Logo

ደቡብ ሱዳን – ከመገንጠል ባሻገር

February 9, 2011

የደቡብ ሱዳን ሪፈረንደም ውጤት ከትናንት ወዲያ ይፋ ሆኗል፡፡ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ በመሆን ለደቡብ ሱዳን ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ድምጻቸውን የሰጡ የአካባቢው ተወላጆች 99 በመቶ የሚሆኑት መገንጠልን መርጠዋል፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ግን ደቡብ ሱዳን አሁንም ቢሆን የሚጠብቃት ከፍተኛ የቤት ሥራ መኖሩን ይጠቁማሉ፡፡

የግዛት ባለቤትነቱን ለመወሰን በቀጣይነት ሌላ ተመሳሳይ ሪፈረንደም ይካሄድበታል ተብሎ በሚጠበቀውና የሰሜኑና የደቡብ ሱዳን አዋሳኝ በሆነው የአቤ የግዛት አካባቢ በተፈጠረው የእርስ በርስ ግጭት ሃምሳ የሚደርሱ ዜጎች ለሕልፈተ ሕይወት ከመጋለጣቸው ውጪ አጠቃላይ ሂደቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመሰገነ ሆኖ ተጠናቋል፡፡ Read more

Share