባ ላይ ነባሩ የፓርቲው አመራር (እነ አቶ ገብሩ አስራት) ተነስቶ አዲስ አመራር ተመርጧል፡፡ ይህንን ስብሰባ እነ አቶ ገብሩ እንደማያውቁትና “የተደረገው ስብሰባ ህጋዊነት የለውም፣ ፓርቲውን ለማጥፋት የሚደረግ ዘመቻ አካል ነው” በማለት እየገለጹ መሆኑም ታውቋል፡፡

በዚሁ ስብሰባ የፓርቲው ጊዜያዊ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አበበ መስፍን በበኩላቸው፣ የፓርቲው ሕገ ደንብ በሚፈቅደው መሠረት ጉባዔው የተካሄደ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ አቶ አበበ፣ ቀደም ሲል የፓርቲው አመራር በወሰዳቸው አንዳንድ እርምጃዎች ምክንያት ቅሬታ የነበራቸው አባላት የአቤቱታ ፊርማ አሰባስበው አስቸኳይ ስብሰባ ለመጥራት ለፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት በማሳወቅ ሕገ ደንቡ በሚፈቅደው መሠረት መንቀሳቀሳቸውን አብራርተው፣ “ነባሩ አመራር በስብሰባው ለመገኘትና ለመወያየት ፍቃደኛ ባለመሆኑ በተገኙት አባላት ይህ እርምጃ ተወስዷል” ብለዋ፡፡ ይህንንም በሚመለከት ለምርጫ ቦርድና ለሌላ አካል ማሳወቃቸውን አቶ አበበ ለሪፖርተር ጋዜጣ መግለጻቸውን የሪፖርተራችን ዘገባ ያስረዳል፡፡
የፓርቲው ሊቀመነበር አቶ ገብሩ አሥራት፣ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አሥራት አብርሃምና ምክትል ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ በርሀ፣ የተደረገው እንቅስቃሴ ምንም ዓይነት ሕጋዊነት የሌለውና ፓርቲው  የማያውቀው መሆኑን ለሪፖርተር ጋዜጣ አስረድተዋል፡፡ ስብሰባው ከመካሄዱ በፊት ፓርቲውን ለማፍረስ ሕገወጥ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በአካባቢው ለሚገኙት የሚመለከታቸው አካላት ማሳወቃቸውን እነ አቶ አቶ ገብሩ አሥራት ገልጸዋል፡፡ በጉባዔው የተገኙት ከፓርቲው የተባረሩ ጥቂት ግለሰቦች መሆናቸውንም ያስረዳሉ፡፡ እነ አቶ ገብሩ አያይዘውም ‹‹ድራማው ዓረና ትግራይን በትግራይ ብሎም በኢትዮጵያ ካለው የፖለቲካ መድረክ ለማስወገድ የሚደረግ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ነው›› ማለታቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የፖለቲካ ታዛቢዎች “በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም፡፡ እነ አቶ ገብሩ የኢህአዴግ መሪዎች በነበሩበት ወቅት ይህንኑ ዓይነት ተግባር በሌሎች ተቃዋሚዎች ላይ ይፈጽሙ ነበር፡፡ ዛሬ ተራው በእነሱ ላይ ደርሷል፡፡ ትግሉ ይህንንም የሚያካትት በመሆኑ ጠንከር ብሎ መታገል ነው መፍትሄው” በማለት ያስረዳሉ፡፡

Share

8 comments on “እነ አቶ ገብሩ አስራት ከአረና ትግራይ ፓርቲ ተባረሩ ተባለ

 1. So the tunisian and egyptian revolt is coming to MeAD, Arena-MEDREK??? Very interesting it is. keep on guys to get rid off Gebru, Seye, Merara, Beyene, Gizachew, Hailu like your egyptian and Tunisian friends are doing on Mubarek ……

 2. ye ethio”fact” reporter, በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የፖለቲካ ታዛቢዎች didnt said that this is a shameful drama of woyane.i think your third way is a ramp to ‘woyane highway’ it doesnt take no where.

 3. tizbt,
  ሁሉን ነገር ለምን በወያኔ ላይ ማላከክን እንመርጣለን? ራሳቸው አይተ ገብሩ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት በነበሩበት ጊዜ እንኳን የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማድረግ ነጻ ፕሬስ መቀሌ አይገባም ነበር እኮ! Why you are making Gebru & Co. a holly cow? በኔ እምነት የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለቱንም ሰይጣኖች በሁለት እጆቹ መታገል አለበት፡፡ እነ ገብሩ ገና የሚያወራርዱት ሂሳብ አለ!!!!

 4. WE don’t need many parties in tigrai because our really enemies, they want to divide us it must stop this kind of joke.we respect our brother Geberu but we dont believe his philosophy.We have stand togther to defeat our enemies.

 5. As an Ethiopian and from Tigray region Ato Gebru isn’t different from those currently ruling Ethiopia. One day all be asked in front of justice. They don’t represent Tigray ppl, i remember in 1985E.C Gebru was supporting the Eritrean regime like his friend Meles. No exuse now “comes around goes around” all the blood shade in between the two country is because of you and Meles.

 6. ኣነ ዝገርመኒ እስካብ ሓዚ ንምንታይ ካብ ምድቃሶም ዘይነቅሑ ኩሉ ግዜ ምሰ ደቀሱ እዮም ሐዚ ኢትዮጵያ ዘድልያ ልምዓት እምበር ናይ ቃላት ጦርነትን ንባዕልካ ስልጣን ንምሓዝ ዝግበር ንሕንሕን ኣይኮነን ፤፤

 7. እነ ገበሩ ኣስራት እኮ ኢትዮጵያ የካዱና ከፅንፈኞት የተሰለፉ ካሃዲዎች ናቸው ሃገርም ለጠላት ኣሳልፎው የሰጡትና የትግራይ ወጣት ወደ ጦር ግንባር በማዝመት የጨረሱት ካሃዲዎች
  ፡፡

 8. we don’t want your propaganda because time has gone while you were ruling members of TPLF to work for the people of Ethiopia and Tigrai.

Comments are closed