Logo

ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዴት ሰነበቱ

August 25, 2011

ኢ/ር ኃይሉ ለጋዜጣው በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ሁለቱ አንጃዎች ሊፈጠሩ የቻሉት እርሳቸው በፕሬዝዳንትነት እንደማይቀጥሉ በገለጹበት ወቅት መሆኑን አስታውሰው፣ በዚሁ መሰረት በፓርቲው ውስጥ የበላይነትን ለመጨበጥ በአቶ ያእቆብ ልኬ እና በእነ ማሙሸት አማረ መካከል ሽኩቻው መጀመሩንና በታህሳስ ወር አጋማሽ ገደማ የተሰየመው ጠቅላላ ጉባዔ ሁለቱ ቡድኖች በተፋጠጡበት ሁኔታ የተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

በጉባዔው እለት ፍጥጫው ጎልቶ መውጣቱን የተመለከቱ አንዳንድ የጉባዔው አባላት ከዚህ ሁሉ እኔ ለጊዜው በፕሬዝዳንትነት እንድቀጥል ለመኑኝ ያሉት ኢ/ር ኃይሉ፣ “እናም በምልጃ ለትንሽ ጊዜ እሰራለሁ ብዬ የመልቀቅ ሃሳቤን ለጊዜው ተውኩት። ምክንያቱም አንዱ ቡድን የበላይነት ይዞ ቢመረጥ ሌላው እንደማይቀበል እኔም አየሁት” በማለት በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ አብራርተዋል።

እርሳቸው ፕሬዝዳንትነቱን ከተቀበሉ በኋላ በሁለቱም ቡድኖች ውስጥ የነበሩ ሰዎች ወደ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንዲገቡ ማድረጋቸውን ኢ/ር ኃይሉ ገልጸው፣ ይሁን እንጂ ከጉባዔው ማግስት በኋላ አንዱ ቡድን ተጎድቻለሁ የሚል ቅሬታ በማምጣቱ እስከ አሁን ድረስ የዘለቀው የፓርቲው ችግር እየተባባሰ መምጣቱን አስረድተዋል።

“ይኸው ተገፋሁ የሚለው ቡድን አባላት ከጥቂት ጊዜ በኋላ የዚያኛውን ቡድን አባላት ቢሮ አትገቡም ብለው በር ዘጉ። እኛም ሁከት ይወገድልን ብለን ጉዳዩን ወደ ፍ/ቤት ወሰድነው። ፍ/ቤቱ ቢሮውን ተረከቡ አለ። ቢሮውን ጥለው በመውጣት ያለ የሌለ ውሸት በመደርደር ከሰሱን። መጀመሪያ ሁከት ይወገድላቸው ብሎ ለኛ የፈረደው ፍ/ቤት እኛን ሳያናግርና ወረቀትም ሳይሰጠን “በሩን በጥንቃቄ ገንጥላችሁ ግቡ” የሚል ትእዛዝ ሰጠ። ነገሩ እየተወሳሰበ ሄደ…” በማለት ኢ/ር ኃይሉ ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸውን ሪፖርተራችን ገልፆ፣ ባለፈው አስራ አምስት ቀን የፓርቲው ላእላይ ምክር ቤት በእየሩሳሌም ሆቴል ባደረገው ስብሰባ የሁለቱንም ቡድን አባላት ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና ከፓርቲው ጭምር ማባረሩን አብራርቷል። ኢ/ር ኃይሉ “ሥራ እንዳይሰራ የሚያደርጉትን አስወጥተናል፣ ውስጣችንን አጥርተናል” ማለታቸውንም ሪፖርተራችን ጨምሮ ገልጿል።

ቅንጅት፤

ባለፈው ሳምንት የቅንጅት ፕሬዝዳንት አቶ አየለ ጫሚሶ ከፕሬዝዳንትነትና ከፓርቲ አባልነት ተባረሩ፣ የፓርቲው ጽ/ቤት ታሸገ ሲል ሪፖርተራችን የላከልን ዘገባ አመለከተ። በአቶ አየለ ጫሚሶ ሲመራ የነበረው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (ቅንጅት) ፕሬዝዳንቱን አባሮ ዋና ፀሐፊውን አቶ ሳሳሁልህ ከበደን ፕሬዝዳንት ማድረጉ ታውቋል።

ቀደም ሲል የመኢአድ መስራችና አደራጅ ሆነው ለረጅም ዓመታት በተቃዋሚው ጎራ ውስጥ የቆዩት አቶ ሳሳሁልህ ከበደ ፕሬዝዳንት የሆኑት፣ አቶ አየለ ጫሚሶ የፓርቲውን ገንዘብ ለግላቸው በማዋል፣ የፓርቲውን ማህተም ተጠቅመው ወደ ውጪ ለሚሄዱ ዜጎች ደብዳቤ እየጻፉ ገንዘብ በመቀበላቸው፣ የፓርቲውን ቢሮ ከፍለው ለግለሰብ በማከራየታቸውና በመሳሰሉት ተግባራት ከፓርቲው እንዲባረሩ በመደረጋቸው መሆኑን ሪፖርተራችን ዘግቧል።

አቶ ሳሳሁልህ ከበደ የፕሬዝዳንትነት ስልጣን ተረክበው በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ አቶ ሰርጎ አለሙ የተባሉ ግለሰብ ለኪራይ ቤቶች ድርጅት ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የፓርቲው ጽ/ቤት መታሸጉ ታውቋል። አቶ ሰርጎ አለሙ ከቅንጅት ቢሮ የተወሰነውን ክፍል ከአቶ አየለ ጫሚሶ ጋር ውል ተፈራርመው ተከራይተው ሳለ እነ አቶ ሳሳሁልህ ከበደ ስላባረሯቸው ለኪራይ ቤቶች ድርጅት ማመልከታቸው ታውቋል ሲል ሪፖርተራችን ዘግቧል።

ኦብኮ፤

የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) ሊቀ መንበር አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ ከሀገር መኮብለላቸው ታወቀ። ዶ/ር መራራ ጉዲና ከአስር ዓመታት በላይ በሊቀ መንበርነት ሲመሩት የነበረውን የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) ከምርጫ 97 በኋላ መፈንቅለ ስልጣን አድርገው ኦብኮን በሊቀ መንበርነት እየመሩ ያሉት አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ ወደ ውጪ ሀገር መኮብለላቸውን ሪፖርተራችን የላከልን ዘገባ አመልክቷል።

አቶ ቶሎሳ ወደ ውጪ ሀገር የኮበለሉት ፖሊስ በወንጀል ጠርጥሮ እየፈለጋቸው በመሆኑ ነው ተብሏል። በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ባወጣው ዘገባ አቶ ቶሎሳ ከግለሰቦች ላይ አንድ ሚሊዮን ብር ገደማ አጭበርብረው መውሰዳቸው ታውቋል።

ኢዴፓ፤

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በርሃብ የተጎዱ ዜጎችን በተመለከተ መግለጫ ማውጣቱና፣ የንግዱ ኅብረተሰብ ግብር ይደብቃል መባሉን መንቀፉ ታውቀ። ፓርቲው ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ በዝናብ እጥረት ምክንያት የተከሰተውን ድርቅና ርሃብ ተከትሎ የተፈጠረውን ሞትና ስደት በመከላከሉ ረገድ ኢህአዴግ ኃላፊነቱን በአግባቡ አልተወጣም በማለት አስታውቋል።

“ቅድሚያ ትኩረት የዜጎችን ህይወት ለማዳን ይሁን” በሚል ርእስ ፓርቲው ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ በቅርቡ ለተከሰተው የዝናብ እጥረት ኢህአዴግን ተጠያቂ ማድረግ ባይቻልም ድርቅ እንዳይከሰት አካባቢን ማልማትና ድርቁ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ረሃብ በመፍጠር በሰው ህይወትና በእንስሳት ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት የመከላከል ስራው የመንግስት ኃላፊነትና ግዴታ ነው ብሏል – ኢዴፓ። ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ይህንን ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ ተጠያቂ መሆኑንም ፓርቲው ገልጿል።

በተያያዘ ዜና፣ ግብር ከፋዩን ኅብረተሰብ “ግብርን ይደብቃል” በሚል በጅምላ በመጠርጠር በግምት ከአቅሙ በላይ ጫና ለማሳረፍ የተደረገውን ሂደት ኢዴፓ አጥብቆ እንደሚቃወም ፕሬዝዳንቱ አቶ ሙሼ ሰሙ አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያስታወቁት፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን “የኛ ጉዳይ” በሚል ፕሮግራም በተደረገ ውይይት ላይ መሆኑን ሪፖርተራችን የላከልን ዘገባ አመልክቷል።

የኢዴፓ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት መንግስት ከዩኒቨርሲቲ የወጡ ልምድ የሌላቸው አዳዲስ ተመራቂዎችን አጭር ስልጠና በመስጠት በየንግድ ተቋማቱ ለአምስትና አስር ደቂቃዎች ቆም ብለው በማየት የሚጥሉትን ግብር ፓርቲያቸው ትክክል ነው ብሎ እንደማይቀበል ገልጸዋል።

አንድነት፤

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ (አንድነት) “ገጽታን ለማሳመር ሲባል የዜጎችን መራብ መደበቅ በታሪክ ያስጠይቃል” ሲል አሳሰበ። አንድነት ፓርቲ ይህንን ያሳሰበው “ፍኖተ ነፃነት” በሚባለው የፓርቲው ልሳን ላይ ባወጣው ርእሰ አንቀጽ መሆኑን ሪፖርተራችን ገልጿል።

የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ‘ድርቅ እንጂ ርሃብ የለም’ ማለታቸውን ፓርቲው በርእሰ አንቀጹ አስታውሶ፣ ይህ አባባል “በግማሽ እውነት ላይ የተመሰረተ ነው” ሲል ተችቷል። የጋዜጣው ርእሰ አንቀጽ አያይዞም፣ ድርቅ ስላለ የግዴታ ርሃብ አለ ለማለት የማይቻል መሆኑን ያደጉ ሀገሮችን ተሞክሮ በምሳሌነት በመጥቀስ አብራርቷል።

ስለሆነም፣ “ርሃብ አለ፣ የተራበም ሕዝብ አለ። ነገር ግን እየደረስንለት ነው። አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ እያደረግን ነው ማለት የአባት ነው። የሀገርን ገጽታ ላለማበላሸት በሚል ከንቱ ሰበብ ‘ድርቅ እንጂ ርሃብ የለም’ ማለት ግን ነውር ነው። በታሪክም ያስጠይቃል” ብሏል አንድነት ፓርቲ – በፓርቲው ልሳን ላይ ባሰፈረው ርእሰ አንቀጽ።

Share

8 comments on “ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዴት ሰነበቱ

 1. tolossa did the right thing if the one million birr was obtained from ala moudin or azeb mesfin.

  hailu shawul is playing with borrowed time. he should have retired long time ago, not just from mead but from politicis all together.

  edp and andinet look calm and composed. but they are toothless organizations that do not pass the sniff test given the mind-boggling challenges lying in front of us.

  chamiso and ‘kinijit’ is simply a joke. woyane only support chamiso and his buddies.

 2. negative,negative,negative = solac. Do you have any positive suggestions you think should lead the struggle,instead of sitting in a dark corner being a sniff tester? You said it,not me!

 3. Thank you “Le`Nesanet”. I think s/he is not Ethiopian. በሚጽፈው ነገር ሁሉ ኢትዮጵያዊ ቃና እንኳ አይቼበት አላውቅም፡፡ የሰውን ልጅ ደግሞ ንግግሩ/ጽሁፉ ነው የሚገልጸው፡፡ ወይ አለመታደል አሉ ፊታውራሪ….! እባክህ እደግ solac! በእድሜ ሳይሆን በአስተሳሰብ!!

 4. Le`Nesanet,

  i am only describing who they are, what they are doing. what positive news do you expect of me while the edme tegeb politicians are hell bent on destroying each other?

  if they cannot lead the struggle to victory, it is about time for them to retire amass from politics and pass on the torch of leadership to the younger generation.

  i do not want to flatter myself by praising these politicians when they have done nothing to deserve praise.

 5. Dagmawi Belay,

  truth is bitter. why do you fool yourself all the time? it is twenty years since opposition politics started in ethiopia. eprdf’s dictatorial behaviour aside, when was the last time the opposition demonstrated their willingness and ability to work together and offer the people of ethiopia a credible alternative? just because i say the opposition is amorphous and unreliable, you cant say am being impolite or devoid of ‘ethiopiawi qana.” i hate flattery and servility. edp and mead and udj have done nothing so far to move the struggle one step forward. if that is being impolite, so be it.

 6. To Solac- no question our current political aristocracy in the opposition,some of their own making,and some from situations out of their control have not attained what is expected of them to be serious contenders for public office.
  However,you cannot deny most,in fact all have sacrificed-from being unjustly imprisoned,harrassed,intimidated and soforth that its a miracle they did not end up with a fate like Prof.Asrat.
  What Im trying to point is,, DO YOUR PART, leave the criticism unless it is factually constructive and to realize every inch and centimetre of the struggle has value.-so long as the common denominator is a united Ethiopia.At this juncture,personalities are least of the worries,as the country cannot afford the luxury of a beauty contest. We might also differ in ideological outlook ( i do not consider disunity as an ideology,as it is not an “idea”, infact a Crime against the State called Ethiopia-my view*)as to how to reduce the mountain in front into rubble.There even might be a fifth column in the ruling party,where the Derg would have not collapsed the way it did.!-one does not know…All you can do is YOUR POSITIVE PARTand try to understand your negative comments are at best irrelevant and waste of cyber time.

 7. Solac,

  You said:

  “if they cannot lead the struggle to victory, it is about time for them to retire amass from politics and pass on the torch of leadership to the younger generation.”

  This is good! But it should include your favorite leaders Birhanu and Andargachew. They should retire too. ok?

 8. Belete,

  ya you are right. it also applies to g7 leaders. you cant feed the people of ethiopia empty rhetoric for ever. the struggle must be based in ethiopia, be it peaceful or violent.

Comments are closed