Logo

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሕግ ሲጥስና ሕግ ሲያወጣ ከርሞ ተዘጋ

July 10, 2011

ምክር ቤቱ ባለፈው መስከረም ሥራውን በጀመረበት ወቅት ካከናወናቸው ተግባራት ውስጥ በዋነኛነት የሚጠቀሰው ቀደም ሲል የነበረው ም/ቤት ለመድብለ ፓርቲ ፓርላማ አሰራር ይጠቅማሉ ብሎ ያወጣቸውን ድንጋጌዎች ለአንድ ፓርቲ የም/ቤት አባላት እንዲመች አድርጎ ማሻሻል እንደነበር የሪፖርተራችን ዘገባ አስታውሶ፣ ይሁን እንጂ እነዚያ የደንብ ቁጥር 3/1998 አንቀፆች እንዲሻሻሉ የተደረጉት ራሱ ደንቡ ላይ በተቀመጠው የአሰራር ስርዓት መሰረት እንዳልነበር ምሳሌዎችን በመጥቀስ ዘጋቢያችን አብራርቷል።

በዚህም መሰረት፣ ሁሉም ፓርቲዎች የሚወከሉበት የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ (የፓርላማ ቡድን) 10 እና ከዚያ በላይ መቀመጫ ባላቸው ፓርቲዎች ውክልና እንዲቋቋም የሚደነግገው አንቀጽ የመድረክ ፓርቲን ተወካይ ለማካተት እንዲችል “አንድ መቀመጫ ያለው ፓርቲ” የሚል ማሻሻያ እንደተደረገበት፣ የም/ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎች ቁጥር ከ13 ወደ 16 ከፍ እንዲል መደረጉን፣ የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላት ቁጥር ከ27 ወደ 21 ዝቅ እንዲል መደረጉን፣… እና የመሳሰሉትን ማሻሻያዎች በማድረግ የህግ መጣስ ርምጃውን ጀምሯል ሲል የሪፖርተራችን ዘገባ አመልክቷል።

ቀደም ሲል በነበረው ደንብና አሰራር መሰረት የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ኃላፊ የየትኛውም ፓርቲ አባል ያልሆነ ገለልተኛ ሰው እንዲሆንና እሱም በአፈ-ጉባዔው አቅራቢነት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሚኖራቸው ስምምነት እንደሚሾም የሪፖርተራችን ዘገባ አመለክቶ፣ ይሁን እንጂ አፈ-ጉባዔው ይህንን አሰራርና ድንጋገጌ በመጣስ የመድረክ ፓርቲን ተወካይ ሳያማክሩ አቶ ንጉሱ የተባሉ እዚያው ምክር ቤት የነበሩ የኢህአዴግ አባል መሾማቸውን ገልጿል።

ምክር ቤቱ የራሱን ደንብ የመጣስ ሂደቱን እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ ቀጥሏል ያለው የሪፖርተራችን ዘገባ አያይዞም፣ በምክር ቤቱ ደንብ መሰረት የቀጣይ ዓመት በጀት ም/ቤቱ ከመዘጋቱ አንድ ወር በፊት (ሰኔ 1 ቀን) መቅረብ እንዳለበት ቢደነግግም የዘንድሮው በጀት ረቂቅ ለም/ቤቱ የቀረበው ከሳምንት በላይ ዘግይቶ ነው ብሏል። ተቃዋሚዎች በብዛት በነበሩበት ባለፉት 5 ዓመታት ግን የበጀት ረቂቅ ይቀርብ የነበረው በደንቡ ላይ በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት ከግንቦት ወር የመጨረሻ ሳምንት ጀምሮ ነበር። ይህም የሚያሳየው ኢህአዴግ ማንም አያየኝም በሚል መንፈስ ምን ያህል ህግ እንደሚጥስ ነው ሲል የሪፖርተራችን ዘገባ አመልክቷል።

በደንቡ አንቀጽ 148 መሰረት የአስተባባሪ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ በየ15 ቀኑ መሆኑንና በዚህም መሰረት በዓመት ቢያንስ 16 መደበኛ ስብሰባዎችን ማካሄድ እንዳለበት ቢደነግግም፣ በአፈ-ጉባዔው የሚመራው አስተባባሪ ኮሚቴ ግን በአንድ ዓመት ቆይታው 4 ጊዜ ብቻ ስብሰባ ማካሄዱን አፈ-ጉባዔው ራሳቸው ሀሙስ እለት በነበረው የመዝጊያ ስብሰባ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል።

በደንቡ አንቀጽ 34 መሰረት የም/ቤት አባላት የንግግር ጊዜ የሚወሰነው ፓርቲዎች ያላቸውን መቀመጫ መሰረት አድርጎ እንደሆነ ቢደነግግም፣ ይህ አንቀጽ መሻሻሉ እንኳ በግልጽ ሳይታወቅ ለም/ቤት አባላቱ የሚመደበው የመናገሪያ ጊዜ በዘፈቀደ ሲሰጥ እንደነበርም የሪፖርተራችን ዘገባ አመልክቷል።

“የተቀዋሚዎች ቀን” ተብሎ በደንቡ አንቀጽ 35 የተደነገገው አሰራርም በም/ቤቱ የአንድ ዓመት ቆይታ ተግባራዊ አልተደረገም። ይሁን እንጂ ይህ አሰራር ስራ ላይ ያልዋለው ከደንቡ ላይ በመፋቁ ይሁን የመድረክ ፓርቲ ተወካዩ አቶ ግርማ አጀንዳ ባለማቅረባቸው በግልጽ አልታወቀም ሲል ሪፖርተራችን የላከልን ዘገባ አመልክቷል። (pdf)

Share

5 comments on “የኢትዮጵያ ፓርላማ ሕግ ሲጥስና ሕግ ሲያወጣ ከርሞ ተዘጋ

 1. Ethiofact,

  One minor correction: why don’t you say our ‘wokil or zegabi’ instead of our ‘telalaki’? I think the word ‘telalaki’ has demeaning conotations in our society. Just my opinion.

  Apart from that I must say thank you for your balanced report. When a ruling coalition controls 99.6 percent of the seats in the national assebly, the borderline between party and government will be irraparably destroyed. To EPRDF apologists and blind supporters like Belai it is simply the sign of invincibility and dominance, despite the massive costs for democracy and nationa cohesion. Since May 2010, Ethiopia has been ruled by one party congress, not by a federal parliament.

 2. The desire for multiparty democracy to flourish in our country has deen politically castrated by the ruling Front (not a coalition,solac)with unconvincing excuses of”imagined” or “advanced” knowledge of “foreign” interference not to allow,or frustrate functioning,independent,democratic-building institutions to develop.
  The judiciary is frankly invisible in its purpose or independence…..The Military,Police,& the major civil-service decisions (makers)are managed & run on either ethnic or by strict loyal`commissars`.It is also impossible to distinguish “the State” and the ” Front”,whereas this ruling Front itself is an undemocratic collective.It cannot be capable to introduce,or have the desire for an acceptable form of multiparty democracy.to reign.
  With 98% control of a “parliament”,then add a decorative but a laughably inert President,the idea of checks & balances is a distant.
  However,the donor nations tell us this ruling Front is “OK”by African standards(not out of love,just master-client relationship) as to make it a reciepient of western aid,to cover as much as 30% of the nations annual budget,and hence helps prop-up this client regime.
  This,my friends,is nothing short of contempt for Ethiopia and we Ethiopians.by the western powers that donate in millions to keep this regime well fed,while fully knowing its dim outlook on questions of a true representative democracy when just on the recent election,their cadre`s managed to overcook the fear factor on ordinary people,,and ended up deligitimising themselves out like N.Korean elections from a properly mandated remit to govern with respect.

 3. solac
  “የዜና ተላላኪ” የሚለው ቃል ችግር ያለው አይመስለኝም፡፡ ችግር ለመፍጠር ከተፈለገ ግን ሶስት ጊዜ ሰላምታ አንዱ ለነገር ነው ይባላል፡፡ ይህንኑ ቃል VOA የአማርኛው አገልግሎትም ይጠቀምበታል፡፡

 4. Thank you for reporter. We have almost forgotten that we have a parliament. It is shame, I do not even know who is in the parliament. I only know Ato Melese, Ato Abdula and Ato Girma. But that aside, If I am not wrong, parliament is a chamber of debate. If there is no opposition to debate with there is no need for standing Member of Parliament on full pay and privileges. Like Mengistu time and in any one party system the parliament could gather twice a year to listen to reports, approve plan of actions and delegate actions to the executives and return home to engage in productive activities. That way, a great deal of resources could be saved. It is my humble suggestion for the decision makers to consider. If the opposition succeed to win seats on the next election,then we can open the chamber of debate. If not we can continue as it is. Keeping 540 able bodies without productive activities 5 days a week and 48 weeks a year just to agree with each other gives the impression to exterrnal observers that we have not yet grasphed the prurpose of a parliament. It is a debating chamber if we have not yet figured out already.

 5. It is interesting. Assuming basic salary is 3 thousand birr per month, 540 members take home more than 97 million in five year time. And this is excluding other previlages such as housing. This is really a waste of public money.

Comments are closed