Logo

ኢዴፓ – “የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች” በሚል ርዕስ ዙሪያ የተደረገ ቅድመ-ውይይት

February 17, 2011

ትምህርትን በተመለከተ በተደረገው ውይይት በአሁኑ ወቅት መንግስት በትምህርት ተደራሽነት ረገድ የሚያስመሰግን ስራ እየሰራ እንደሆነ የታመነበት ሲሆን የትምህርት ጥራትን በተመለከተ የሚታየው ችግር ግን እጅግ ሰፊና አሳሳቢ መሆኑ ታምኖበታል፡፡ አንድን ትውልድ ለአገርና ለወገን በሚጠቅም መልኩ በመቅረፅ እረገድ የትምህርት ሚና የማይተካና ከሁሉም በላይ በመሆኑ በዋናነት ከካሪኩለም ቀረፃ፣ ከትምህርት መርጃ መሳሪያ አቅርቦትና ከመምህራን ብቃትና ብዛት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በመፍታት የትምህርት ጥራትን በከፍተኛ መጠንና ፍጥነት ማሻሻል እንደሚገባ ታምኖበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ገዢው ፓርቲ መምህራንንና ተማሪዎችን የራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ በማሰብ በትምህርት ተቋማት ላይ የሚፈፅመው መጠነ ሰፊ ድርጅታዊ ጣልቃ ገብነት ለትምህርት ጥራት መጓደል አንድ አሳሳቢ ችግር በመሆኑ ሊወገድ እንደሚገባው ታምኖበታል፡፡ ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Share