Logo

የዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳን የሕይወት ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ታተመ

July 18, 2011

ዳንኤል ተፈራ በተባለ ጋዜጠኛ ተጽፎ ለንባብ የበቃው ይኸው መጽሐፍ ‘ዳንዲ’ “የነጋሦ መንገድ” በሚል ርዕስ የታተመ ሲሆን፣ የዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳን የሕይወት ታሪክ ከተወለዱበት ደንቢዶሎ እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች እንቅስቃሴ፣ ከዚያም የጀርመንን የስደት ሕይወትና ከኦነግ ጋር የነበራቸውን ትግል፣ የኢህአዴግ አባልነትና ርዕሰ ብሔርነት እንዲሁም አሁን እስካሉበት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራርነት ያሳለፉትን ውጣ ውረድ ያስቃኛል ሲል የሪፖርተራችን ዘገባ አመልክቷል።

ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት ሲዘጋጅ አርቃቂ ኮሚሽኑን በሊቀ መንበርነት መምራታቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ በዚያ ወቅት የነበረውን ሁኔታ በተመለከተ፣ “እኔና ዳዊት ዮሐንስ አንቀጽ 39 መኖር አለበት፣ መሬትም መሸጥ መለወጥ የለበትም ብለን ተከራክረናል። …የብሔር ጥያቄን በተመለከተ የኦሮሞ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል መከበር አለበት የሚል ነበር አቋሜ። አሁንም የሕዝቡ የራሱን እድል በራስ የመወሰን መብት መከበር ትክክል ነው። ዴሞክራሲያዊም ነው” በማለት ያኔም ሆነ አሁን በተለያዩ ፖለቲካዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ያላቸውን አቋም የሕይወት ታሪካቸውን አጠናቅሮ በቀረበው መጽሐፍ ላይ ገልጸዋል።

ለሀገሪቱ ርዕሰ ብሔርነት እንዴት እንደታጩና ማን እንዳነጋገራቸው በዝርዝር ያስረዱት ዶ/ር ነጋሦ፣ እርሳቸው ከመታጨታቸው በፊት ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ለፕሬዝዳንትነት ከብአዴን ተጠቁመው እንደነበርና ‘የኢትዮጵያ ሕዝብ ሴት ርእሰ ብሔር ለመምረጥ ዝግጁነት የለውም’ በሚል ምክንያት ሃሳቡ ውድቅ መደረጉን ዶ/ር ነጋሦ አብራርተዋል። አቶ መለስ “በመንግስት ስራ የምታሳልፈው 15% ሲሆን፣ ቀሪውን 85% በድርጅት ስራ ታውላለህ” በማለት እንዳግባቧቸውም ዶ/ር ነጋሦ ተናግረዋል።

ከሕወሓት የተገነጠለውን “ውሕዳን” ቡድን በተመለከተ “ከታገዱት ግለሰቦች ጋር ወገንተኛነት አለህ የሚለውን ለመቀበል ሊያሳምነኝ የሚችል ምክንያት አላገኘሁም… እንዲያውም ውህዳኑ ጥፋት መፈጸማቸውን በግልጽ ተናግሬአለሁ” በማለት ዶ/ር ነጋሦ በወቅቱ የያዙትን አቋም በመጽሐፉ ላይ ገልጸዋል ሲል የሪፖርተራችን ዘገባ አመልክቷል።

ዶ/ር ነጋሦ በሕይወታቸው የሚያስቆጫቸው ነገር ምን እንደሆነም ተጠይቀው ሲመልሱ “…በክፍፍሉ ወቅት የኢህአዴግን የሸረኛነት ባህሪ አለመገንዘቤ አሁን ድረስ ይጸጽተኛል” የሚል ምላሽ መስጠታቸው በመጽሐፉ ላይ እንደሚነበብ የሪፖርተራችን ዘገባ ያብራራል።

የኢህአዴግ የልማት ድርጅቶችን በተመለከተም ዶ/ር ነጋሦ አውቃለሁ ያሉትን ሃሰብ የሕይወት ታሪካቸውን በዘገበው በዚሁ መጽሐፍ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፣ “የኤፈርት ገንዘብ ከየት መጣ? የሚል ጥያቄ ተነስቶ፣ መለስ ‘ሕወሓት በትግል ጊዜ በተለያዩ መንገዶች ገንዘብ ያገኝ ነበር። የሚያገኘውን ገንዘብ ግን ሙሉ ለሙሉ አላጠፋውም። በትጥቅ ትግሉ ጊዜ የሚያስፈልገውን ያህል ከተጠቀመ በኋላ የተቀረውን ባንክ ውስጥ አስቀምጦ ስለነበር የተወሰነውን በኤፈርት ድርጅቶች ላይ ኢንቨስት አድርጓል’ አለ። ታዲያ ይሄ ገንዘብ የማን ነው ሲባል በቁጣ ‘ይሄ ገንዘብማ የህወሓት ነው። ሌላ ማንንም አያገባውም’ ብሎን አረፈ። በእውነት በጣም ደስ አይልም። እጅግ ነበር የተሰማኝ” የሚል ቁጭት የተቀላቀለበት ምላሽ መስጠታቸው በመጽሐፉ ላይ ይነበባል ሲል ሪፖርተራችን ዘግቧል።

የኢህአዴግ አባል ሆነው ያሳለፉትን ጊዜ በተመለከተም “ከሁሉም በላይ ከዚህ ድርጅት ጋር መቀጠል የለብኝም ብየ እንድወስን ያስገደደኝ፣ ኢህአዴግ የሚመራበትን ርዕዮተ-ዓለም እንደቀየረ በተገለጸበት ጊዜ ነው። በዚያ ስብሰባ ‘ማርክሲስት ሌኒኒስት አለ ወይ? የሶሻሊዝም ጉዳይ ቀረ?’ የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር። ‘ማርክሲስት ሌኒኒስት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የለም። ሰዎች ቢኖሩም እንደ ቡድን ኢህአዴግን የሚመራ ርዕዮተ-ዓለም መሆኑ ቀርቷል። ሶሻሊዝምን ጠረጴዛችን ስር ደብቀነዋል። ከምዕራባውያን ድጋፍ ለማግኘትና የኢትዮጵያ ሕዝብ በደርግ የተነሳ ስለጠላው የምናራምደው ነጭ ካፒታሊዝም ነው’ አለ መለስ። ‘እስከ መቼ?’ ሲባል ‘ይሄ የኔ ጉዳይ አደለም። እስከ ልጅ ልጅ ሊዘልቅ ይችላል’… ‘ይሄን መቼ ወሰናችሁ?’ ሲባል ደግሞ፣ ‘ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ነው’ አለ። ብዙ ሰው ነው ብግን ያለው… እኔማ ቅጥል አልኩ። ለካ አስር ዓመት ሙሉ አታሎን ነበር…” ይላሉ አሁን የሊበራል ዴሞክራሲንና የነፃ የገበያ ስርዓትን የሚያቀነቅነውን አንድነት ፓርቲን በምክትል ፕሬዝዳንትነት የሚመሩት አፍቃሬ ማርክሲስቱ ዶ/ር ነጋሦ።

በመጽሐፉ ላይ እንደተመለከተው “ቅንጅትን ማን አፈረሰው?” የሚልም ጥያቄ ለዶ/ር ነጋሦ ቀርቦላቸው ነበር። ለዚህ ጥያቄ “ለኔ ኢዴፓ እና በአቶ አየለ ጫሚሶ የሚመራው ቡድን ናቸው” የሚል አጭር መልስ ካስቀመጡ በኋላ ወረድ ይሉና “ኢህአዴግም የራሱ ትልቅ ድርሻ አለው” በማለት ለቅንጅት መፍረስ ተጠያቂ የሚሆን ሶስተኛ አካል ይጨምራሉ። በዚህ ሳያቆሙ አሁንም ወረድ ይሉና “ምርጫ ቦርድና ፍርድ ቤትም አስተዋጽዖ አድርገዋል” በማለት የቅንጅትን አፍራሾች ቁጥር ወደ አምስት ከፍ ያደርጉታል ሲል ሪፖርተራችን የላከልን ዘገባ ያብራራል፡፡

ዶ/ር ነጋሦ የሕይወት ታሪካቸውን የተናገሩበት ይኸው መጽሐፍ ዋጋ ሃምሳ ብር ሲሆን፣ ጋዜጠኛ ዳንኤል ተፈራ መጽሐፉን ለማዘጋጀት ከዶ/ር ነጋሦ ጋር ሦስት ወራት የፈጀ ቃለ ምልልስ ማድረጉንም በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ገልጿል።

Share

18 comments on “የዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳን የሕይወት ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ታተመ

 1. ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል እንደ * ይጠየፉ የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜም ለምን ለኦጋዴን ህዝብ የሪፈረንደም እድል ሰጥተነው እዚያ አካባቢ ያለውን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ አንፈታውም ብለው ለአቶ መለስ ሀሳብ አቅርበው መለስ ክፉኛ ተቆጥቷቸው ነበር ይባላል:: ምናልባት መጽሀፋቸው ላይ ጠቅሰውት ይሆን?

 2. arega,

  negaso was not an insider does not mean he did not know anything about kinijit. this is an information age. if you have the verve, you can learn and say a lot even about foreign political parties, let alone homegrown ones like kinijit. even ordinary, apolitical guys like me can tell for sure who is responsible for kinijit’s demise.

 3. this man is one of the disgress of the Ethiopian opposition. he is selfish, has no stand and above all has no any popularity. the best thing to him is to retire and go to church.

 4. የህገ መንግስቱ አርቃቂ ኮሚሽን ሊቀመንበር ክፍሌ ወዳጆ መስለውኝ ነበር

 5. Negaso is still working for article 39.wheather you like it or not Negaso joined Andnet because he found a power gap.nothing more.He vever believe in one Ethiopia. He is one of the few who were diging a hole to bury Ethiopia but fortunatly he got power “president ´´ until he quarels with Meles as an individual not because of Ethiopia and ethiopians. It was purely personal case.Negaso never ask a question or raise an issue of Ethiopia as a parlamanterian his qustions or comments were only ´´oromiya“.i wonder for ´´Andnet´“` poor party who can´t find a leader from 80 million Ethiopians and found a Woyane leftovers.

 6. Negaso is against EDP it is clear for me because EDP leaders are wise and they know his anti Ethiopia activity from the begining. Ledetu was in struggle against woyane (Negaso and Meles) when he was a presedent so It is ´to be foolish to expect a positive comment about EDP from Negaso. Negaso knows how strong belief and prinsiple EDP has concetning one Ethiopia and Ethiopians.

 7. Thank you Romeo!
  This man is already damaged Ethiopa. I can say destroyed it . He worked against Ethiopa and Amharic langugage in Germany . We know what he didvery well but the so called andnet leders if they exist did knoe nothing about him kkkkkkkkkkkkkk

 8. I respect OLF leaders than Negaso. Negaso has no stand.First he betray OLF and now woyane tomorrow he betry Andnet. He is a pure opportunist.I reaaly don´t like such selfish person.

 9. Negaso has no jobb.His wife also is jobbles foerigner.
  As I know Negaso has no income. He has never worked professionally. he was president and then he earn salary from the parleamen.Now no income att all so the only income generating means is to lead a ´´political party´´ especially Andnet who collected money in millions for few years back not now of course. Now many of the vocal diaspora understand and learned a lesson. Only fools contribute to Andnet

 10. Who is Negaso to comment Kinijit. Is he really concerned about Kinijit?I don´t think that.Negaso was woyany when EDP exposes all woyane /EPRDGs anti Ethiopia move. He is responseble for all damage done with woyane. EDP is against 25 points in the constitution written by Negaso so what do you expekt from Negaso about EDP?

 11. Negaso is a ´´Dr`´ why he didn´t write himself? may be he cant write in Amharic or english . He may write it in oromifa but no oromo may buy it kkkkkkkk
  Let negaso learn how towrite a book from Lidetu Ayalew.

 12. Gemechu,

  i share some of your disappointment about abandoning this today and joining that tomorrow. i hate opportunism. but Negaso had no reason to give up on EPRDF if all that mattered to him were money. i think the income thing you mentioned is irrelevant.

 13. Negaso confirmed that he is socialist!!!!! . Thank you.
  A good news to all´´ he will be a best leader to Andnet´´.

  Negaso is pure opportunist . I agree with the above comments

 14. About Dr. Nagaasso:
  First of all I thank those guys who tried to write their witnesses about his historical facts that he did against one Ethiopia.
  Additional living facts:
  1. He wrote his thesis (diplma works) on western Wollaggaa oroommoo peoples as the only oppresseed people in Ethiopia.
  2. He strongly worked against Amhara and the language Amharic during his long time stay in Germany “Frankfurt” with his German wife deeply working to dismantle OROOMIYAA from her mother Ethiopia
  and organized (forwarded) the Orooomoo people to use the Latine Alphabets which was for the first time by one German originated in the late 19 century. (This German man has lived with the then Gaallaas in Ethiopia.)
  3. He has no concrete stand politically, that is why he left what did for years and joined the Woyane leadership
  and came back to Ethiopia from his exile and served for Wayne until Woyane dismissed him from power.
  4. Even though he is an old man he dreams even now a Politica Power, that is why he joined the Andnet Party,
  To tell the truth he never accepts Andnet within Ethiopians and One Ethiopia. Read his PhD Desertation and collect informations during his stay in Germany.

 15. Negasso Gidada was dumb enough not to realise he was the biggest pawn(and a pathetic joke)when he was the name-only President of our Country. He was chewed and spat-out .Thats the price opportunists get paid in,and this was not forgotten by Meles and co. He desrves his misery,but i say he should stop dabbling on matters of kinijit or EDP-as he is the least qualified to comment. He has done more harm to his `OROMO` dream,the least we need is this man trying to interpret history in his warped, opportunistic,unqualified way for a better ONE Ethiopia!

Comments are closed