Logo

ኢዴፓ በቸሃ ወረዳ እምድብር ከተማ አስራ ሶስተኛ ቢሮውን ከፈተ

November 20, 2012

ቡድኑ በእምድብር ከተማ ከደረሰ በኃላ የፓርቲውን ዓላምና አቋሞች በመደገፍ  በቦታው ከተገኙ የማህበረሰቡ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱም ላይ  በማህበረሰቡ አካላት የተነሱት ጥያቄዎች  በአካባቢያቸው ስላለ ከፍተኛ ጭቆናና አፈናና  መደራጀት መብታቸው ስለሚጻረሩ ድርጊቶች የሚገልጹ ሲሆኑ ጭቆናና አፈናው የሚፈጸመው በግለሰቦች ላይ ብቻ ሳይሆን በአካባቢው መካሄድ የነበረበትን የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴዎች በማጨናገፍና በማስተጓጎል ጭምር ሲሆን የነበሩ መሰረተ ልማቶችም እንዳይጠናከሩ በማዳከም ከፍተኛ መድሎ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው የተገኝው ቡድን ባደረገው ጉብኝት መሰረታዊ መድሎውን ለመመልከት የቻለ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ ከበርካታ ኣመታት በፈት በጉራጌዎች መንገድ ስራ ድርጅት አማካኝነት ያሰራው የጥርጊያ መንገድ ዛሬም አስፋልት መልበስ አቅቶት ለጉዞ እጅግ አዳጋችና አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለመመልከት ችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ በአካባቢው ተገኝተው ከማህበረሰቡ ጋር በተወያዩበት ወቅት  ቃል ገብተውት የነበረው ሆስፒታልም እስካአሁን ድረስ የት እንደደረሰ ለማወቅ አለመቻሉን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ በአጠቃላይ አካባቢው ልማት እጅግ የራቀውና ትኩረት የተነፈገው በመሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ በልማት ኃላ ቀር ከሚባሉ ወረዳዎች እንኳን ባነሰ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑንን አስተውለናል፡፡

ይህንን ተከትሎ በፓርቲያችን ፕሬዚዳንት በተሰጠው ማብራርያ የቸሃ ወረዳ እምድብር ከተማ የኢዴፓ ደጋፊ ማህበረሰብ የአካባቢውን ችግሩን መፍቻ መንገዱ የመንግሰትን እጅ ማየት ብቻ እንዳልሆነ ከመገንዘቡም በላይ ከምርጫ 97 በኃላ የደረሰበትን  ተጽእኖ ሳይበግረው አማራጭ ሊሆነኝ ይችላል ያለውን ፓርቲ ኢዴፓን መምረጡና መብቱንና ጥቅሙነ ለማረጋግጥ በሰላማዊ መንገድ ትግሉን አጠናክሮ ለመቀጠል መወሰኑን አወድሰዋል፡፡

እንደዚህ አይነቱ ጠንካራ የራስ በራስ ተነሳሽነት ብዙ ጊዜ ያልተለመደ መሆኑን ጠቅሰው ሰላማዊ ትግሉ መንግሰትን በሰላማዊ መንገድ በምርጫ የመተካቱን የመጨረሻው ግብ ኢዴፓ ከመቀዳጀቱ በፊት ዜጎች በየ አካባቢያቸው ተደራጅተው መድሎን በመታገልና መብታቸውን በመጠየቅና መታገላቸው አካባቢዊ ልማትን ያለመድሉ ለማረጋገጥና በገዢው ፓርቲ ላይ ተጽእኖ ለማሳደር ትልቅ ጉልበት እንደሚሰጥ ገልጠዋል፡፡

ኢዴፓ በዚህ ዓመት ለማከናውን በያዘው እቅድ መሰረት በአለታ ወንዶና በወላይታ ከተሞች ቢሮዎችን የከፈተ ሲሆን  በላሊበላና በደሴ ስብሰባዎችን ማድረጉ ያታወሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በነዚህ ከተሞች ላይ ሁለት ንዑስ ጉባኤችን በማካሄድ አመራሮች የመረጠ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሁሉም ከተሞች በሚገኙ በርካታ  አጎራባች ወረዳዎች ላይ የማደራጀት ስራውን እያከናወነ  መሆኑን ፓርቲው ዘግቧል፡፡

Share

2 comments on “ኢዴፓ በቸሃ ወረዳ እምድብር ከተማ አስራ ሶስተኛ ቢሮውን ከፈተ

  1. የጉራጌና ኦሮሚያ አካባቢዎች በጣም የተረሱ ይመስላሉ:: በተለይ ወደ ገጠሩ አካባቢ:: ቢያንስ ቢያንስ ንጹህ ውሃና የኤሌክትሪክ መስመር አገልግሎት ለህዝቡ መቅረብ አለበት:: እስከመቼ በወንዝ ውሀ ይኖራል:: ለነገሩ ተቃዋሚ ፓርቲ እነደዚህ እንቅስቃሴ ማድረግ ሲጀምር ኢሃዴግም ፉክክር ውስጥ ስለሚገባ በሰበቡ በአካባቢው አንዳንድ የልማት እንቅስቃሴ ይጀመር ይሆናል::

Comments are closed