Logo

የአባይ ግድብ ግንባታ እውን ወቅታዊ ነው?

April 19, 2011

እኔ በበኩሌ የዚህን ግድብ እቅድ ዜና ስሰማ ስለሌላ ስለምንም ነገር ከማሰቤ በፊት በህሊናዬ ውስጥ የመጣው ሀሳብ “ይህ ግድብ ከዚህ በኋላ በዚህ መንግስት ዘመን ተገነባም አልተገነባም ሐገራችን ግን በአባይ ረገድ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራምዳለች ቢያንስ ለብዙ ዘመናት ግብጾች አባይ ላይ ግድብ ልንገድብ ነው ብንላቸው ምን ይሉናል ለሚለው ጥያቄ መልሱን ከግምት ባለፈ በተግባር እናይበታለን” የሚል ስለነበር ከፍተኛ ደስታ ነበር የተሰማኝ፡፡ በርግጥ እያደር በነገሩ ላይ ሳስብበት እንዳንድ ጥያቄዎችን ማንሳቴ አልቀረም፡፡

ለእኔ ከሁሉም በላይ ጥያቄ የሆነብኝ እቅዱን ወደ ተግባር ለመለወጥ የተወሰነበት ጊዜ በእርግጥ ትክክል ነው ወይ? የሚለው ነው፡፡

በአባይ ጉዳይ ላይ ላለፉት ሃምሳ ወይም ከዚያ በላይ ለሚሆኑ አመታት ሐገራችን ግድብ የመገንባት ምኞት እና እቅድ ነበራት ሆኖም ግን ይህ ምኞት እና እቅድ አንድ እና አንድ በሆነ ምክንያት ወደ ተግባር ሳይቀየር ቀርቷል፡፡ እዚህ ላይ መቼም ሁላችንም የምንስማማበት ነጥብ ከኢህአዴግ በፊት የነበሩ የኢትዮጵያ መንግስታት የነበራቸው የሐገር ፍቅር ከኢህአዴግ አስር እጥፍ የሚበልጥ ስለነበር በእነዚህ መንግስታት ግዜ አባይ ያልተገደበው በሐገር ፍቅር ማጣት ነው ማለት እንደማንችለው ሁሉ አሁንም ኢህአዴግ ባለው ልዩ የሐገር ፍቅር ይህንን ግድብ ለመገንባት ተነሳ ማለትም በፍፁም አንችልም፡፡ እንደውም አባይን ለመገደብ የሚያስፈልገው የሐገር ፍቅር ብቻ ቢሆን ኖሮ ምን አልባት አባይ በኢህአዴግ ዘመን ፈፅሞ ሊገደብ አይችልም ብዬ በድፍረት እንድናገር የኢህአዴግ ባህሪ ያስገድደኛል፡፡

ስለዚህ ለአባይ እስከ አሁን ድረስ ያለመገደብ ዋናው እና ብቸኛው ምክንያት ገንዘብ ነው፡፡ ሐገራችን ከማንም ሐገር በላይ ደሃ ሆና ባለችበት ሁኔታ እና ከሐገራት ለምናም ይሁን ተበድራ ገንዘብ እንዳታገኝ ግብጾች በንቃት በሚሰሩበት ሁኔታ ይህንን ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ ፕሮጀክት ለመስራት ማሰብ በማኝኛውም ወቅት
ቢሆን/ ከባድ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ 

ታዲያ በአሁኑ ወቅት ከሁለቱ ችግሮች የትኛው ተቀርፎ ነው ይህ እቅድ ወደተግባር ሊለወጥ የታሰበው የሚለውን ጥያቄ ስንመልስ ግን ከኢህአዴግ ጋር ልዩነት እንፈጥራለን፡፡ መቼም በግብጾች በኩል የተያዘው አቋም ተቀይሯል ብለን ማንኛችንም እንደማንከራከር ግልፅ ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ80 ቢሊዮን ብር ግድብ ለመገንባት የሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ወይስ አልደረሰም የሚለው ላይ ይሆናል፡፡ ኢህአዴግ ለዚህ የሚሰጠው መልስ ግልፅ ነው፡፡ መንግስት እንደ መንግስት ፕሮጀክቱን ሙሉ በሙሉ በራሱ ወጭ መስራት እንደማይችል እያመነ በሰፊው እና ቆራጡ ህዝብ ትብብር ግን ይህን እቅድ እውን ለማድረግ እንደሚቻል ይከራከራል፡፡ ችግሩ ያለው እዚህ ላይ ይመስለኛል፡፡

ይህ ሰፊ የሚባለው ቆራጥ ህዝብ እውነት ኢህአዴግ እንደሚለው ከሚበላው ተርፎት የ80 ቢልዮን ብር ግድብ የመገንባት አቅም አለው ወይ? ተብሎ ቢጠየቅ አብዛኛው ሰው ከፍላጎት እና ከምኞት የዘለለ አቅም አለው ተብሎ መናገር የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ይህን የምለው እንዲሁ ኢህአዴግን ለመተቸት አይደለም፡፡ በትክክልም በህዝቡ ውስጥ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ስለማውቀው ነው፡፡

እኔ እራሴ እንደ አንድ ኢትዮጵያ ወስጥ እንደሚኖር ዜጋ የራሴን ህይወት በማየት ስለብዙ ኢትዮጵያዊያን በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡ እራሴን መካከለኛ ሊባል ባይችልም አነስተኛ ግን ሊባል የማይችል ገቢ ካላቸው ኢትዮጵያውያን አንዱ አድርጌ መውሰድ እችላለሁ፡፡ ይህ እኔ ያለሁበት የገቢ ሁኔታ ደግሞ ብዙ በተለይ በእኔ እድሜ ላይ ያሉ ወጣቶችን የሚወክል ነው ብዬ በድፍረት መናገር እችላለሁ፡፡ በአንፃሩ እኔ ካለሁበት የኑሮ ደረጃ በብዙ እጥፍ የሚሻል ገቢ እና የኑሮ ደረጃ ያላቸው ቢኖሩም የባሰ እና አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ኑሮአቸውን የሚገፉት ደግሞ ብዙዎች ናቸው፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው ቤተሰብ ስለሚበላው ነገር የሚጨነቅ ነው፡፡ እኔ በምሰራበት የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ያለውን ነገር በማየት ብቻ ምን አይነት ኑሮ እየተኖረ እንደሆነ መገመት እችላለሁ፡፡ ምክንያቱም የእኛ መስሪያ ቤት ጥሩ ደሞዝ ይከፍላሉ ተብለው ከሚታሰቡት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ስለሆነ በዚህ መስሪያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ኑሯቸውን በችግር እንደሚመሩ ከታወቀ በሌላ መንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩቱ እንዴት ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት አያዳገትም፡፡
ለአባይ ግድብ ማስገንቢያ መዋጮ ከማሰባሰብ ስራ ጋር ተያይዞ በተለይ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ የ1ወር ሙሉ ደሞዝ መስጠት በአሁኑ ወቅት ያልተፃፈ ህግ ሆኗል፡፡ በእኛ መስሪያ ቤትም ይህ ህግ ተግባራዊ ሲደረግ ያየሁት ሁኔታ በየቀኑ በቴሌቪዥን የማየው ሁሉ ምን ያህል ውስጡን ለቄስ የሆነ ነገር እንደሆነ እንድገነዘብ እረድቶኛል፡፡ ሁሉም ለማለት በሚቻል መጠን ለአባይ ግድብ አስተዋጽኦ ማድረግ ይፈልጋል ግን የሚሰጠው የለውም፡፡ አንዳንዶቹን ቀረብ ብዬ ስሜታቸውን ለመረዳት ስሞክር ደግሞ የበለጠ ብሶታቸውን ለመስማት ችያለሁ፡፡

በዚህ ጉደይ ላይ ካናገርኳቸው ባልደረባዎቼ ውስጥ አንዷ እድሜዋ በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ስትሆን ለእኔ የቅርብ አለቃዬ ናት፡፡ በአባይ ግድብ መገንባት በጣም ደስተኛ እንደሆነች ነግራኝ ግን አስተዋፅኦ ለማድረግ አቅሟ ባለመፍቀዱ ታዝናለች፡፡ ቢያንስ እንኳን የአንድ ወር ደሞዜን ስሰጥ ደስተኛ መሆን ነበረብኝ ትላለች በቁጭት፡፡ አሁን ግን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም የአንድ ወር ደሞዜ እንደ ሚወሰድ ሳውቅ ብዙ ነገር ነው ያሰብኩት ትላለች ምክንያቱም ይህች ወጣት የሁለት ልጆች እናት ስትሆን ባለቤትዋ ደግሞ የግል ስራ የሚሰራ ቢሆንም በቅርቡ መንግስት የሁለት እና ሶስት አመት ግብር አልከፈልክም ተብሎ የሚያንቀሳቅሰው ቢዝነስ ካለው ካፒታል የሚበልጥ ግብር እና ቅጣት ስለጣለበት ስራውን መስራት ባለመቻሉ ይህንኑ በመንግስት የተጣለበትን እዳ ለመክፈል እየጣርን ነው በማለት አሁን ደግሞ ከሷ ደሞዝ ላይ በወር ከአንድ መቶ ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ ለሁለት አመታት ያህል እንዲቆረጥባት መፍቀድ ምን ያህል ከባድ እንደሆነባት ትናገራለች፡፡ ታዲያ በዚሁ መስሪያ ቤት ውስጥ ከዚህች ወጣት በታች የሆነ የወር ደሞዝ እየበሉ ብዙ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ብዙ ሰዎች ስላሉ የነሱ ህይወት ደግሞ ምን እንደሚመስል መገመት አይቸግርም፡፡ እዚህ ጋር መዘንጋት የሌለብን ነገር ግን ምንም እንኳን ኑሮው በጣም ቢከብደውም ለግድቡ መገንባት ካለው ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ የወር ደሞዙን ሲሰጥ በጣም ደስተኛ የሚሆን ሰውም ሊኖር እንደሚችል ነው፡፡ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ግን በእኛ መስሪያ ቤት ውስጥ እንደዚህ አይነት ሰው እኔን አላጋጠመኝም፡፡

ነገሩን ከሁሉም የሚያከፋው ደግሞ መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ገበያን በማረጋጋት ሰበብ በወሰደው እርምጃ መሰረታዊ የሚባሉ እንደ ስኳር እና ዘይት የመሳሰሉ የፍጆታ እቃወች በከፍተኛ ሁኔታ ከገበያ ላይ ከመጥፋታቸው የተነሳ ዋጋቸው ለመገመት ከሚያስቸግረው በላይ ተወዷል፡፡ አንድ ኪሎ ስኳር ከ 25-30 ብር ሶስት ሊትር ዘይት እስከ 150 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ (አንዳንድ ቀልደኞች ወቅቱ ፋሲካ ከመሆኑ ጋር አያይዘው ሲቀልዱ ዘንድሮ ለፋሲካ የሚታረደው ዘይት ነው ይላሉ) መንግስት ይህን እርምጃ ነጋዴዎች ያለአግባብ ዋጋ አስወደዱ ብሎ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት 1ኪሎ ስኳር 16 ብር ዘይት ደግሞ 3ሊትሩ 70 ብር ገደማ ነበሩ፡፡  በእርግጥ መንግስት በራሱ ሱቆች ውስጥ እና በሸማቾች ማህበራት ውስጥ በበቂ ሁኔታ አቅርቦት አለ እያለ ቢሆንም እኔ እስካየሁት እና እስከማቀው ግን ቢያንስ በናዝሬት አካባቢ ይህ በፍፁም ውሸት ነው፡፡ አንዳንዴ የመንግስትን ፕሮፓጋንዳ ስሰማ እኔ የማላውቃት ሌላ ኢትዮጵያ አለች እንዴ እስከማለት እደርሳለሁ፡፡ እኔ ባየሁዋቸው የመንግስት ሱቆች ውስጥ አንድ ሊትር ዘይት እንኳ ሲሸጥ አይቼ አላውቅም፡፡ ስኳርም ቢሆን ለአንድ ሰው ሁለት ኪሎ ብቻ የሚፈቀድ ሲሆን እሱንም ለማግኘት ብዙ ወረፋ እና ችግር አለው፡፡ ባጠቃላይ በአሁኑ ወቅት በሐገሪቱ ውስጥ የእቃዎች ዋጋ ንረት በከፍተኛ ሁኔታ ይታያል፡፡ ይህም አነሰ ተብሎ
ከአንድ ሳምንት ወዲህ የነዳጅ ዋጋ ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ መጠን በሊትር ከ5 ብር በላይ ጨምሯል፡፡ ገና ደግሞ በነዳጁ ጭማሪ የሚመጣውን ጉድ መገመት ይቻላል፡፡

ታዲያ ይህ እና ሌሎች ብዙ ያልተዘረዘሩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያለበት ሰፊው የተባለው ህዝብ በምን አይነት መንገድ በቆራጥነት ገንዘብ በማዋጣት አባይን እንደሚገነባ ኢህአዴግ ያውቃል፡፡

እንደ እኔ እምነት ኢህአዴግ በእያንዳንዷ እርምጃው የቻይናን ፈለግ ነው የሚከተለው፡፡ ምንም የማልጠራጠረው ነገር ቢኖር መንግስት ይህን እቅድ ሲያስብ የቻይናን ምክር መጠየቁን ነው፡፡ ይህ በራሱ የሚያመጠው ችግር አይኖርም፡፡ ኢህአዴግ የሳተው ነገር የሚመስለኝ ግን የቻይና ህዝብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ በጣም በተራራቀ ባህል እና ኑሮ ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች መሆናቸውን ይመስለኛል፡፡ አንድ መሰረታዊ ነጥብ እንኳን ብናይ በቻይና ውስጥ ያለው መንግስት ዛሬ የደረሰበት የእድገት ደረጃ ከመድረሱ በፊት የሰራው ትልቅ ስራ ቢኖር ህዝቡ ለሐገሩ ፍቅር እና ክብር ለራሱ ደግሞ ግለሰባዊ ዋጋ (Value) እንዲኖረው ማድረግን ነው ለዚህ ቀላል ማሳያ የሚሆነን እዚህ እኛ ሐገር ለስራ የሚመጡትን ቻይናውያንን ማየት ነው፡፡ ምንም ቢሆን ከሐገራቸው ቋንቋ ውጭ መናገር የማይፈልጉ ሲሆን በተቻላቸው መጠን እዚህ ሐገር ያለውም ቢያንስ አብሯቸው የሚሰራው ሰው ቻይንኛ እንዲለምድ ሲጥሩ ይታያል፡፡ ቻይና ኢትዮጵያ ውስጥ ቻይንኛ ቋንቋ ብቻ የሚያስተምር ት/ቤት እስከመክፈት ደርሳለች፡፡ በሌላ በኩል ማንኛውም ቻይናዊ ለእለት ኑሮው ከሚሆነው ውጭ ደሞዙን እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ አይቀበልም ምክንያቱም ገንዘቡ ከሐገሩ እነዲወጣ ስለማይፈልግ ነው፡፡ ይህ ዝም ብሎ የመጣ ነገር ሆኖ ሳይሆን ለራሳቸው እና ለሐገራቸው ባላቸው ክብር ነው፡፡ በአንፃሩ በእኛ
ሐገር ውስጥ ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ግዜ ጀምሮ ህዝቡን ቢያንስ የነበረውን የሐገር ፍቅር እና ክብር እንደያዘ እንዲቀጥል ከማድረግ ይልቅ ኢትዮጵያ የምትባል ሐገር የለችም ብሎ በድፍረት እስከመናገር በመድረስ እንዲሁም ህዝቡ ቀጥታ ከሐገር ክብር ጋር የሚያያይዛቸውን እንደ ባንዲራ አይነት ነገሮችን በማቋሸሽ ተተኪው ትውልድ ኢትዮጵያ ስለምትባለው ሐገር ያለው አመለካከት እና ፍቅር ቀዝቃዛ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት አድርጓል በተወሰነ ደረጃም ተሳክቶለታል፡፡ ይህ አካሔድ ትክክል እንዳልሆነ ለመረዳት ኢህአዴግ ከ15 አመት በላይ ወስዶበታል፡፡ ይህ ጉዳይ አሁን ሐገሪቱን ሐገራዊ የሆኑ እንደ አባይ ግድብ ያሉ ነገሮችን ለመስራት ብዙ ዋጋ ያስከፍላታል፡፡ ዛሬ የኢሀአዴግ ባለስልጣናት በየአሜሪካው እና አውሮፓው ዲያስፖራውን ለማነጋገር እያሉ እንዲንከራተቱ ያደረጋቸው በአንድ ወቅት የሰሩት የጥላቻ ፖለቲካቸው ውጤት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ድሮ በነበረን የሐገር ፍቅር እና ክብር ላይ ኢህአዴግ አብሮ የመስራትን እድል በመፍጠር የማጎልበት ስራን ሰርቶበት ቢሆን ኖሮ ለአባይ ግድብ ግንባታ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጉትጎታ ባላስፈለገ ነበር፡፡ ታዲያ እንዲህ አይነት እና የተለያዩ መሰረታዊ ልዩነት ባላቸው የቻይናና የኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ተመሳሳይ ፖሊሲ በመከተል ተመሳሳይ ውጤት ማስመዝገብ አስቸጋሪ ይመስለኛል፡፡ 

ባጠቃላይ እንደኔ አመለካከት ይህ የአባይ ግድብ ግንባታ ምንም ያህል አስፈላጊያችን ቢሆን እና ለዘመናት ስንመኘው የነበረ ነገር ቢሆንም ወደተግባር ለመለወጥ ግን ትንሽ የፈጠን ይመስለኛል፡፡ ኢህአዴግ የአባይ ግድብን የሚያክል ትልቅ ስራ ከመስራቱ በፊት ቅድሚያ ሰጥቶ ሊሰራቸው የሚገባቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ መቼም የማይካድ ነገር ነው፡፡ ቢያንስ በሚቀጥሉት አምስት አመታት ውስጥ በጣም ተስፈኛ የሆነውን የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ብሎ ያቀደውን ግብ የህዝቡን ኑሮ በመለወጥ እና የተሻለ ገቢ እንዲኖረው በማድረግ ቢጠቀምበት ለሐገሪቱ ከፍተኛ ለውጥ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ደግሞ እንዲህ አይነት ፕሮጀቶችን መገንባት ትንሽም ቢሆን ወቅታዊ ይሆናል ባይ ነኝ፡፡

አመሰግናለሁ
ቢንያም አስቻለው

Share

29 comments on “የአባይ ግድብ ግንባታ እውን ወቅታዊ ነው?

 1. በጣም ጥሩ አስተያየትና እኔም የምጋራው ህሳብ ነው:: እየተካሀዱ ያሉ ግንባታዎች ጋብ ብለው መንግስት እንደነዳጅ ባሉ ነገሮች ላይ ድጎማ ያድርግ በሚባልበት ወቅት የ80 ቢሊዮን ፕሮጀክት መጀመር በአብዛኛው ህዝብ ላይ እንደ ትልቅ ዱብዳ ነው::
  የዘይት ስኳር የመሳሰሉትን ዋጋ መናር በሚመለከትም መጀመሪያውኑ ዋጋ ትመና ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ጥናት ማካሄድ ነበረባችው:: ምናልባት መንግስት የሚሰራውን ሊያውቅ ይችላል ማለትም የተጠቀሱት ሸቀጦች በጣም አትራፊ ስለሆኑ ከነጋዴዎች ንግዱን ነጥቆ እራሱ መነገድ ፈልጎ ይሆናል::
  ለማንኛውም ግን የዋጋ ንረቱ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው:: የአባይ ግድብ ደግሞ “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነው”

 2. I am not surprised history always has shown us time and time again. You are totally entitled to air your opinion, however there are times where you have to pay a price for a better future. Yes currently as it is a case elsewhere there are difficulties I am not denying it but we need to be courages as long as it is going to brighten the future generation as our forefather have paid their only life to give us freedom.

 3. What amazes me is that this balanced article and a good argument is followed by an idiotic` commentator` called Justin. Moderators, this moron can argue for the Dam to be built, but how does to ask the question if it is wise to build it now make you a Shabia? So,please stop dummies dumbing-down this great website.

 4. It a very nice move.Something should be started some time and it is done. What ever differences I have with woyane I appriciate the start and the interview given by meles with regard to builld a Abay dam.

 5. Dear Biniam,

  Use your mind for the benefit the nation, What ever the difference you have we all should Unite for our common problem i.e.”Poverty”. Poverty is not Ehadig’s or Opposition parties problem (it is not a matter of poletics). you should change your “Attitude” the other way round. This Mega Project will benefit to the nation i.e. poor people like you. you should not be selfish, be ready for the implementation and leave a legacy for the future generation.

  Therefore let us Shared these Values

  Loyalty
  Loyal to the Nation and Corporation
  Professionalism
  Committed, Innovative, Proactive and always starving for excellence.
  Integrity
  Honest and Upright
  Cohesiveness
  United in purpose and fellowship

  Thanks,

  Agera from London

  [b][/b][b][/b]

 6. Regarding fuel price I think the government can do nothing when it comes price increase. A 50 cents increase in fuel price in the global market means the equivalent of around 8 ethiopia birr.But I too don’t like to see the government to engage in retailing trade, it is nonsense.

 7. dear agera
  you are saing those individuals like Biniam selfish. u realy living in LONDON? U KNOW a kind of life we are pushing now.do you know our todays problem realy? Besimet atinedu!!!!!

 8. dear justin
  selfish and semetawi woyane!!!
  have u read/heard about abye dam on 5 year transformation plan of EPRDF? no no…….
  ……… ze one who protest the implimentation of this project must be on the other side of ethiopins/ethiopia.But the intention of woyane is to shift the attentions of ethiopian.if not why not it included in 5year plan? you must answer it.otherwise do’t damege the heart of loyal ethiopins.

 9. The government is doing fantastic job when it comes to economic development. We shouldn’t deny that fact. But to build confidence and garner support from the people, it must be willing to make changes on the hated ethnic policy, amend the constitution to remove harmful articles, start working to restore Ethiopian access to sea and also always consult the public in the future on any major issues that affects Ethiopian future before implementing them.

  The other day I was listening to the press release by EPRDF. They were repeatedly saying ‘Hizboch’ instead of saying ‘Hizb’ I am not sure whether the intention was also to annoy the people. There is only one Ethiopian ‘Hizb’; not ten or hundred, just as there is only one American ‘Hizb’ or one Chinese ‘Hizb’.

 10. Don’t you think it is better to permanently solve power shortage and at the same time earn the much needed foreign currency instead of subsidising fuel forever…your argument is like saying it is better to keep on feeding people forever instead of solving food shortage once and for all…

 11. ` በመጀመሪያ በዚህ ውይይት ተሳታፊ ለሆናችሁ ሁሉ ምስጋናዬን እና አድናቆቴን መግለፅ እወዳለሁ፡፡ በቀጣይነትም ብንወያይ ብዙ ነገር የምንማማር ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በታች ከላይ በተሰጡት አስተያየቶች ላይ ተመስርቼ እኔም የግሌን ሐሳብ ማቅረብ ፈልጌአለሁ፡፡ ለየግለሰቡ መልስ ከመስጠት ይልቅ ጠቅለል አድርጌ ጠቃሚ ናቸው በምላቸው ጉዳዮች ላይ ነው ያተኮርኩት፡፡
  ህዝብን ሁል ግዜ በችግር ከመመገብ ይልቅ የምግብ እጥረትን ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ማጥፋት ይሻላል፡፡ እኔም እንደማንኛውም ሰው ይህንን ሃሳብ በቀላሉ ነው የምጋራው፡፡ እንደ እኔ ችግሩ ያለው እዚህ ላይ ሳይሆን ይህንን ለመተግበር የምንጠቀምበት ዘዴ ላይ ነው፡፡ እኔ በፅሁፌ ላይ ለመግለፅ የፈለግሁት የአሁኑ የአባይ ወንዝ ላይ የሚሰራው ግድብ ኢትዮጵያ አሁን ካላት ኢኮኖሚ እና ዝግጁነት አንፃር እጅግ በጣም ውድ እና ከባድ ፕሮጀክት ስለሆነ ቢያንስ ለአምስት አመት አዘግይተነው ህዝቡ አቅሙን የሚያሳድግባቸው ስራወች ላይ በማተኮር ጊዜው ሲደርስ ብንሰራው አሁን ላለውም ይሁን ለሚመጣው ትውልድ ያለምንም ጉዳት ውጥታማ ልናደርገው እንችላለን፡፡ በአባይ ላይ ግድብ ለመገንባት ግዴታ አሁን ያለው ትውልድ መራብ እና መቸገር ያለበት አይመስለኝም፡፡ አባቶቻችን እኮ መተኪያ የሌላትን ህይወታቸውን ገብረው በነፃነት ይህችን ሐገር ሲያስረክቡን አማራጭ ስላጡ እና ግድ ስላላቸው ነው እንጂ ሳይሞቱ በነፃነት ሐገራቸውን ለተተኪው ትውልድ የማስተላለፍ አማራጩ ኖሯቸው ግን ጠልተውት አይደለም፡፡ ይህ አሁን ሊተገበር የተዘጋጀው የአባይ ግድብ በአባይ ላይ ሊገነቡ ከሚችሉት ግድቦች ሁሉ ትልቁ እና ውዱ እንደሆነ ተነግሮናል፡፡ እኔ የምለው ግዴታ አሁን የመጨረሻ ትልቁን ግድብ መገንባት አለብን ወይ ? ለምን ከአነስተኞቹ ውስጥ እዛው ቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ እና አማራ ክልል ላይ ሊሰሩ እንደሚችሉ ከታመነባቸው ሁለት ግድቦች ውስጥ አንዱን እየገነባን በሂደት ወደ ትልቁ አንሄድም ነው፡፡ እነዚህ አነስተኛ የተባሉት አንዱ ከ2000ሜጋዋት ሌላው ደግሞ ከ1500ሜጋዋት በላይ ማመንጨት የሚችሉ ናቸው፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይልን በተመለከተ ግቤ 3 በሰላም ከተጠናቀቀ ብቻ ሐገሪቱ አሁን ባለችበት ሁኔታ ምን አልባትም ለሚመጡት ጥቂት አመታታ ያላት የሐይል አቅርቦት ለራሷ ብቻ ሳይሆን በመጠኑ ለጎረቤት ሐገሮችም ሊበቃ የሚችል ነው፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ከላይ እንደጠቀስኩት በአባይ ላይ አንድ 2500 ሜጋዋት የሚያመነጭ ግድብ ቢገነባ የኃይል አቅርቦቱ እጅግ ከበቂ በላይ ነው የሚሆነው፡፡ ምክንያቱም በዚህች አገር ላይ ኢንዱስትሪ ተስፋፍቶ የሐይል እጥረት ለመከሰት መጀመሪያ በመንግስት ውስጥ ያለው የተወሳሰበ ቢሮክራሲ እና ሙስና መገታት ወይም መቀነስ አለበት፡፡ በአሁኑ ወቅት በሐገራችን ውስጥ በኢንቨስትመንቱ በተለይም ደግሞ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከሚሳተፉት ውስጥ ቻይና ቀዳሚውን ስፍራ ትይዛለች፡፡ ሰሞኑን በሰማነው ዜና ቻይና ኢትዮጵያ ውስጥ ልትሰራ ካሰበችው ስራ ውስጥ ማከናወን የቻለችው 11 በመቶውን ብቻ መሆኑን ሰምተናል፡፡ ለዚህ እንደ ትልቅ ምክንያት የተጠቀሰው የኃይል አቅርቦት ችግር ሳይሆን የመንግስት ምቹ ሁኔታን አለመፍጠር ነው፡፡ ታዲያ ለሐገር እድገት በቀናነት ከታሰበ የቱ ነው የሚቀድመው? ስለዚህ ከኛ የሚተርፈውን በደንብ አድርገን እንሸተዋለን፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት መንግስት ያለ አቅሙ እንዲህ አይነት ስራ ውስጥ እየገባ ለዚያ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት በሚያደረገው ጥረት ህዝቡን አያሰቃየው ነው፡፡ ነዳጅ በአሁኑ ወቅት በአለም ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በአለም ገበያ ነዳጅ ሲጨምር እኛም ሀገር መጨመር እንዳለበት 1 1=2 የሚለውን ሂሳብ የሚያውቅ ሁሉ ያውቀዋል፡፡ እኛ ሐገር እየሆነ ያለው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ የተፈጠረው ጭማሪ ከፍተኛው በሌትር 3.52 ብር አካባቢ ነው እኛ ሀገር ግን በአንድ ሊትር 5.80 አካባቢ ነው የተጨመረው፡፡ ታዲያ ይህ ከምን የመጣ ይመስላችኋል፡፡ ድጎማው ቀርቶ አግባብ ያለው ችማሪ ቢቻ ቢደረግ ምን ያህል ልነት ሊኖረው እንደሚችል በቀና ልብ ካሰብነው ለመረዳት ከባድ አይመስለኝም፡፡
  በመጨረሻም እነዚህን ጥያቄዎችን በማንሳት ስለ ህዳሴው ግድብ ወቅታዊነት መጠየቅ ዝም ብሎ በፖለቲካ ልዩነት ወይም በራስ ወዳድነት ወይም ደግሞ ሻዕቢያ በመሆን የሚመጣ አይደለም የቱ ይሻላል ብሎ አማራጩን ከማየት እንጂ፡፡ እኔ አሁን ለዚህ ግድብ ማድረግ አለብኝ የምለውን ያህል አስተዋፅኦ በአቅሜ አድርጌአለሁ፡፡ ወደፊትም ቢሆን አባይን በማልማት ላይ ኢህአዴግ ይስራውም ማንም የአቅሜን ድጋፍ ከማድረግ ወደኃላ አልልም፡፡ ዝም ብሎ በስሜታዊነት መነዳትን እና ጭፍን ጥላቻን በዚህ ትውልድ ላይ አቁመን ተተኪው ትውልድ በማስተዋል የሚራመድ እንዲሆን የበኩላችንን በመወጣት የታሪክ ሰሪነት ጥማችንን ማርካት እንችላለን፡፡
  አመሰግናለሁ

 12. የአባይ ግድብ መገንባት ወቅታዊና አስፈላጊም ነው፡፡ ይህች ሀገር በከፍተኛ የ°ድገት ጉዞ ላይ ትገኛለች፡፡ አንዳንድ መረጃዎች ዘንድሮ የሀገሪቱ °ድገት ከቻይናና ከሕንድ ሁሉ ሊበልጥ እንደሚችል ተንብየዋል፡፡ ይህም የሀገሪቱን ሃይል ፍላጎት በከፍተኛ መጠን እንደሚያሳድገው ግልî ነው፡፡ ትክክለኛ ፍርድ ለሚሰጥ ሰው የህዝቡ ኑሮ እየተለወጠና የግለሰብ የሃይል ፍጆታውም እየጨመረ መሆኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ በመሆኑም የህዳሴ ግድብ መሰራት ወቅታዊና ተገቢ ውሳኔ ነው፡፡ እንዲያውም ሰለቀጣዩ ግድብም ማሰብ መጀመር አለበት ባይ ነኝ፡፡ ለኔ ውሳኔው ከሃይል አቅርቦት በላይ ሀገራዊ እንደምታም አለው ባይ ነኝ፡፡ ለዚህም ነው ህዝቡ ከዳር ዳር እንሰራዋለን! ብሎ በሙሉ ልቡ እየተነቃነቀ የሚታየው፡፡ [quote][/quote]
  ኢትዮጵያዊነት ያኮራል!
  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!

 13. ውድ ሰዊት
  አንድ ጥያቄ ብቻ መልሽልኝ፡፡/ፆታ የተጠቀምኩት በስም ላይ ተመስርቼ ስለሆነ ከተሳሳትኩ ይቅርታ/ የኢትዮጵያ እድገት የሚለካው በምንድን ነው? እንደተባለው ህዘቡ የኤሌክትሪክ ኃይል በግለሰብ ደረጃ ከበፊቱ ይበልጥ ኤሌክትሪክ መጠቀም መጀመሩን በደንብ አምናለሁ፡፡ የዚህ ምክንያቱ ግን የህዝቡ የኑሮ ደረጃ ከፍ ስላለ ነው በሚለው አልስማማም፡፡ በአሁኑ ሰዓት የነዳጅ ዋጋ እጅግ በጨመረበት ሁኔታ እና ከሰል እንኳን አንደ ማዳበሪያ እስከ 100 ብር በሚሸጥበት ሁኔታ የኤሌክትሪክ ዋጋ የተሻለ ስለሆነ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡
  የህዳሴው ግድብም ይሁን ሌላ ግድብ በአባይ ላይ መገንባቱ ለሐገሪቱ እጅግ ጠቃሚ እና አስፈላጊ መሆኑን ሁላችንም የምንስማማ ይመስኛል፡፡ ልዩነታችን በወቅታዊነቱ ላይ ስለሆነ አንቺን ወቅታዊ እንደሆነ እንድታምኚ ያደረገሽን ነገር በደንብ ብታስረጂን በጣም የሚጠቅመን ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ እባክሽ የኢትዮጵያ እድገትን የምንለካው በምን እንደሆነ ፣ የኢትዮጵያ እድገት ከቻይና እና ከ ህንድ የተሻለው በምን መልኩ እንደሆነ አንቺ የተረዳሽውን ከአባይ ግድብ ወቅታዊነት ጋር አብረሽ አብራሪልን፡፡
  አመሰግናለሁ
  አሜን ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ!

 14. Dear Biniam,

  I think your argument only revolves around the economic aspect of a very complex issue which has more of a geo-political dimension than just money.. .. ..but you don’t realise that you are perhaps unknowingly pursuing Egyptian cause by trying to delay a project we can only do ‘now or never’ in terms of geopolitical situation in the region and the world in general….Time is what Egyptians have been buying and time is what you are trying to offer them for free..think about it if you are ethiopian…. This project will not only enhance ethiopia’s economic development but will also change Ethiopia’s position in relation to the Nile..

 15. ውንድሜ ቢንያም

  የጽሁፍህን ቋንቋ አጠቃቀምህን በጣም ወድጀዋለሁ። ቀልድና ቁም ነገር ያዘለ አጻጻፍ ይዘት አለህ። ጥሩ ጸሀፊ ነህና ከመጻፍ እንዳትቦዝን።

  ይህንን ካልኩ ቦሓላ ወደ አባይ ልመለስ። የጽሁፍ አላማ ለምን አሁን የሚል ነው?

  እንደኔ ከሆነ አባይን ሳንገድብ አንድ ቅን ባደር ቁጥር የመጠቀም መብታችን እየተነጠቀ ነው የሚሄደው፡ የመገንባት መብት ቢሰጠንም ከታች ያሉ ተጠቃሚዎች ውሀውን መጠቀም ጀምረው ከሆነ፡ ያፈሰሱትን ንዋይ ካሳ ካልከፈልን የአለም አቀፉም ህግ የመጠቀም መብት አይሰጠንም። በተለይ ግብጾች ይህንን ህጋዊ ድጋፍ ለማግኘት ቀን ተሌሊት እየሰሩና ከፍተኛ ንዋይ እያፈሰሱ ነው። ቶስካን ፕሮጀክ ብለው ከ 300 ኪሎ ሜትር ባላይ የሚሆን ሰው ሰራሽ ወንዝ ፈጥረው ወዳ ምእራብ ግብጽ ከወስዱት ሰንብተዋል። በቢሊዮን የሚቆጠር ሄክታር የሳህራን በርሀ ወደ ለም መሬት ለመለወጥ ከጀመሩ ሰነበቱ። የኛ ነገር ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል እንደሚሉት ከሆነ ሰንብቶዋል።

  በተለይ ግብጽና የቀድሞ የቅኝ ግዛት ሀገሮች ተስማምተው ውሉ ከፈረሰ። “ጨዋታ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ” እንደሚሉት የአባይ ውሀ የሻሞ ጨዋታ ይሆናል። የዛሬ አምስት አመት ብር በስልቻ ተሸክመህ ብትመጣም ጠብታ ውሀ ማቅዳት የበለጠ ዋጋ የሚያስከፍል ይሆናል። እንደ ጠበብቶቹ አባባል ግብጾች 55 ቢልዮን ኪዩቢክ ውሀ ተጠቃሚ ይሆናሉ። ይህ ማለት የማንንም ውሀ ሳይሆን እንጠጣ የምንለው፡ የሰው ባንቡዋ ነው። ስለዚህ ብንችል ትላንትና ካልቻልንም ዛሬ መገደብ የተሻለ ነው። ስለዚህ ኢህአዴግ ልብ ገዝቶ ይህንን የሀገር ሀብት ተሻምተን ለልጆቻችን እናስቀር ካለ በርታ ነው መባል ያለበት። ስራው ይጀመር፡ ባምስት አመት አቅማችን ባይችል በ10 ይለቅ። ዋናው የባለቤትነታችንን ማረጋገጡ ጉዳይ ቀላል ዋጋ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።

  እንዲያው ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም ብለን ብር ያለው በብሩ፡ እውቀት ያለው በእውቀቱ፡ ጉልበት ያለው ደግሞ ዶማውን ይዞ ይህንን ቅርስ ለልጅ ለማውረስ መሞከር አለብን።

  ይህንን ስል ግን መንግስት ሰዎች ከሚሽከሙት በላይ እንዳይጭን ከፈተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። በተለይ ሰራተኛውን ከፍቃዱ ውጪ ደምወዙን እንዲሰጥ ማስገደድ የለበትም።

  በቸር ይግጠመን

  YHM

 16. Dear All
  This is part of the TPLF work (contract) to fulfil the westerns/ and Arabs agenda to control Abbay river and its sources/ Ethiopia/ Ethiopian Nationalism/ This is part of dismantling and controlling Ethiopia.

  Also it is against the current constitution – Article 39. For any water diversion/ Dam or major irrigation project TPLF needs the approval of the Amhara region. According to Article 39 Abbay is belonging to the Amhara people. It is only the Amhara people who can make the decision to develop Abbay..

  Why TPLF want to build a dam outside the Amhara region? Right of nations, nationalities and peoples to secede from the Ethiopian federation is respected by TPLF. What would happen if l Benishangul-Gumuz region decide to secede from the federation?

  We do not need TPLF, Western / Sudan and Egypt help to build this dam. This is part of enslaving Ethiopia by TPLF and their supporters. For any pan Ethiopian project first you should debate on the implications of Article 39 .
  Workewoha

 17. ለእኔ ከሁሉም በላይ ጥያቄ የሆነብኝ እቅዱን ወደ ተግባር ለመለወጥ የተወሰነበት ጊዜ በእርግጥ ትክክል ነው ወይ? የሚለው ነው፡፡

  የትግራይ ጉጅሌዎች ቡድን አባይን (ግዮንን)ልገድብ ማለቱ የባዶ-ተስፋን ብድግ አድርጎ የጠቀለለበት መርዝ ውስጡ ስላለ ነው፤ መርዙም የሕዝቡን ነፃነት መግደል ነው ።

 18. Workewoha, your view is shared by evry infuriated [b]Shabya[/b] I come across. It would be good if Eritreans spend their time on developing the so called “Eritrea”.

 19. Now everytime someone opposses TPLF does that make him the even worse Shabiya?
  -Really i am beginning to think we really are dumb,hopeless people who deserve being POOR(in mind,spirit,and material). The TPLF propaganda is to blame all opposition to be Shabiya,because they are `clever` to know shabiya is the most hated people by most Ethiopians. If you fall for this most basic propaganda,Meyesaw&Justin,you are idiots, otherwise you are non-brained low-level TPLF supporters wasting online space at this website. BEKA!

 20. Thanks Alolo.

  TPLF and its supporters to answer this Q.

  discussing democracy human right, and development ,environmental impact, displacement of people, the specific issues related to Abbay river such soil erosion, mini dam on tributaries to grow food and to produce electric and the financial cost of mega dams so on… are not important issues for TPLF and their supporters.

  Like all dictators the mass has to be confused by mega project. For the TPLF it is not only the traditional dictators big project it’s and selling electric to Sudan. (TPLF is hoping to gain considerably from selling electric to the Arabs).

  The main reason for TPLF to build the dam is..

  TPLF, supporters and sponsors such as Sudan Egypt and west prime interest is changing Abbay’s geo politics from the traditional Ethiopia vis-à-vis Arabs to inter Ethiopian conflict (Ethiopia vis-à-vis Benishangul) building a dam outside traditional Pan Ethiopian area.( The Arabs and the West headache)

  it is the main reason why Sudan and Egypt support this dam. (Don’t buy TPLF Spin Egyptian threat)

  I just want to ask TPLF and their supports about their specialisation ‘the implication of article 39’.

  Please can you answer this? Please don’t label me! I am Ethiopian who suffer lots under TPLF racist rule and experienced the meaning of Article 39. Also I am not from Gojam or Amhara region! Shall i say i am typical the product of the Ethiopian melting pot! By the way some one said to me we are more than 12 million in Ethiopia! I think soon we need to organises yourself to demand our own region! Ethiopians region!

  Why TPLF want to build a dam outside the Amhara region? Right of nations, nationalities and peoples to secede from the Ethiopian federation is respected by TPLF. What would happen if l Benishangul-Gumuz region decide to secede from the federation? 10 years 50 0r 100 years time ?

  I am sure Sudan and Egypt would be happy to support and sponsor Benishangul-Gumuz liberation front as they support TPLF from its inception
  Workewoha

 21. To All.
  What is astonishing is no one seems to ask how BOND financial instruments work.
  In short,over five years the government will give 5-6% interest on original investment,in principle. However,the `quality` of the Bond is the question.Firstly,at current rate of inflation,the original investment,after 5yrs will end up losing 40% of its value.Secondly,all proper Bonds are rated internationally,like at MOODY`S and such. What we have here is what is called Junk Bonds,with no underwriting by an international insurer or otherwiseWhy do you think no major financial institution or foriegn government is involved? D`nt tell me Egypt or bankrupt Eritrea has the muscle in convincing the world to stop financial institutions not to invest in a supposedly lucrative deal?Oh,the money will be raised by our gracious people,but it will end in tears and already looking forward for EPRDF`s scapegoat .
  Secondly,I believe this government should have done what is its good at and an expert since its genesis,instead of deception! Simply beg for funding,internally and abroad.We all want the Nile to benefit our Country.I do not believe this government is capable for several reasons more ,but enough for today. BEKA!

 22. ይህ የአባይ ግድብ ወሬ በአራዳ ቁዋንቁዋ ቁጩ መሰለኝ . በተባለው ቦታ ግድብ ለማስገንባት የሚያስችል ከተለያየ አንጻር የተደረገ ጥናትና የውሳኔ ሀሳብ እንዳለ ባፋልግ ማግኘት አልቻልኩም . እንዲህ ያለ እቅድ መቸም ሰፊ የፊዚቪሊቲ ጥናት እንደሚያስፈልገው የሚያጠያይቅ አይመስለኝም .

  መለስም ሆነ ባለስልጣኖቹ ወይም እዚህ ዋርካ ላይ የሚፎክሩት ጉጅሌዎቹ የግድቡ እቅድ ጥናት ፕላን ይህ ነው ሲሉ አልሰማሁም .

  የተባለው ግድብም ቀደም ሲል በወጣው የአምስት አመት እቅድና ትራንስፎርሜሽን ውስጥ አልተገለጠም . ይህ ራሱ ወደ አንድ ትርሊዮን ብር አካባቢ ያስፈልገዋል . ይህ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ የመለስ መንግስት ራሱን በስልጣን ላይ ለመጠበቅ ከምንጊዜውም በበለጠ ብዙ ገንዘብ በሚዘራበት ጊዜ ነዉ . ገንዘብ እያተሙ መንዛቱ ደሞ እንፍሌሽን አሻቅቦ እንዲፈረጥጥ ያደርገዋል . የብር የመግዛት አቅም ወደታች ያሽቆለቁላል ….በእንዲህ ያለ ጊዜ መንግስታት እንፍሌሽንን ለመቁጣጠር የሚያደርጉት አንዱ መንገድ ቦንድ መሸጥ ነው

  እንደሚመስለኝ መለስ የወርድ ባንክ አማካሪውቹን አስጠርቶ ጫቱን አብሮ እየቃመ እንደዚምባቡውዌ ብር በጆንያ ልሆን ነውና ምን ይሻላል ይላቸውል .

  አማካሪዎቹም ይህማ ቀላል ነው እንፍሌሽኑን ለመቀነስና ለመግታት በስርጭት ላይ ያለውን ገንዘብ ሰብስብ ይሉታል . እንዴት አድርጌ …? ይላል መለስ . አማካሪዎቹም ከብዙ አመታት በሁዋላ የሚከፈል የመንግስት ቦንድ እየቸበቸብህ ብሩን ሰብስበህ አቃጥል ይሉታል ….

  መለስ የእትዮፕያ ህዝብ አምኖ ከሱ ቦንድ እንደማይገዛ ያውቃል . ቀላሉ መንገድ ጥሩ መሸወጃ መፍጠር ነው . ስለሆነም የግድብ አኒሜሽን አሰርቶ አባይን መገደቢያ ከሊቅ እስከደቂቅ …ከስረኛ እስከ አሳሪ አገር ሁሉ በመም ቦንድ በውዴታ ግዴታ ግዙ ብሎ በበዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ብር መሰብሰብ .

  ይህን ብር ሰብስቦ በማቃጠል እንፍሌሽንን ማስታገስ ይቻል ይሆናል ….. አላውቅም እኮኖሚስትች ካላች ሁ አስረዱ

  ገንዘብ ከተሰበሰበ ብሁዋላ የአባይ ግድብ ለምን አልተሰራም ብሎ የሚጥውይቅ ካለ …..ለንዲህ አይነቱ ሰው ካሁኑ የሀውልት መሰረት ሊጣልለት ይገባል ..

  እስኪ በቤቱ ኮኖሚስት ካለ ሀስብ ይስጥ


 23. EVERYTHING THING IS POSSIBLE; HISTORY HAS SHOWN US PEOPLE HAVE THOUGHT THE UNTHINKABLE AND MADE IT HAPPEN,MADE THE IMPOSSIBLES POSSIBLE,IMAGINED BEYOND EXPECTATION AND WENT FAR IN ACTION!!! ABEBE BIKILA, HAILE GEBRESELASSIE, MARTIN LUTHER KING, MAHTAMA GHANDI, NELSON MANDELA, OSAMA BIN LADEN, BARACK OBAMA, CAN YOU ADD SOME; I BET U SURELY DO!!!
  WHAT MATTERS IS JUST ONE THING: BURNING DESIRE!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

 24. its nice idea but i think everything is not confer t our b/z we have more and very more problem ………………………………………………………

 25. what are u guise toking? know Ethiopia don’t wont your toke it is now at work pleas let as give her our hands b/c that’s what she went not your toking.

Comments are closed