Logo

በአዲስ አበባ ግብረሰዶም በአስደንጋጭ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው!

August 12, 2013

*ግብረሰዶማዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ “ሬንቦ” የተባለ ማህበር አቋቁመዋል
*በግብረሰዶማውያን ዙርያ የተካሄዱ ጥናቶች አዳዲስ መረጃዎችን ይፋ አድርገዋል
*ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የጥቃት ሰለባ ሆነዋል
*ኢትዮጵያውያን ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ወሲብ ሲፈፅሙ የሚያሳዩ ፊልሞች ለገበያ ቀርበዋል

ከወራት በፊት እዚህ አዲስ አበባ ከተማችን ውስጥ የተፈፀመ ታሪክ ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈፀመው በአንድ ስመ-ጥር የወንዶች ልብስ መሸጫ ቡቲክ ውስጥ ነው፡፡ ወጣቱ በቡቲኩ ውስጥ ተቀጥሮ መስራት ከጀመረ ቆየት ብሏል፡፡ በአለባበሱ ሽቅርቅርና ዘመናዊ ነው፡፡ ወደ ቡቲኩ የሚመጡትን ደንበኞች በፈገግታና በትህትና እየተቀበለ ያስተናግዳል፡፡ ደንበኞች የፈለጉትን ልብስ አስወርደው ለመለካት ወደ መልበሻ ክፍል ሲገቡ በዓይኑ ይከተላቸዋል፡፡ በገቡበት የመልበሻ ክፍል መጋረጃ ላይ አይኖቹን ተክሎ ለደቂቃዎች እንደሚቆይ የቡቲኩ ባለቤት ብዙ ጊዜ ታዝቦታል፡፡ ሆኖም ደንበኞቹ አዲሱን ልብስ ለብሰው ሲወጡ ለማየት ከመጓጓት የተነሳ እየመሰለው በዝምታ ያልፈዋል፡፡ “ለምን እንዲህ ታያለህ?” ብሎ ጠይቆት አያውቅም፡፡

ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (አዲስ አድማስ)

Share

One comment on “በአዲስ አበባ ግብረሰዶም በአስደንጋጭ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው!

  1. አዲስ አድማስ ነገሩ ትኩረት እንዲያገኝ በየጊዜው የሚያደርገው ጥረት ሊያስመሰግነው ይገባል::
    ነገር ግን መንግስት ጉዳዩን ችላ ያለበት ምክንያት ግልጽ አይደለም::

Comments are closed