Logo

‹‹የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከባድ ማጥ ውስጥ ነው›› አቶ ሙሼ ሰሙ፣ የኢዴፓ ሊቀመንበር

July 1, 2011

አቶ ሙሼ፡- በሁለት መንገድ መግለጽ ይቻላል ብዬ ነው የማስበው፡፡ አንደኛው ዓለም አቀፍ መግባባት የተደረሰበት በቁጥር የምንገልጸው አስር፣ አሥራ አምስትና ሃያ ፐርሰንት የምንለው ነገር ነው፡፡ እንግዲህ ያንን ስንወስድ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በተለይ በዚህ ወርና ባለፈው ወር ያለው ግሽበት ወደ አርባ ፐርሰንት አሻቅቧል፡፡ ያ ማለት በመግዛት አቅማችን ላይ አርባ ፐርሰንት ቅናሽ ታይቷል ማለት ነው፡፡ ይኼ ቁጥሩ ነው፡፡ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ ትክክለኛ ገለጻ ነው ወይ ስንል? አይደለም፡፡ ቁጥሩ በሕይወቱ ላይ ምን ያህል ጉዳት እንዳደረሰበት የሚያሳይ አይደለም፡፡ በሕዝቡ በውስጡ ያለውን ስቃይና መከራ የሚገልጽ አይመስለኝም፡፡ ሁለተኛው መገለጫ መንገድ ደግሞ እኛው ራሳችንን እንደ አንድ ተጠቃሚ የምናይበት መንገድ ነው፡፡ ያለው አቅርቦት ፍጹም አስተማማኝ አይደለም፡፡ የአቅርቦት መጥፋት ብቻ ሳይሆን ጥራት ፈጽሞ የጎደለበት፣ ሚዛን የተዛባበትና የግብይት ሥርዓቱ የተናጋበት ሁኔተ ውስጥ ነው ያለነው፡፡ የምርቶች ዋጋ በአንድ ዲጂት ሳይሆን በሁለትና በሦስት ዲጂት አድጓል፡፡ አንድ ብር ስንገዛው የነበረውን ነገር በሚቀጥለው ቀን አምስትና ስድስት ብር የምንገዛበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በጥቅሉ ስናየው የግብይት ሥርዓቱ ተናግቷል፡፡ አቅርቦቱ ተናግቷል፡፡ የዋጋ ንረቱ ይህ ነው ተብሎ ሊገለጽ የሚችል አይደለም፡፡ የኢትዮጰያ ኢኮኖሚ ከባድ የሆነ ማጥ ውስጥ ነው ነው፡፡  ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (ሪፖርተር)

Share