ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ አረፉ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) ለበርካታ አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ያገለገሉት ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ አረፉ።
ለረጅም ጊዜ በህመም ላይ ቆይተው በ83 ዓመታቸው ከሁለት ቀን በፊት ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
ዶክተር አምሳሉ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ከሚባልበት ዘመን ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያስተማሩ መምህር ነበሩ፡፡
የቀብር ስነ ስርአታቸው በደብረ ሳህል ሚካኤል (የካ ሚካኤል) በመጭው እሁድ ይፈጸማል።
በውጭ ሃገር የሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እስኪሰበሰቡ ድረስ የቀብር ስነ ስርአታቸው የሚፈጸምበት ቀን መዘግየቱን ከቤተሰቦቻቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ዶክተር አምሳሉ አብዛኞቻችን የመዝገበ ቃላትን አጠቃቀም የተማርንበትን እንግሊዝኛ – አማርኛ መዝገበ ቃላት በማዘጋጀት ይታወቃሉ።