Logo

ኢዴፓ – በደቡብ ክልል የደቡብ ምዕራብ ንዑስ ቀጠና ጠቅላላ ጉባኤ

November 4, 2011

በጥናቱ መነሻነትም በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ ላይ  በሐምሌ ወር ባደረገው ስብሰባ በደቡብ ክልል የደቡብ ምዕራብና  የደቡብ ምስራቅ ቀጠናዎችን በማደራጅት ንዑስ ድርጅታዊ ጉባዔ እንዲደረግ ቅድመ ሁኔታዎችን ባመቻቸው መሰረት  የመጀመርያውን ንዑስ ደርጅታዊ ጉባኤውን ቅዳሜ ጥቅምት 18 ቀን 2004 ዓ.ም የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ሙሼ ሰሙና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ነጻነት ደመላሽ በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል፡፡

በንዑስ ድርጅታዊ  ጉባኤው ላይ  ከወላይታ ዞን 13 ወረዳዎች፣ ከዳውሮ ዞን 4 ወረዳዎች፣ ከኮንታ ልዩ ወረዳ ሁለት የምርጫ ክልሎች እንዲሁም ከጋሞጎፋ ዞን በከፊልና  ወደፊት በቀጠና ደረጃ በሚደረጉ ንዑስ ጉባኤዎች ላይ የሚሳተፉ አባላት የልምድ ልውውጥ እንዲያደረጉ ለማገዝ በደቡብ ክልል ከደቡብ ምስራቅ ቀጠና  ሲዳማ ዞን ከአለታወንዶ፣ ከጉጂ እና ከጌዴኦ ዞኖች የየዞኖቹ ኃላፊዎችን  ጨምሮ በጥቅሉ 30 አመራሮች  ተገኝተዋል፡፡

በዚሁ ንዑስ ጉባኤ ላይ የቀድሞ አመራሮች የሁለት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡና ውይይት የተካሄደበት ሲሆን፤ ኢዴፓ በከፍተኛ አመራሩ ውስጥ እያደረገ ያለውን የኃላፊነት ሽግግር  በፓርቲው የተለያዩ  መዋቅሮች ውስጥ  በተግባር እንዲለመድ ባለው እቅድ መሰረት አራት  የቀጠናውን ነባር አመራሮች በአዲስ በመተካትና ሶስት አዳዲስ አመራሮችን  መርጧል፡፡ ከተመረጡት አመራሮቹም ውስጥ ሁለት ሴቶች በምርጫ ውጤታቸው መሰረት ተካተዋል፡፡

በመካሄድ ላይ የሚገኝው ይህ ንዑስ ድርጅታዊ ጉባኤ በቀጣይ በሰሜን፤ በምስራቅና በምዕራብ ኢትዮጵያ የተለያዩ ዞኖችና ቀጠናዎች የሚቀጥል መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ምንጭ (Source) – http://edponline.org/

Share

3 comments on “ኢዴፓ – በደቡብ ክልል የደቡብ ምዕራብ ንዑስ ቀጠና ጠቅላላ ጉባኤ

  1. EDP is doing its job as usual from the ground unlike others that exists only by name but has no a single root.

    Go on EDP

Comments are closed