Logo

ከተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከኢዴፓ የተሰጠ መግለጫ

April 9, 2013

በፖለቲካም ሆነ በልማት ስም ያለበቂ ዝግጅትና ቅድመ ሁኔታ የተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ኢዴፓ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ባለፉት ዓመታት የአማራው ብሔረሰብ ተወላጆችና ሌሎችም ብሔር-ብሔረሰቦች በብሔረተኝነትና በፖለቲካ ምክንያት ሕይወታቸውን ከመሰረቱበት ቀየ ሲፈናቀሉና ሲሰደዱ መስማት የተለመደ ጉዳይ ነበር፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የመፈናቀሉ ጉዳይ ጋብ ያለ ቢመስልም የዛሬ ዓመት ገደማ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከጉራፈርዳ ወረዳ በርካታ የአማራ ተወላጆችን መፈናቀልን ተከትሎ በቅርቡ ከሶማሌ ክልላዊ መንግስት ከጅጅጋ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች መፈናቀላቸው ተዘግቧል፡፡ አሁን በቅርቡ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በሺህ የሚቆጠሩ አማራዎች የመፈናቀላቸው ጉዳይ ሰፊ የዜና ሽፋን አግኝቶል ከርሟል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከልማትና ከኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ ምክንያትም የኦሮሞው፣ የጋምቤላው፣ የአፋርና የሌሎች ብሔር- ብሔረሰቦች ከመኖርያ ሰፈራቸውና ከትውልድ ቀያቸው ያለበቂ ዝግጅትና ቅድመ ሁኔታ፤ የተገባላቸው ቃል ሳይከበርና ሕይወታቸውን ለማሳካት የሚያግዛቸው መሰረታዊ ነገር ሳይሟላ ተፈናቅለውና ተበትነው የመቅረታቸው ጉዳይ አሁንም የዓለም አቀፍና የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡

ዜጎች የሚፈናቀሉበት ምክንያት ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ አሊያም ብሔረተኝነት፤  የትውልድ ቦታቸውና መሰረታቸው ከየትኛውም ብሔር ይነሳ የሚፈናቀሉትበት መንገድ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀበለቻቸውና ስምምነት የተደረሰባቸው የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን ያከበረ መሆን አለበት፡፡ በተለይ ደግሞ በሕገ-መንግስታችን ውስጥ በክፍል አንድ ሰብዓዊ መብቶች  አስመልክቶ በአንቀጽ 14 ላይ የሕይወት፣ የአካል ደህንነትና የነጻነት መብትን አስመልክቶ በተደነገገው መሰረት “ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነጻነት መብት አለው፡፡” የሚለውንና እንዲሁም በአንቀጽ 25 የእኩልነት መብት አስመልክቶ “ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በሕግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ በዘር፣በብሔር ፣ በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው፡፡” የሚሉትና ሌሎችም መሰረታዊ የመብትና የሕልውና ጥያቄዎችን የማይጻረር መሆን ይገባዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (EDP)

Share