Logo

እነማሙሸት አማረ በፍ/ቤት አሸነፉ፣ ኢ/ር ኃይሉ ከመኢአድ ፕሬዝዳንትነት ይባረሩ ይሆን?

August 6, 2011

የዚህ ውዝግብ ዋነኛ ምክንያት ተብሎ የሚገለጸው ኢ/ር ኃይሉ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ውጪ አቶ ያዕቆብ ልኬን ምክትል ፕሬዝዳንት አድርገው መሾማቸው መሆኑንም በዘገባዎቻችን አመልክተናል።

ይኸው መኢአድ ውስጥ የተከሰተ ሽኩቻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጋመና እየተፋፋመ በመሄዱ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ተሸጋግሮ እነ ማሙሸት አማረ ወደ መኢአድ ጽ/ቤት እንዳይደርሱ ሲደረግ፣ ከአቶ ማሙሸት ጋር የነበሩት ሌላኛው የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ እና አቶ ግርማ አጋ በእነ ኢ/ር ኃይሉ በወንጀል ተከሰው በፍ/ቤት በተሰጠ ውሳኔ ሁለት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወርደዋል።

ጉዳዩን እየተከታተለ ያለው ሪፖርተራችን በላከልን ተከታይ ዘገባ መሰረት፣ ዶ/ር ታዲዎስ እና አቶ ግርማ አጋ ከታሰሩ በኋላ፣ ኢ/ር ኃይሉ እነ ማሙሸት አማረን ወደ መኢአድ ጽ/ቤት እንዳይገቡ በማድረግ ከፓርቲው ደንብ ውጪ ጠቅላላ ጉባዔው ሳይሰበሰብ በተባረሩትና በታሰሩት ሰዎች ምትክ አዳዲስ የላዕላይ ምክር ቤት እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን በመሾም ቢሮውን ሲገለገሉበት እንደነበር ሪፖርተራችን ገልፆ፣ ይሁን እንጂ እነ ማሙሸት አማረ ኢ/ር ኃይሉ ከፓርቲው ደንብ ውጪ እያደረጉት ያለውን ሕገ ወጥ አካሄድ ገልጸው ለፍርድ ቤት በሰጡት መልስ የአራዳ ፍ/ቤት ሰኔ 21 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት በኢ/ር ኃይሉ የቀረበውን ክስ በሙሉ ውድቅ በማድረግ እነ ኢ/ር ኃይሉ የያዙትን ቢሮ ለእነ ማሙሸት አማረ እንዲያስረክቡ ውሳኔ ማሳለፉን አብራርቷል።

ይሁን እንጂ፣ እነ ኢ/ር ኃይሉ በፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ባለመቀበል ቢሮውን እስከ አሁን ድረስ ሊያስረክቡ ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም ያለው የሪፖርተራችን ዘገባ፣ በዚህም መሰረት የእነ ማሙሸት ቡድን የአፈጻጸም ትዕዛዝ አውጥቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቶ ሊሳካላቸው ባለመቻሉ ጉዳዩን ለፍ/ቤቱ ተመልሰው ማቅረባቸውን አመልክቷል።

የአራዳው ፍ/ቤት ትናንት ሀሙስ ሀምሌ 28 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት የፍ/ቤት ትእዛዝ ያላከበሩት እነ ኢ/ር ኃይሉ ሻውል በፖሊስ ተገደው እንዲቀርቡ ሲወስን፣ ቢሮውንም ዛሬ ዓርብ ሐምሌ 29 ቀን 2003 ዓ.ም ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት የወረዳው አስተዳደርና የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ለእነ ማሙሸት አማረ እንዲያስረክቡ ውሳኔ ማሳለፉን ሪፖርተራችን ያጠናቀረው ዜና አመልክቷል።

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሸናፊነትን የተቀዳጁት እነ ማሙሸት አማረ ቢሮውን ከተረከቡ በኋላ ምን እንደሚያደርጉና ከእነ ኢ/ር ኃይሉ ጋር በጋራ የሚሰሩ ስለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ “ፍትህ” የተሰኘ ጋዜጣ ጥያቄ ያቀረበላቸው ሲሆን፣ አቶ ማሙሸት አማረ በሰጡት ምላሽ “እኛ ቢሮውን እንደተረከብን የላዕላይ ምክር ቤቱ ስብሰባ እንዲጠራ እናደርጋለን። ከዚህ ጋር ግን መታወቅ ያለበት ጉዳይ የሚጠሩት የላእላይ ምክር ቤት አባላት በታህሳስ ወር 2003 ዓ.ም በተካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ የተመረጡትን እንጂ ኢ/ር ኃይሉ እኛን አባርሬአለሁ በማለት ከፓርቲው ደንብ ውጪ ለቃቅመው ያመጧቸውን ሊሆን አይችልም። እናም ሁሉም ነገር የሚወሰነው በላእላይ ምክር ቤት ይሆናል ማለት ነው” የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ሪፖርተራችን ፍትህ ጋዜጣን ዋቢ አድርጎ የላከልን ዘገባ ያመለክታል።

ይህም ሁኔታ ኢ/ር ኃይሉ ሻውልን ከመኢአድ ፕሬዝዳንትነት ሊያሰናብት እንደሚችልና የመኢአድን የውስጥ ጉዳይ ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚያሸጋግረው ሪፖርተራችን ገልፆ፣ በሌላ በኩል ግን ዲያስፖራው ገንዘቡን ለመኢአድ የሚለግሰው በኢ/ር ኃይሉ በኩል ስለነበር እነ ማሙሸት አማረ ቢሮውን ቢይዙም መኢአድን ወደፊት ይዘው ለመሄድ የሚችሉበት የፋይናነስ አቅም ሊኖር እንደማይችል ሪፖርተራችን ያሰባሰባቸው አስተያየቶች ያመለክታሉ።

Share

7 comments on “እነማሙሸት አማረ በፍ/ቤት አሸነፉ፣ ኢ/ር ኃይሉ ከመኢአድ ፕሬዝዳንትነት ይባረሩ ይሆን?

 1. Diaspora members contribute into Hailu Shawel’s account? Nice one! I was just wondering how he managed to purchase a delightful house in the States for himself. This was the man who was going to lead Ethiopia had his party won the 2005 elections. Thank god woyane ‘rigged’ the election.

 2. MEAD is dead when they elect Mamushet as secretary. He knows only insulting and smearing .I am so sorry to such white liers in the opposition camp. I heard him one before the past electoion in one paltalk room when he lied .He said that there is no candidate from woyane /EPRDF in BUgna and that was especially planned to bring Lidetu to the parlement.he added that MEAD has a candidate and Eng.hailu will gå to Bugna to campain for their candidate.
  I would like to ask him who is elected in Bugna and why Lidetu didn´t won. He is well known in labeling every member who has a bit different opinion as´´ woyane´´
  As to me Eng. hailu is better ´´dictator´´ than a white lier illitrate Mamushet.
  I am ashemed to be on the oppostion camp because of such nonsense individuas. There is a saying which said
  People get a leader that they deserve. It is true

 3. መኢአድ እንደዚህ በቀላሉ ይጠፋል ማለት በጣም ያስቸግራል:: ምክንያቱም በተለይ በገጠር መሰረት ያለው ድርጅት ስለሆነ ነው::

  በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል እንደሚባለው ፖለቲካና እሳትን ከሩቁ ይል የነበረውና በኋላ ምርጫ 97 እየተቃረበ ሲመጣ የህዝቡን ተንሳሽነት በማየት ለስልጣን ያለውን ጥማት ለማርካት ሲል በ11ኛው ሰአት ፖለቲካውን የተቀላቀለው ብርሃኑና ጓደኞቹ ትርምስምሱን አወጡት እንጂ መኢአድና ኢዴፓ አንዳንዴ እየተናቆሩም ቢሆን የፖለቲካ ሀሞቱ ፈሥሶ የነበረውን ህዝብ በማንቃትና በማደራጀት ከፍተኛ ስራ ሰርተው ነበር:: በከተማ የኢዴፓ ልጆች ባንዲራ ተከናንበው በየቀበሌው ቅስቀሳ ሲያረጉ በገጠር ደግሞ ኢንጅነር ሀይሉ ከትግል አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በፈረስ ጀርባ ላይ በመሆን የኪነት ባንድ ይዘው እልም ባለ ገጠር ሁሉ እየገቡ ነበር ቅስቀሳ ያደርጉ የነበረው::

  ዋናው ነጥብ መኢአድ ትግራይና ወለጋ ሳይቀር ደጋፊዎች ስላሉት በተጨማሪም በተለይ በገጠር ያሉ አባላቱ የህይወት ሁሉ መስዋእትነት የከፈሉበት ስለሆነ በአመራር ላይ ያሉት ሰዎች ፍርድ ቤት ከመሯሯጥ ተቻችለውና ታርቀው ጠቅላላ ጉባኤ ቢጠሩና አመራራሩን ለተተኪው ቢያስተላልፉ ጥሩ ነው::

 4. አንድ የዘነጋሁት ነገር ደግሞ ውጭ ያሉ አንዳንድ የመኢአድ ደጋፊዎች ከፓልቶክ እንደምሰማው አንዱን ማቅረብ ሌላውን ማግለል ስራዬ ብለው ተያይዘዋል:: ያ ድርጅቱን የበለጠ ያዳክመው እንደሆን እንጂ ምንም ጥቅም አያመጣም:: አንዱን ወያኔ ምናምን እያሉ ጥምብ እርኩሱን እያወጡ ሌላውን ደግሞ ከመካብ ሁሉንም በአንድ አይን በማየት ከወገንተኝነት በጸዳ መልኩ የገንዘብ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን የአስታራቂነት ሚናም መጫወት አለባቸው::

 5. I think it is time that there is truce in the warring factions with in AEUP leadership. Yes there may be problems with in the AEUP leadership.But it does not mean that they shold lose sight and focus of defending Ethiopia. As Ex US resident Abrham Lincoln stated, a divided house can not stand by itself.

  We should not forget that many people have died spearheading the struggle to defend Ethiopia since the early days of TPLF taking power in Ethiopia. We have to bear in mind and pause for a second that Ethiopia’s finest son, Professor Asrat, gave his life defending the terrirorial integrity and indivisibility of Ethiopia, its people and the tri colour green-yellow -red flag. Professor Asrat was instrumental to found AAPO which later changed to AEUP.

  So AEUP is not simply Engineer Hailu’s or Ato Mamushet’s party,it is the party of all Ethiopians who happily gave their life. Thus this senseless self-inflicted internal division must stop urgently.

 6. Who is going to forget the lion’s share contribution of AEUP in the shinning glorious days of Kinijit? It was AEUP which was the largest party with in Kinijit which made miracle. Most importantly, it is a multi national party which is the antithesis of TPLF’s ethnic policy.

  My advise to every pan Ethiopian is that we should be vigilant not to add to put fuel in further disintegration of AEUP, EDP and UDJ. In spite of all our differences, these partyies are based at home where the peaceful struggle matter most, they all transcend ethnic and religious divisions and they all have a firm stand on the territorial integrity and national soverignity of Ethiopia. Most importantly they are not opportunist and fake party like G7!

 7. Tazabi: AEUP has to reform for good or must die! AEUP should stop being a disgrace to Ethiopia. We just do not need another party with absolute monarchist and dictatorial mentality.

  The sooner the reform and reinviguration of AEUP, the better for the party and the struggle for that matter.

  So stop taking sides and tell to all the warring factions enough is enough.

Comments are closed