የኢትዮጵያ መምህራን ጥያቄና የትምህርት ሥራ
በገሞራው ካሣ
ሀ) እውን መምህራን የደሞዝ ጭማሪ አልጠየቁም?
ሚዚያ 14 ቀን 2004 ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ዜና ቀጥሎ ጠ/ሚኒስተሩ ፓርላማው ውስጥ ሆነው ቀደም ሲል ያካሄዱትን የጥያቄና መልስ ፕሮገራም እንዲደገም በሕዝብ ተጠይቋል ተብሎ ሲተላለፍ በቴሌቪዥን ተከታትያለሁ፡፡ ሕዝብ ከሳቸው አንደበት በቀጥታ መስማት ያለበት የሀገር አሳሳቢ ጉዳዮች ነበሩ የተነሱት፡፡ እኔን ይበልጥ ያሳሰበኝ አቶ መለስ በመምህራን ጉዳይ ላይ የተናገሩት ነው፡፡ ቃል በቃል ባልጠቅሳቸውም ፍሬ ነገሩ እንዲህ የሚል ነበር፡-