Logo

የኢዴፓ ጠቅላላ ጉባዔ ተጠናቀቀ፤ አቶ ልደቱ ስልጣናቸውን ለአቶ ሙሼ አስረክበው ወደ ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ወረዱ

ethiopian democratic party - newly elected leaders (2011)
March 22, 2011

1. አቶ ሙሼ ሰሙ ፕሬዝዳንት (ቀድሞ ዋና ጸሐፊ የነበሩ)
2. ወ/ሮ ሶፍያ ይልማ ዴሬሳ ም/ፕሬዝዳንት (ቀድሞ በነበሩበት ያሉ)
3. አቶ መስፍን መንግስቱ ዋና ጸሐፊ (ቀድሞ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበሩ)
4. አቶ ነፃነት ደመላሽ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ (ከማእከላዊ ከሚቴ አባልነት ከፍ ያሉ)
5. አቶ ሳህሉ ባዬ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ (ቀድሞ የፋይናንስ ኃላፊ የነበሩ)
6. ወ/ሪት ሣራ ይስሃቅ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ (በምርጫ 2002 ወደ ፓርቲው የመጣች፣ ወጣት ኢንጅነር፣ ከትግራይ ክልል)
7. አቶ ጫኔ ከበደ የፋይናንስ ኃላፊ (ከማእከላዊ ከሚቴ አባልነት ከፍ ያሉ፣ ከአማራ ክልል ጎጃም)
8. አቶ ወንድወሰን ተሾመ የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ (ከምርጫ 97 በፊት የፓርቲው ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ፣ ከምርጫ 97 በኋላ ኢዴፓን ተለይተው የመኢአድ ዋና ጸሐፊ የሆኑና ኃይሉ ሻውል ከመኢአድ ሲያባርሯቸው እንደገና ወደ ኢዴፓ የተመለሱ)
9. ዶ/ር ባንትይገኝ ታምራት የጥናትና ምርምር ኃላፊ (ከምርጫ 97 በፊት የፓርቲው ተራ አባል የነበሩ፣ ከምርጫ 97 በኋላ ኢዴፓን ተለይተው ከቆዩ በኋላ እንደገና ወደ ኢዴፓ የተመለሱ)

ሲሆኑ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ደግሞ የሚከተሉት ናቸው።

10. ወ/ሪት ፅጌ ጥበቡ፣ (ከኦሮሚያ አዲስ ዓለም፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ)
11. አቶ አዳነ ታደሰ፣ (ከአዲስ አበባ፣ የፓርቲው መስራች አባል፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ)
12. አቶ ኤርሚያስ ባልከው፣ (ከአዲስ አበባ፣ ወጣት ፖለቲከኛ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ)
13. አቶ ልደቱ አያሌው፣ (ወደ ማእከላዊ ኮሚቴ ዝቅ ያሉ)
14. አቶ ደረጀ ደበበ፣ (ከድሬዳዋ፣ ወደ ማእከላዊ ኮሚቴ ዝቅ ያሉ)
15. አቶ አለማየሁ ባልዳ፣ (ከሐረሪ ክልል፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ)
16. አቶ አንዳርጋቸው አንዱዓለም (ከአማራ ክልል ጎጃም፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ)
17. አቶ ተስፋ መስፍን፣ (ከአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር)
18. ወ/ሮ ሳባ ተስፋዬ (ከአዲስ አበባ)
19. አቶ ጎሹ አውደው፣ (ቀድሞ የኢዲዩ አባል የነበሩ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ)
20. አቶ ሰለሞን ሰንደቁ፣ (ከአዲስ አበባ፣ የፓርቲው መስራች አባል)
21. አቶ ጌታሁን ብሬ፣ (ከአዲስ አበባ)
22. አቶ ታረቀኝ ኃይሉ፣ (ከኦሮሚያ ዝዋይ፣ የባንክ ባለሙያ)
23. አቶ ሔኖክ ሄደቶ (ከኦሮሚያ አርሲ፣ ወጣት ኢንጅነር)
24. አቶ ጌትየ አስፋው (ከአዲስ አበባ)
25. አቶ ቴዎድሮስ (ከአዲስ አበባ)

የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ አባላት ደግሞ፦

1. አቶ ግዛቸው አንማው፣
2. አቶ አስማማው ተሰማ፣
3. አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ፣ ናቸው።

ዛሬ ሰኞ ማምሻውን በራስ ሆቴል በተደረገ የኢዴፓ ጠቅላላ ጉባዔ የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ጋዜጠኞችና ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ አቶ ልደቱ አያሌውም ስልጣናቸውንና የፓርቲውን አርማ ለተተኪው ፕሬዝዳንት ለአቶ ሙሼ ሰሙ አስረክበዋል። የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላቱም ቃለ መሃላ ፈጽመው ኃላፊነታቸውን በይፋ ተረክበዋል።

አቶ ልደቱ አያሌው በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር “ከ18 ዓመት በፊት ወደ ትግሉ ስገባ የነበረኝ አስተሳሰብና አሁን ያለሁበትን ደረጃ ሳነጻጽር ብዙ የአስተሳሰብ ሽግግር አድርጌአለሁ። ያኔ ባዶ ወረቀት ነበርኩ። አሁን ብዙ እውቀት አካብቻለሁ። ባለፉት ዓመታት ትልቅ ት/ቤት ውስጥ ነበርኩ። ሰው ነኝ፣ እየሰራሁ ነበር፣ አስቸጋሪ የፖቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ነበርኩ። እናም እያጠፋሁም እያለማሁም ብዙ ተምሬአለሁ። ሂደቱ ፈጣን የለውጥ ሂደት ነበር። በሂደቱ ያስቀየምኳችሁ ጓደኞቼን ሁሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ስህተቶችና ጥፋቶች ቢኖሩም ከቅንጅት ጋር የነበረንን ግንኙነት በተመለከተ የወሰድነው ውሳኔ ግን ምንም ዓይነት ስህተት አልነበረውም።

“ከዚህ በኋላ በፓርቲው ፕሬዝዳንትነት እንዳልቆይ የፓርቲው ህግ ያስገድደኛል። ‘ለፓርቲው ህልውና ስል፣ አባላት እግሬ ላይ ወድቀው ስለለመኑኝ፣…’ በሚል ሰበብ ስልጣን ላይ መቆየት አልችልም። እኔ ዛሬ ለፓርቲዬ ደንብ ተገዥነቴን አረጋግጫለሁ። ተተኪየም እንዲሁ እንደሚያደርግ አምናለሁ። ይህንን አሰራር ሌሎች ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆኑ በሀገር ደረጃ ተግባራዊ እንዲደረግ እፈልጋለሁ።

“ዛሩ እኔ ስልጣን በመልቀቄ ‘እሰየው ተገላገልን’ የሚሉም፣ ‘ትግሉ አንድ ደረጃ ላይ ሳይደርስ እንዴት ይለቃል?’ የሚሉም ወገኖች ይኖራሉ። የፓርቲ ስልጣኔን ባስረክብም ከኢትዮጵያ ፖለቲካ በቃኝ ልል አልችልም። ፖለቲካ የህይወት ጥሪዬ ነው። ይህንን ጥሪየን የትም ልጥለው አልችልም። እናም በፓርቲየ ውስጥ ትግሉን እቀጥላለሁ። በፖለቲካ ትግሉ ውስጥ ስቀጥል ግን ውጤቴን የምለካው የአገር መሪ በመሆን አደለም። በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ መሆኔን ካረጋገጥኩ ያ ነው የኔ የፖለቲካ ውጤት። እንግዲህ ስለእኔ የሚጽፉ ጋዜጦች፣ ስለእኔ የሚያነቡ ሰዎች፣ ጥዋት ማታ ተጨንቀው ስለእኔ አሉባልታ የሚፈበርኩ ሰዎች በኔ ገለል ማለት ትንሽ እፎይታ ያግኙ። እኔም አረፍ ብየ የሄድኩበትን መንገድ ልፈትሽ” በማለት ሰፋ ያለ የመሰናበቻ ንግግር አድርገዋል።

Share

24 comments on “የኢዴፓ ጠቅላላ ጉባዔ ተጠናቀቀ፤ አቶ ልደቱ ስልጣናቸውን ለአቶ ሙሼ አስረክበው ወደ ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ወረዱ

 1. Well-done EDP. This is how institutions are built. Institutions that last beyond the lifespan of their founders. The leadership is a good mix between young and experienced. Between those who left EDP through the confusion but regret to return to the party. It is diversified leadership from various regions with some representation of women but more work need to be done in the future. All the best!

 2. I read ENA’s coverage. It seems they forgot why they went there i.e. Reporting about the conference. Instead they picked less relevant issue from the event. You remember many were astonished by ETV’s false report regarding edp’s press release following the 2010 election.

 3. Unlike any other political party in Ethiopia, EDP has shown once again a system of choosing and replacing its leader thtough free and fair election. Congratulation to Ato Lidetu. Your courage in the face of discouragement is exemplary to those who choose to be a leader. Also, for those who had serve and replaced by others, congratulation for leading such a meaningful life.

 4. well done ato Ledetu!! we know everything! you have done everything for your country for your party! But the ppl who creat false acusation in1997 election on you history will judge them!! we know that those ppl who strggel in kinijit with you they were stant for there power not for our ppl fredom!! Thatt is why we have seen them they fail to unite without you!! If you were there problem for there unity they can not split b/n eachother!!

  Ato Ldedetu Ethiopian ppl know everything our generation can’t be like those old greedy dog generation who are struggel for there billy! we are with you keep struggel we will be with until victorey come!

  Everything in history remains!!

  Thank you ato Ledetu!!!!!

 5. EDP WILL BE GOOD EXAMPLE FOR OTHER PARTY TOO. OTHER PARTY THEY MUST LEARN FROM EDEP TRNSFER POWER FOR THERE PARTY MEMBERS.

  ATO LEDETU IS THE FIRST EXAMPLE IN ETHIO POLITICS HISTORY.

 6. EDP is so amazing. It is the only party that made itself open for the young generation,which makes it the only future alternative.
  Congratulations Ato LIdetu
  Congratulations Ato Mushe
  Congratulatins all of you in EDP!!!

 7. I am sure Ato Lidetu Will be there in Ethiopian politics. We all know that he is a born politician,….a man that never gives up!!

 8. አንድ አብዱራህማን ቢኖር እሱም ራሱን አገለለ አሉ፡፡ ቅንጅትም ፀረ-እስላም ነበረ፣ ኢዴፓም ወደዚያው እየሄደች ነው መሰል፡፡ ከንግዲህ በኢትዮጵያ በሙስሊሞች የሚመራ (Muslim-led) ፓርቲ መቋቋም የግድ ነው፡፡

 9. Hassan, some muslims say participating in politics is haram. I don’t agree.
  Any way as i live in addis edp is open to anyone . You just make yourself available, have the ambition and work hard. You will reach to your destination.

 10. ለይላ፤

  እስልምና በፖለቲካ አትሳተፉ አይልም፡፡ ይህንን ማንም ሙስሊም የሆነ ሰው (ምናልባት ካንቺ በስተቀር) ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ሙስሊሞች በፖለቲካ መሳተፍ ግዴታቸው መሆኑን የሚያመለክቱ በርካታ ሀዲሶችም አሉ፡፡ ችግሩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለሙስሊሞች የሚመች አደለም፡፡ በዚህም ምክንያት በሀገራቸው ጉዳይ ዳር ሆነው መመልከትን የመረጡ ይመስለኛል፡፡ ደፍረው የገቡትም ዋጋቸውን አግኝተው እየወጡ መሆኑ እየታየ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በድሩ አደምን፣ መሐመድ አሊን፣ አብዱራህማንን፣… መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአጋጣሚ ወደላይ ቢወጡም ተስፋ ቆርጠው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ መሆን የነበረበት ግን ድክመት ቢኖርባቸው እንኳ የአቅም ግንባታ እያደረጉና እያበረታቱ ትግሉን እንዲቀጥሉ ማድረግ የፖለቲካ መሪዎች ኃላፊነት ይመስለኛል፡፡ ግን ይህ ባለመደረጉ ይኸው “ተገፋን፣ ሙስሊም የሚመራው ፓርቲ፣… ምናምን” ማለት ተጀመረ፡፡

 11. Hassan- I disagree with you on so many levels. The most important is this- In todays and the future Ethiopia we should hope and work for post-religious modern and developed Mother Ethiopia! In the 21century why you think a politicians religion should matter is backward looking.
  Nations who have tried to mix religion and nation hood are mostly back ward abd highly under developed. As you know even states with huge oil wealth but religious interference in the state such as Saudi are still highly back ward and under developed in human development index. Saudis continue to hire Western and Asian educated class to run their country and insituations. They have failed to formulate self reliance.

  Ethiopia has a cherished historical place in the history of Islam, as it gave sanctuary to the families of the prophet when they fled Mecca after they were chased by the Qurashi tribe. As a result Ethiopia were given recitation in the Quran protecting all Ethiopians from any religoious war. We Ethiopians should be proud of our history but it is time to look to modernisation of our coutry. Religious should be private and not public or political.

 12. If your comment is regarding Abdurahman or others who are in EDP then, you have to remeber EDP is a LIBERAL party not religious or ethnic based party. In
  fact persons who join EDP are by definition not moslems or Christians or any other religion. They believe in personal liberty and individual autonomy away from group/ethnic/religious doctrine.
  Abdurahamn is founding member of EDP because he is Libertrian not a moslem. All members of EDP are not this or that religion when it comes to Ethiopia. They are Ethiopians who want to modernise our zero sum and violent political culture.

 13. Well:What can i say other than congratulations!! This is a historic moment and unprecedented in Ethiopian politics. Ato Lidetu served two terms and gave way to others after two terms per the party’s bye laws with out ifs and buts. What can others ( both the ruling party and the opposition) learn from this? I think the future is bright for EDP. Deeds speak more than words.Weldone EDP. EDP has once again provesd it is indeed the party of the future.

 14. This is EDP!!!Congradulations Lidetu Ayalew!!!!
  You are a unique creature . You have overcomed all kinds of fabrications and reached to this time. We know what you did for Ethiopia. Bravo !!! The truth remains no one can´t remove it. Although some selfish persons trying to defame you now time confirmed who are you and who are they.We hope we will see you as a leader of Ethiopia in the future.You are especially gifted. Congratulations!!!!!

 15. This is Lidetu the pioneer!!!
  We appriciate your decsion. let the old dogs copy or learn from you as usual.
  Bravo!!!!!!!!!!!!!!1

 16. To home of 1st Hijra-Ethiopia,
  ስሜ ተደጋግሞ ስለተነሳ ነው ይህንን ማስታወሻ ለመጻፍ የተነሳሁት፡፡
  1. በመጀመሪያ ደረጃ እኔ በምንም ዓይነት አስገዳጅ ሁኔታ ተገፍቼ ወይም ተስፋ ቆርጨ አደለም ከኢዴፓ የወጣሁት፡፡ እስከሚበቃኝ ቀን ድረስ ታገልኩ፣ ወደ ፓርቲው ስገባ ባስቀመጥኩት ቀነ ገደብ መሰረት ወጣሁ፡፡ ይኸው ነው፡፡ ሌላ ፍልስፍና የለውም፡፡
  2. ከእስላም ጋር ተያይዞ የተነሱትን ነጥቦች ተመልክቻቼዋለሁ፡፡ ከርእሱ ጋር አብረው የሚሄዱ ባይሆንም ከተነሱ አይቀር የግሌን አስተያየት መስጠት እፈልጋለሁ፡፡ እንደተባለው ኢዴፓ የሊበራል አስተሳሰብን አራምዳለሁ የሚል ፓርቲ ነው፡፡ የአባልነት መስፈርቱም ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ ይህ ስለተባለ ግን ኢዴፓ በሩን ከፍቶ ቢሮው የሚመጡትን ብቻ እየመዘገበ አባል አያደርግም፡፡ ፓርቲው በሁሉም ገጽታው ኢትዮጵያውያንን የሚወክል እንዲሆን (በኮታ መልኩም ባይሆን) እንደ አስፈላጊነቱ ለትግሉ አስፈላጊ የሆኑ ዜጎችን ከምስራቅም፣ ከምእራብም፣ ከደቡብም፣ ከሰሜንም፣ ከመሐልም የመመልመል ኃላፊነት አለበት፡፡ ኢትዮጵያ የሁሉም ናት ካልን ይህንን በፓርቲው ውስጥ ለማሳየት በኃይማኖትም፣ በፆታም ያለውን ስብጥር ቢጠብቅ ይጠቅመዋል እንጂ አይጎዳውም ፡፡ ካለበለዚያ ከአንድ አካባቢ ብቻ የተሰባሰቡ አባላት ካሉት ገጽታው አያምርም፡፡ “የኢትዮጵያውያን” የሚለውን ስያሜውንም የተሟላ አያደርገውም፡፡
  3. በነገራችን ላይ ወደተለያዩ ፓርቲዎች የገቡ ሰዎች የሃይማኖት ጓደኞቻቸውን የማሰባሰብ አቅጣጫን እንደሚከተሉ አንዳንድ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ፡- ብርቱካን በዙሪያዋ እያሰባሰበች የነበረው የእርሷን እምነት ተከታዮች ነበር፡፡ (ስም መጥቀስ ስላልፈለግኩ ነው) ከኢህአዴግ ሚኒስትሮች ውስጥ ተሾመ ቶጋ፣ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ፣ አለማየሁ ተገኑ፣ አስፋው ዲንጋሞ፣… የአንድ ዓይነት ቤተ-ክርስቲን ሰዎች ናቸው፡፡ ሌላም ሌላም ማንሳት ይቻላል፡፡
  4. አሁን ያሉት የኢትዮጵያ ዘጠኝ ክልሎች ቢበታተኑ ያለምንም ጥርጥር ስድስቱ የእስላም መንግስት ማቋቋም እንደሚችሉ አይታችሁታል? ስለዚህ በኔ እምነት የሙስሊሞችን ነገር “ከፈለጉ ይምጡና ይታገሉ፣ ሴኩላር ፓርቲ ነው፣ ምናምን” እያልን ከምናድበሰብሰው Affirmative Action መውሰዱ ይጠቅመናል እንጂ አይጎዳንም፡፡

 17. I agree Abdurahman with you and thank your intervention. I know you guys have been going though very difficult time and crisis and fighting for its survival for the last 5 years, there is no excuse for not making a sustained effort. So one of the many things that the new leadership should make happen it invest it to address this area. EDP needs to work day and night to reflect the true beauty of Ethiopia. It is a challenge but considering what EDP managed to achieve under challenging environment, I am pretty sure they would achieve this target. As a founder and setting the vision of the party, you need to push the agenda. Sometime it is important to set targets and milestones. Again thank you for clarifying some of the point and I hope you would continue in setting up the vision of EDP which is a truly united, democratic and all inclusive vision a reality. So keep the good job up. This election should be a new begining to leave its trouble behind. I am sure we all have to work hard to bring this vision to reality.

 18. you a small brain, don’t think seams like!
  Politics and religious are far each other.

Comments are closed